Entertainment

 • አንዲት እንስት አንበሳ የነብርን ግልገል እያጠባች ትገኛለች

  በጉድፈቻ ወይስ በመዋለድ ድንቅ የእናትነት ርህራሄ፡፡

  አንበሳና ነብር የተለያዩ ዝርያዎች ቢሆኑም አንዲት የታንዛኒያ እንስት አንበሳ በመካከላቸው ያለው ልዩነት ሳይገድባት ትንሿ የነብር ግልገል እያጠባች ትገኛለች፡፡

   

  በታንዛኒያ የአለም የዱር ነብር ጥበቃ ድርጅት የፓንዜራ ፕሬዚዳንትና የጥበቃ ኃላፊ ዶክተር ሉኬ ሁንተር አጋጣሚውን አስደናቂ ብለውታል፡፡

  በሁለቱ ተላላቅ የዱር እንስሳት መካከል የተፈጠረው ይህ አስደናቂ ሁኔታ ከዚህ ቀደም ታይቶ እንደማይታወቅ ዶክተር ሉኬ ተናግረዋል፡፡

   

  ብዙ ጊዜ አናብስቶች የነብር ግልገሎች ሲጠጓቸው ምግባቸውን የሚሻሙ እየመሰላቸው ይገድላቸዋል ብለዋል ዶክተር የተናገሩት፡፡

   

   

   

   

  Read more
 • ግሽ ዓባይ የኪነት ቡድን የት ነው?!

   የነፃነት አቀንቃኙ ማርቲን ሉተር ኪንግ "ዓለም ሁለት ታላቅ ስጦታዎች አሏት፡፡እነሱም የአምላክ ቃል እና ሙዚቃ ናቸው" ይላል፡፡

   በአማራ ክልል ቀደም ባለው ጊዚያት ፣ሶስት ግዙፍ የባህል ቡድኖች ነበሩ፡፡የፋሲለደስ፣የወሎ ላሊበላ እና የግሽ ዓባይ ቡድኖች፡፡እነዚህ የኪነት ቡድኖች እስከ 1984 ድረስ ባህልን በኪነጥበብ በማሳየት የላቀ አበርክቶት ነበራቸው፡፡ነገር ግን የጠናከረ ተቋማዊ አደረጃጀት ስላልነበራቸው ከ 1985 ዓ/ም ጀምሮ ጠፍተው ቆይተው ከ 2006 ዓ/ም ጀምረው ደግሞ እንቅስቃሴ ላይ ይገኛሉ፡፡

   የሰባት አውራጃዎች ወይም የጎጃም ክፍለሀገር ወኪል የነበረው ግሽ ዓባይ የባህል ቡድን የተመሰረተው ሀምሌ 5 ቀን 1972 ዓ/ም ነው፡፡በ 60 ያህል አባላት የተመሰረተው ግሽ ዓባይ የባህል ቡድን፣በሙዚቃ ብቻ ሳይሆን በስነፁሁፍ ዘርፉም ይሰራ ነበር፡፡

   

  እነ ይሁኔ በላይ፣ሰማኸኝ በለው፣ አንሙቴ ወዘተ የግሽ ዓባይ የባህል ቡድን ፍሬዎች ናቸው፡፡በ 13 ኛው የዓለም አቀፍ ወጣቶች ቀን ሀገር ብሎም አፍሪካን በመወከል በፒዮንግያግ ሰሜንኮርያ የኪነጥበብ ድግሱን አቅርቧል፡፡አቅርቦም ዓለም አቀፍ ተቀባይነት ተችሮታል፡፡

   

  ከ 1977 ዓ/ም በሀገሪቱ በተከሰተው ድርቅ የኪነት ቡድኑ ከመንግስት በጀት አጣ፡፡በእርግጥ ግሽ ዓባይ የኪነት ቡድን ቀድሞውንም ብዙ ድጋፍ የሚያገኘው ከህዝብ ነበር፡፡ግን ህዝቡ ለድርቁ ምላሽ ለመስጠት ግሽ ዓባይ ተዘነጋ፡፡በ 1978 ዓ/ም ግሽ ዓባይ ተደራጅቶ እስከ 1984 ዓ/ም ዘልቆ ነበር፡፡

   

  ከሽግግር መንግስቱ በኋላ ግሽ ዓባይ የባህል ቡድን በባህርዳር መሪ መዘጋጃቤት እንዲመራ በሚል የወቅቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ታምራት ላይኔ ደብዳቤ ፅፈው ነበር፡፡ነገር ግን መሪ ማዘጋጃ ቤቱ የኪነት ቡድኑን ለመደገፍ አቅም አነሰው፡፡ግሽ ዓባይም ፈረሰ ይላል ጋዜጠኛ ደረጀ ጥበቡ በኪነት ቡድኑ ዙሪያ ባቀረበው አጭር ጥናት፡፡

   

  የግሽ ዓባይን የኪነት ቡድን ወደ ነበረበት ግርማ ሞገሱ ለመመለስ ከ 4 ዓመት በፊት የባህር ዳር ከተማ አስተዳደር እርምጃ ጀምሯል፡፡የግሽ ዓባይ የባህል ቡድን ተመስርቷል፡፡የቱን ያህል እየተጓዘ ነው? በሌላ ጊዜ የምመለስበት ሆኖ የባህል ቡድኑ ከሰምኑ የፊታችን ቅዳሜ ጀምሮ የሙዚቃ ቀንን ያከብራል፡፡ከባህል ና ቱሪዝም ተቋማት፣ከኢትዮጲያ የሙዚቃ ማህበራት እና ከሌሎች አካላት ጋር ሆኖ ባለውለታዎቹን ይሸልማል፡፡የኪነት እንቅስቃሴውን ይቃኛል፡፡

   

   

   

  Read more
 • በወባ ትንኝ ደም ወንጀለኞችን ማግኘት እንደሚቻል ያውቃሉ?

  አንድ ወንጀለኛ የሰው ህይወት ካጠፋ እራሱን ለመደበቅ ሲል የእጅ አሻራውን፤ የእግር ዱካውን አጥፍቶ ያለምንም ማስረጃና ምስክር ሊኖር ይችላል፡፡

   ይሁንና ወንጀለኛው ወንጀሉን በፈጸመበት አካባቢ ላይ በወባ ትንኝ ተነድፎ ከነበረ ማንነቱን ለመለየት የሚያስችል ግኝት ላይ ደርሰናል ብለዋል ተመራማሪዎቹ፡፡

   የናጎያ ዩኒቨርሲቲ ተመራማሪዎች እንደሚገልጹት ከሆነ ወንጀለኛው በወባ ትንኟ ከተነደፈ በኋላ ባሉት 48 ሰዓታት ውስጥ የግለሰቡን ማንነት በመለየት በቀጥጥር ስር ማዋል ይቻላል፡፡

   የምርመራ ሂደቱም በወባ ትንኝ ውስጥ የተገኘው ዘረ መል የግለሰቡን ማንነት ስለሚያሳውቅ ለወንጀል መርማሪ ፖሊሶችም ቀላል መፍትሄ እንደሚያመጣላቸው ነው የተመራማሪዎቹ ቡድን መሪው ቶሺሚቺ ያማማቶ የገለጹት፡፡

   ይህን የምርመራ ዘዴያቸውን በፍቃደኛ ግለሰብ ላይ በመሞከር በወባ ትንኝ ውስጥ በተገኘ ደም ዘረመል ማንነቱን መለየት እንዳስቻላቸው ተናግረዋል፡፡

   

  ምንጭ፡ ዴይሊ ሜይል

   

  Read more
 • የ”ዘመን” የቴሌቭዥን ድራማ አባላት እስራትና ድብደባ ደረሰባቸው

  በህዝብ ዘንድ ተወዳጅ የሆነው ዘመን የቴሌቭዥን ድራማ አባላት ለቀረፃ ስራ በተሰማሩበት በሶማሌ ክልል ሽንሌ ዞን በክልሉ ፖሊስ ድብደባና እስራት ተፈፅሞብናል ሲሉ ተናገሩ።

  የድራማውን የስደት ታሪክ የሚቀርፁት የካሜራ ባለሙያዎችንና ተዋንያንን ጨምሮ በቦታው የነበሩት የቡድኑ አባላት ዓርብ ዕለት ሰኔ 30 አመሻሹን በአራት ፒክ አፕ የተጫኑ 30 ያህል የፖሊስ አባላት ከበው እንደደበደቧቸውና በማያውቁት ቋንቋ ስድብና ማዋከብ እንደደረሱባቸው ተናግረዋል።

  “መሳሪያ ተደግኖብን በከፍተኛ ጩኸት በሶማሊኛ ስንዋከብ ምን መመለስ እንዳለብን ግራ ገብቶን ነበር። በአማርኛ ለማስረዳት ስንሞክር እነሱ ለመስማት ፈቀደኛ አልነበሩም” ትላለች ከቡድኑ አባላት አንዷ።

   

  “በወታደር ጫማ ከጉልበቴ ስር ተመታሁ ሌሎችም ወታደሮቹ በያዙት ዱላ ባገኙት ነገር ወንድ ሴት ሳይሉ እየተማቱ በከፍተኛ እንግልት ፒካፕ መኪናቸው ላይ ወረወሩን ……..ወታደሮቹ ፒካፕ መኪና ላይ ከጫኑን በኃላ 12  ኪሜ እርቀትን በ160 የመኪና ፍጥነት በፒስታ መንገድ ላይ እየከነፉ ወደ አንድ ግቢ አስገቡን። ግቢ ውስጥ እንደገባን ከመኪናው ላይ እየጉተቱ ከወረዱን በኃላ የያዘነው እቃ ፊት ለፊት እንድናስቀምጥ ካደረጉን በኃላ በየተራ እያስቆሞ እያመናጨቁ ፈተሹን ወንዶች ለብቻ ሴቶች ለብቻ ካደረጉን በኃላ የመጡት ወታደሮች ሁሉ ከ10 ጊዜ በላይ ቆጠሩን። ይሄ ሁሉ ሲሆን እንድናወራ አልፈቀዱልንም እራሳቸው ይጠይቃሉ እራሳቸው ይመልሳሉ ደግሞ ይጮሀሉ” ብሏል የቡድኑ አባል ታሪኩ ደሳለኝ በፌስ ቡክ ገፁ።

  የሶማሌ ክልል የፀጥታ ባለስልጣናት በስልክ ስለቡድኑ ከሌላ አካል ካረጋገጡ በኋላ እንደለቀቋቸው አባላቱ ተናግረዋል።

  “ከድሬዳዋ አስተዳደር የተፃፈ ደብዳቤና ሌሎች መረጃዎችን ለማሳየት እንኳን ጊዜ አልስጡንም፣ እኔ ፀሎቴ የያዙትን መሳሪያ እንዳይተኩሱብን ነበር” ከአባላቱ ሌላዋ።

  የሶማሌ ክልል ፕሬዝዳንት ቢሮ ተፈጠረ የተባለው ችግር ተራና ለሚዲያ የሚበቃ እንዳልሆነ ለዚህም ምላሽ መስጠት እንደማይፈልግ በቃል አቀባዩ በኩል ለዋዜማ ገልጿል።

  “ማንም ቢሆን ተደብቆ ፀረ ሰላም እንቅስቃሴ ለማድረግ ወደ ክልላችን ቢገባ ከዚህ የባሰ ችግር እንደሚገጥመውና ያለ ፌደራል መንግስት ወይም የክልሉ ፕሬዝዳንት ሳያውቁ ሚዲያ ወደ ክልሉ መግባት አይችልም” ብለዋል በማሳረጊያቸው።

  ዘመን ድራማ ያላፉትን ወራት በቴሌቭዥን በመቅረብ ላይ ያለ አበበ ባልቻ ፣ስዩም ተፈራ ፣ሰለሞን ቦጋለና ዘውዱ አበጋዝን ጨምሮ በርካታ አዳዲስ ተዋንያንን ያካተተ ተከታታይ ድራማ ነው።

   

  Read more
 • አስደናቂ እውነታዎች - Amazing Facts

                                                     

  • አይጥና ፈረስ አያስመልሳቸውም
  • የሲጋራ መለኮሻ (ላይተር) ከክብሪት ቀድሞ ነው የተፈጠረው
  • አዞ ምላሱን ማውጣትም ሆነ ምግብ ማኘክ አይችልም
  • በሰውነታችን ውስጥ ካሉት አተሞች ውስጥ 98 በመቶዎቹ በየአመቱ ራሳቸውን ይተካሉ
  • ድምፅ ከአየር ይልቅ በብረት ውስጥ በ15 እጥፍ ይጓዛል
  • ጎሪላዎች በቀን ለ14 ሰዓታት ይተኛሉ
  • የአንድ ሰው ልብ በቀን 100ሺህ ጊዜ ይመታል
  • ወሲብን ለመደሰቻ የሚጠቀሙበት የሰው ልጅና ዶልፊን ብቻ ናቸው
  • የእጅ ጥፍራችን ከእግር ጥፍራችን በአራት እጥፍ ያድጋል
  • ልክ እንደ እጅ አሻራ ሁሉ የእያንዳንዳችን የምላስ አሻራ የተለያየ ነው ልክ እንደ እጅ አሻራ ሁሉ የእያንዳንዳችን የምላስ አሻራ የተለያየ ነው
  Read more
 • "ጆሮና ቀንድ" - ከዳንኤል ክብረት

                                                                     

  አንድ ጥጃ የሚያሳድግ ሰው ነበር::ጥጃውን ሲፈልግ ጆሮውን ይጎትተዋል፣ሲፈልግ በዱላ ይዠልጠዋል፣ሲፈልግ ጨው እያላሰ ይስበዋል፣ ሲፈልግ ደግሞ በገመድ አሥሮ ያስከትለዋል፡፡ በዚህ መንገድ ሄዶጥጃው አደገና  ወይፈን ሆኖ ቀንድ አበቀለ የጥጃውም ባለቤት እንደለመደው በዱላ ሊመታው፣ ጆሮውንሊጎትተው፣ በዱላም ሊዠልጠው ተነሣ::ያን ጊዜ ጥጃው አፍንጫውን ወደ መሬት አስነክቶ አኩረፈረፈናእንደ ስፔን በሬ ተወርውሮ በቀንዱ ወጋው፡፡ ሰውየውም ወገቡን ይዞ እየተጎተተ ቤቱ ደረሰ፡፡

  ታሞ ሊጠይቁት የሄዱ ጎረቤቱ የሆነው ነገር ሰሙና ‹ወዳጄ የጆሮና የቀንድን ዘመን እንዴት መለየትአቃተህ?› አሉት፡፡ ‹የጆሮና የቀንድ ዘመን ምንድን ነው?› አላቸው ወገቡን አሥሮ እየተገላበጠ፡፡‹በመጀመሪያ የበቀለን ጆሮ በኋላ የመጣ ቀንድ በለጠው› ሲባል አልሰማህም፡፡ ጥጃው መጀመሪያ ጆሮ ብቻስለነበረው ያልከውን ሁሉ ይሰማህ፣ ይታዘዝህ ነበር፤ ብትመታው ይችላል፣ ብትጎትተው ይከተላል፣ብታሥረው ይታሠራል፡፡ ጆሮ ብቻ ስለነበረው መስማት ብቻ ነበር የሚችለው፡፡ በኋላ ግን ቀንድ አበቀለ፡፡ቀንድ ካበቀለ በኋላ እንደ ድሮው እጎትተዋለሁ ብትል አይሆንም፡፡ አሁን ከተስማማው ይቀበልሃል፤ካልተስማማው ግን መዋጋት ይጀምራል፡፡ አሁን አንተ ያደረግከውን ማድረግ የሚቻለው በጆሮ ዘመንነው፡፡ በቀንድ ዘመን እንደዚህ ማድረግ ሞኝነት ነው፡፡

  ሁሉም ነገር የጆሮና የቀንድ ዘመን አለው፡፡ በሀገራችን አንድ መንግሥት ሲተከል ሕዝቡ የጆሮ ዘመንይሰጠዋል፡፡ ዝም ይላል፣ ይሰማል፣ ይቀበላል፤ አልጋው እንዲረጋ፣ ዙፋኑ እንደዲጸና ይተጋል፤ ከትናንትዛሬ፣ ከዛሬም ነገ ይሻላል ብሎ በተስፋ ይጠብቃል፡፡ ባያምንም ይቀበላል፤ ባይስማማም ይተባበራል፤ባይግባባም አብሮ ይሠራል፡፡ ይሄ የጆሮ ዘመን ነው፡፡ ብልህ መሪ ከጆሮ ዘመን በኋላ የቀንድ ዘመንእንደሚመጣ ያውቃል፡፡ ስለዚህም ሥርዓት ሠርቶ፣ ሕግ አጽንቶ፣ አገር አልምቶ፣ ሕዝብን አስማምቶይጠብቃል፡፡ በጆሮ ዘመን ያልሠራውን ሥራ በቀንድ ዘመን እሠራለሁ ቢል የሚያምነው የለም፡፡ እንደቀድሞው ዝም ብሎ የሚሰማ፣ አሜን ብሎ የሚቀበል፣ እሺ ብሎ የሚከተል፣ ጎንበስ ብሎ የሚጎተትአይገኝም፡፡ ለተስማማው ጆሮውን ላልተስማማው ቀንዱን ያቀርባል፡፡ ሥራውን በግድ ብተትሠራ እንኳንትግሉ ብዙ ነው፡፡ ሕዝብ ቀንድ ከማብቀሉ በፊት እንደ ቀንዱ ዘመን ማድረግ እንደማይቻለው ሁሉ፣ ቀንድካበቀለ በኋላም እንደ ጆሮው ዘመን ማድረግ አይቻልም፡፡ ራሱ ቀንድ አብቃዩም እንደ ድሮው ልሁን ቢልእሺ አይለውም፡፡ ያላወቁትን እንዳላወቁ፤ ያልሰሙትን እንዳልሰሙ፣ ያላዩትን እንዳላ፣ ያልደረሱበትን እንዳልደረሱ መሆን አይቻልም፡፡ ለውጥን ፈልገህው ብቻ አታመጣውም የቀንድ ዘመን ሲሆን ሳትፈልግም ትለወጣለህ፡፡  

  አገር ብቻ ሳይሆን ድርጅት፣ ማኅበር፣ ፓርቲና ተቋምም ቀንድ ያበቅላሉ፡፡ በጆሮ ዘመን አባሉ ሁሉይሰማሃል፤ ትእዛዝ ከበላይ እግር ወደላይ ብሎ ያምናል፡፡ አንድ ቦታ የበሰለውን በልቶ፣ አንድ ቦታየተጠመቀውን ጠጥቶ፣ የተባለውን ሁሉ ሰምቶ፣ ውደድ የተባለውን ወድዶ ጥላ የተባለውን ጠልቶይኖራል፡፡ በአንድ ዓላማ የተመመ፤ በአንድ አቋም የቆመ፤ አንድ ግብ የጨበጠ፤ በአንድ መመሥመርየሠለጠ የሚመስልበት የጆሮ ዘመን አለው፡፡ እንደ አህያ ጆሮ እንደ ጦር ጉሮሮ አንድ ሆኖ ተካክሎየሚታይበት፡፡                              እንደ አንድ ልብ መካሪ እንደ አንድ ቃል ተናጋሪ የሚመስልበት ዘመን አለ፤ያኔ አባሉናአካሉ የተግባባና የተስማማ የመሰለው ተግባብቶና ተስማምቶ ብቻ አይደም፡፡ ጊዜው የጆሮ ጊዜ ስለሆነነው እንጂ፡፡

  የቀንዱ ዘመን ሲመጣ ጠያቂ፣ መርማሪ፣ ተከራካሪ፣ ሞጋች ተች፣ ይበዛል፡፡ በፊት የጣመው አሁንይመረዋል፤ በፊት ያስደሰተው አሁን ያስከፋዋል፤ በፊት ዝም ያለው አሁን ያስጮኸዋል፣ በፊት የታገሠውንአሁን ይሰለቸዋል፡፡ በፊት የፈራውን አሁን ይደፍረዋል፡፡ በፊት የተወውን አሁን ያነሣዋል፡፡ ‹ቀኝ ኋላ ዙር›ስለተባለ ብቻ አይዞርም፡፡፡ አባል ስለሆነ ብቻ የድርጅቱን ነገር ሁሉ አይቀበልም፡፡ መለኮታውያን ናቸውያላቸውን መሪዎቹን ሰው አድርጎ መመልከት ይጀምራል፡፡ ላመነው ነገር እንኳ ቢሆን ተጨማሪ ማስረጃይፈልጋል፡፡ የጥንቱን ትርክት ብትተርክ፣ የጥንቱን ዘፈን ብትዘፍን፣ የጥንቱን ፉከራ ብትፎክር እንደ ሞኝ ይቆጥርሃል፡:፡ ያ ሁሉ የጆሮ ዘመን ታሪክ ነውና፡፡ በዚህ ጊዜ ለምን እንደ ጥንቱ ጆሮውን ስንጎትተውአልተጎተልንም፣ ስንመታው ለምን አልሄደም፣ ስንስበው ለምን አልተሳበም፤ ስንቆነጥጠው ለምንአልተቆነጠጠም ብለው የሚያስቡ ዘመንን ማንበብ የማይችሉ ናቸው፡፡ አሁን የቀንድ ዘመን ነው፡፡ የጆሮጊዜ አልፏል፤ ማሳመን ማግባባት፣ ማስረዳት፣ ይፈልጋል፡፡ መስማት ብቻ ሳይሆን መሰማትም ይሻል፡፡

  እርጅና በየዘመኑ ነው፡፡ ልጅነት በዘመኑ ያረጃል፤  ወጣትነትም በጊዜው ይጠወልጋል፤ ድርጅትና ማኅበር፤ ተቋምና ፓርቲ በዘመናቸው ያረጃሉ፡፡ ብልህ እንደ ንሥር ያድሳቸዋል፡፡ እንደ እባብ ቆዳ ለዘመኑ የሚመጥን ልብስ ያለብሳቸዋል፡፡ በጆሮ ዘመን የሠሩበትን በቀንድ ዘመን እንሠራበት አይሉም፡፡ እባብ ያድግና ቆዳው አላላውስ ሲለው ቆዳውን ገሽልጦ ጥሎ ለዕድገቱ የሚስማማ ቆዳ ይለብሳል፡፡ ድርጅትና ፓርቲም እንዲህ ካልሆኑ እርጅናው ሞትን ያመጣል፡፡ የጆሮ ዘመን ሲያረጅ ለቀንዱ ዘመን ተዘጋጅ፡፡

  ቤተ እምነቶች በዘመናችን ያልተረዱት ቁም ነገር ይሄ ነው፡፡ አንተ ምእመን ነህ ዝም ብለህ ገንዘብህን ስጥ፣ የምንልህን ብቻ ተቀበል፣ ለምን? የት? መቼ? እንዴት? ብለህ አትጠይቅ፤ አባቶችህ ከአንተ በላይ ያውቃሉ፤ አገልጋዮቹ ከአንተ ይሻላሉ፤ አትከራከር፣ ቁጣ፣ መቅሰፍት፣ መዓት ይወርድብሃል፣ ስለተባለ ብቻ የሚቀበልበት የጆሮ ዘመን አልፏል፡፡ መስጠት ብቻ ሳይሆን የሰጠው ገንዘብ የት እንደዋለ ማወቅም ይፈልጋል፤ አባቶቹን ማክበር ብቻ ሳይሆን ክብራቸውን ሲጠብቁ ማየትም ይፈልጋል፤ የሚባለውን መስማት ብቻ ሳይሆን ለሚባለው ነገር ማስረጃም ይሻል፤ ይመዝናል፤ ያመዛዝናል፤ የጥንቱን ከዛሬው፣ ድርጊቱን ከሕጉ ያመሳክራል፤ በሕጋዊው ቤት ሕገ ወጥነት፣ በመንፈሳዊው ቤት ዓለማዊነት፣ በእግዚአብሔር ቤት ቄሣር፣ በጽድቁ ቤት ርኩሰት ሲሠለጥን እያየ ዝም የሚልበት የጆሮ ዘመን አልፏል፤ አሁን የቀንድ ጊዜ ነው፡፡

  ተገለጠልኝ፣ ታየኝ፣ በራልኝ፣ ወረደልኝ፣ ፈለቀልኝ፣ ሰማይ ደርሼ መጣሁ፤ አሥር ሺ ሰይጣን አወጣሁ ስላልክ ብቻ የሚቀበልበት የጆሮ ዘመን አልፏል፡፡ ይመዝነዋል፣ ይፈትነዋል፤ ያነጥረዋል፣ ያበጥረዋል፡፡ ‹ኩሎ አመክሩ ወዘሠናየ ግበሩ› ነውና የተባለው፡፡ ከቻለ ይሞግትሃል፤ ካልቻለ ትቶህ ይሄዳል፡፡ ዝም ብለህ ተቀበል የሚባልበት የጆሮ ዘመን አሁን የለም፡፡ እንደ ጆሮው ዘመን ወደፈለግከው አዳራሽና ጸሎት ቤት፣ ወደፈለግከው የራእይና የተአምራት ቦታ አትጎትተውም፡፡ አሁን አልሄድም ብሎ ሊወጋህም ይችላል፡፡ በዚህ ዘመን በየቤተ እምነቱ በምእመናኑና በእምነት አለቆች መካከል የምናየው ውጊያ ይሄ ነው፡፡ ወደፈለግነው አቅጣጫ እንጎትታለን በሚሉ የጆሮ ዘመን አለቆችና ‹ቀንዴ ከፍ ከፍ አለ› በሚሉ ቀንድ ባበቀሉ ምእመናን መካከል፡፡

  ድርጅትህን ስትመሠርተው ልጅ ስለነበር እንደፈለግክ ታደርገው ይሆናል፡፡ እየሰፋ፣ እያደገ፣ እየተለጠጠ፣ እየታወቀና እየሠለጠነ ሲሄድ ግን ከጆሮው ዘመን አልፎ የቀንዱ ዘመን ላይ ይደርሳል፡፡አንተ ድርጅቱን መምራት ብቻ ሳይሆን ድርጅቱም አንተን ሊወጋህም ይችላል፡፡ ብዙዎች በገዛ ድርጅታቸው ቀንድ ተወግተው ታሥረዋል፣ ከሥረዋል፣ ጠፍተዋል፣ በሽተኞች ሆነዋል፡፡ ጭንቀት ውስጥ ገብተዋል፤ ሙስና ውስጥ ተዘፍቀዋል፡፡ ብልህ ነጋዴ በጆሮው ዘመን ቀድሞ ያስባል፡፡ እንደ ጥንቱ እመራዋለሁ፣ አስተዳድረዋለሁ፣ እኔ እበቃዋለሁ፣ ለዚህ ደግሞ መቼ አንሳለሁ አይልም፡፡ የልጅነቱን ልብስ አሁን ልልበስ እንደማይለው ሁሉ የጥንቱን አሠራር አሁን ልከተል አይልም፡፡ ለቀንዱ ዘመን የሚመጥን አሠራር፣ ሥርዓት፣ አስተዳደር፣ ባለሞያ፣ ሕግ፣ አደረጃጀት፣ የደረጃ ምጣኔና አስተሳሰብን ይገነባል እንጂ፡፡

  በሀገራችን ዘመን ተሻግሮ ከልጅ ልጅ የሚተርፍ ድርጅት ያጣነው፣ ባለቤቶቹ ድርጅቱን በጆሮው ዘመን አስተሳሰብ በቀንዱ ዘመን እንምራው ስለሚሉ ነው፡፡፡ ድርጅቱ አድጎ አድጎ ከዐቅማቸው በበላይ ይሆንና ያሳደገው አውሬ እንደሚበላው አዳኝ ያሳደጉት ድርጅት እነርሱንም ይበላቸዋል፡፡ ስንት ዘመን መርቼው፣ ድንጋይ ጥዬ መሥርቼው፣ ላቤን ጠብ አድርጌ እዚህ አድርሼው ማለቱ አይጠቅምም፡፡ ያ የጆሮ ዘመን ነውና፡፡

  ምንጭ:- የዳንኤል ክብረት እይታዎች

  Read more