PLANET  ETHIOPIA.com

የወሲብ እርካታን/ፍላጎት ማጣት መፍትሔዎች (በዶር ቤቴል ደረጀ - የማህፀን እና ጽንስ ስፔሺያሊስት)

 

 

 

 

(በዶር ቤቴል ደረጀ - የማህፀን እና ጽንስ ስፔሺያሊስት)

የወሲብ እርካታን/ፍላጎት ማጣት መፍትሔዎች

ባለፈው ፅሁፌ የወሲብ እርካታን/ፍላጎት ማጣት መንስኤዎቻቸውን በአጭሩ ዘርዝሬ ነበር። በርካታ ተሳታፊዎች ላደረሳችሁኝ ጥያቄዎች እና አስተያየቶች ምስጋና እያቀረብኩ ዛሬ ደግሞ መፍትሔዎቹ ላይ ትንሽ እናውጋ።

አንድ ሰው የሥራ ኃላፊነቱን በአግባቡ ለመወጣት የአእምሮም የአካልም ጤንነት እደሚያስፈልገው ሁሉ ለጤናማ የወሲብ እርካታም የጤንነቱ ጉዳይ ወሳኝ ነው።

ብዙዎቻችሁ ጤናማ ነኝ፣ አልታመምኩም ግን ይህ ችግር ለምን እኔን አጋጠመኝ? ልትሉ ትችላላችሁ። እስቲ ራሳችሁን ጠይቁ፤ በሥራ የደከመ ሰውነት፣ ብዙ ባለጉዳይ ሲያስተናግድ የዋለ አእምሮ ተይዞ ወደ ቤት ሲገባ ስንቶቻችሁ ለፍቅር/ለትዳር አጋሮቻችሁ ከሞቀ ፈገግታ ጋር ትገባላችሁ?

ቤት የዋላችሁትስ ብትሆኑ ከውጭ ለሚመጣው/ለምትመጣው አጋራችሁ ስለዋላችሁበት ድካም በማውራት ነው ወይስ ለመንከባከብ በመሞከር ትቀበላላችሁ? የስነልቦና ዝግጅቱ ከዚህ ይጀምራል፡፡

‹‹እኔ እኮ እርሱን አላረካውም፣ የኔ የወሲብ አካል ትንሽ ስለሆነ እሷን ማርካት አልችልም፣ ደግሞ ምን ሊለኝ/ልትለኝ ይችል/ትችል ይሆን?›› የሚሉት ሀሳቦች ሁሉ የስነ-ልቦና አቅምን ስለሚያዳክሙ እራሳቸውንም አጋሮቻቸውንም ለማርካት እንቅፋት ይሆናሉ፡፡ በተለይ ደግሞ እነዚህ ሀሳቦች በግንኙነት ላይ ሆነው ሲታሰቡ ችግሩን ያብሰዋል። አለፍ ሲልም ጤናማ የፍቅር ግንኙነት እንዳይኖራቸው አስተዋፅኦ ያደርጋል።

ይህ ችግር በጭንቀት ውስጥ ያሉትን (stress/depression)፣ በትዳር ላይ ሆነው ልጅ ያላገኙትን፣ የመካንነት ምርመራ አድርገው ‹‹በኔ ምክንያት ነው ቤቱ ያልሞቀው›› ብለው የሚብሰከሰኩትን በአብዛኛው ይመለከታል።

ከዚህ በፊት የአስገድዶ መደፈር ጥቃት የደረሰባቸው (ወንድም ይሁን ሴት) ብዙውን ጊዜ በፈቃደኝነት በተመሠረተ የፍቅር ግንኙነት ላይ ጭምር ፍራቻ ይኖራቸዋል። ስለ ወሲባዊ ግንኙነት ሲያስቡ ያሳለፉት ዘግናኝ አጋጣሚ ትዝ ስለሚላቸው በግንኙነቱ አይደሰቱም ወይም ፈፅሞ አይፈልጉትም። በርትተው የሚፈፅሙትም ቢሆኑ በጥቃቱ የተፈጠረ አካላዊ ጠባሳ ካለ ከደስታ ይልቅ ህመምን ሊያስተናግዱ ይችላሉ።

ለረዥም ግዜ በህመም ላይ የቆዩ ሰዎች ደግሞ ዘወትር ስለህመማቸው እያሰቡ ከመብሰልሰል አልፈው እራሳቸውን ለወሲብ ፍላጎት ማነቃቃት ሲሳናቸው ይታያል። 
ከላይ ለማብራራት እንደሞከርኩት ከወሲብ በፊት የስነልቦና ዝግጅት በማድረግ ችግሮቹ ሊስተካከሉ ካልቻሉ ጥንዶች የስነ-ልቦና ድጋፍ በግልም ሆነ በጋራ ማድረግ ይገባቸዋል።

ቸር እንሰንብት

Related Articles

Post your comment