ተደጋጋሚው የኢንተርኔት መዘጋት - በኢትዮጵያ

Loading...
861 Views
Published

በኢትዮጵያ የኢንተርኔት አገልግሎት ሙሉ ለሙሉ ከተቋረጠ አራት ቀናት ኾኖቷል። መንግሥት አገልግሎቱ መዘጋቱን አምኖ ይህ የተደርገው ከዚህ ቀደም ያጋጠመው የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት መልቀቂያ ፈተና ሾልኮ እንዳይወጣና ተማሪዎች ከስጋት እና ከመረበሽ ነፃ ሆነው እንዲፈተኑ ለማስቻል እንደሆነ አስታወቋል። የዩኒቨርስቲ መምሕራን እና የድረገጽ አምደኞች ድርጊቱን ይቃወሙታል። ለተነሱ ፖለቲካዊ ችግሮች መፍትሔ ከመስጠት ይልቅ ቴክኖሎጂውን ማፈን መፍትሔ አይሆንም ይላሉ።
Originally published at - https://amharic.voanews.com/a/ethiopia-internet-shetdown/3885311.html

Category
News