PLANET  ETHIOPIA.com

ፕሬዚዳንት ትራምፕ በወሩ መጨረሻ ከፕሬዚዳንት ቡሃሪ ጋር በኋይት ሃውስ ይወያያሉ

                  

የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ጋር በወሩ መጨረሻ ከናይጀሪያው አቻቸው ሙሃማዱ ቡሃሪ ጋር ሊወያዩ ነው።

የመሪዎቹ ውይይት የዛሬ ሁለት ሳምንት የሚካሄድ ይሆናል ተብሏል።

የኋይት ሃውስ ቃል አቀባይ ሳራ ሳንደርስ፥ ውይይቱ በፕሬዚዳንት ትራምፕ ግብዣ መሰረት እንደሚካሄድ ተናግረዋል።

ዶናልድ ትራምፕ ከፕሬዚዳንት ቡሃሪ ጋር የሃገራቱን የሁለትዮሽ ግንኙነት ማጠናከር በሚያስችሉ ጉዳዮች ዙሪያ ይወያያሉም ነው ያሉት ቃል አቀባይዋ።

ሽብርተኝነት፣ ኢኮኖሚያዊ እድገትና ማሻሻያዎች እና ሌሎች የፀጥታና የደህንነት ስጋት የሆኑ ጉዳዮች የመወያያቸው ነጥቦች ይሆናሉ ነው የተባለው።

ከዚህ ባለፈም ናይጀሪያ በምዕራብ አፍሪካ ያላትን የመሪነት ሚና ማጠናከር በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይም እንደሚመክሩ ይጠበቃል።

ምንጭ፦ ቢቢሲ

Related Articles

Post your comment