PLANET ETHIOPIA.com

Ethiopian History የኢትዮጵያ ታሪክ


 • ፍቅርና ጋብቻ በቀይ ሽብር ዘመን - Love and Marriage During Red Terror

                                                                   

  ቅር ተስፋ በሌለባቸው ቦታዎችም ያብባል

  ለአይናለምና ለገነትም ይህ ነበር የሆነው። እ.አ.አ በ1978 በኢትዯጵያ ታሪክ ከባድ የቀይ ሽበር ወቅት ተጋቡ።

  የደም መፋሰሱ ከጋብቻቸው ከዓመት በፊተ የጀመረ ሲሆን፤ እሱም መንግሥቱ ኃይለማሪያም ሥልጣን ይዞ ጠላቶቹን ለማጥፋት ቆርጦ የተነሳበት ጊዜ ነበር። .

  ሥልጣን በተቆጣጠረበትም ጊዜ በሺህ የሚቆጠሩ ሰዎች ሞቱ ደግሞም በሺህ የሚቆጠሩ ለመፈናቀል ተገደው ነበር።

  ይህ ግን አይናለምንና ገነትን ከአዲስ አበባ ወጣ ብላ በምትገኘው በሰንዳፋ የጋብቻ ቃላቸውን ከመቀያየር አላገዳቸውም ነበር።

  ለዚህ ታስበው የተወሰዱት ፎቶግራፎች ከ Vintage Addis Ababa ሲሆን በልዩ ሁኔታዎች ላይ ሰዎች እንዴት እንደሚኖሩ ማሳያ እንዲሆን ታስቦ በቤተ-መዛግብት የተቀመጡ ነበሩ።

  ረዥሙ የመጠናናት ጊዜ

  እ.አ.አ በ1973 ነበር፤ ወጣቶቹ የተዋወቁት በአንድ ሰፈር ይኖሩ ስለነበር ነው።

  በዓመቱ ደርግ መንግሥት ወደ ሥልጣን ሲመጣ ለመንግሥቱ ኃይለማሪያም የሥልጣን ጥርጊያ መንገድ አመቻቸ።

                                                                                  

  አጭር የምስል መግለጫእ.አ.አ በ2008 በሌለበት መነግሥቱ ኃይለማሪያም ሞት ተፈርዶበታል። እሱ በዚምባብዌ ነው የሚኖረው።

  ይህን ተከትሎ የተከሰተው ግርግር ሳያስቡት ሕይወታቸውን አንጠልጥሎ አስቀረው።

  አይናለም ገነትን የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት እንደጨረሰች ለማግባት አቅዶ ነበር።

  ሆኖም ግን እ.አ.አ በ1978 የተቃውሞ ሰልፍ ላይ ተይዛ ለሦስት ወራት ታሰረች።

  "በደርግ ስር መኖር ቀላል አልነበረም" ትላለች ገነት። በመቀጠልም "ያለው ፍራቻ ሙሉ ሰው ከመሆን ያደናቅፈን ነበር" ብላለች።

  የደርግ ሥርዓት የታሰረን ሰው ቤተሰብ እንዲጠይቅ ባይፈቅድም፤ አይናለም ግን በየተወሰነ ቀናት ገነትን ያያት ነበር።

  የአብዮቱ ጠባቂ ስለነበር ሌሎች ተቃዋሚዎች ስለግንኙነታቸው ቢያውቁ ለሕይወቷ ያሰጋ ስለበር በጣም ይጠነቀቅ ነበር።

  "ሰላም መባባልም ሆነ መነጋገር አንችልም ነበር። ጥበቃዎቹ እንደምንተዋወቅ ሊያውቁብን ይችሉ ነበር። ሆኖም ግን ግቢው ውስጥ ባየሁት ቁጥር ደስ ይለኝ ነበር" ትላለች።

  ገነት ታስራ የነበረ ቢሆንም የጋብቻቸው ፎቶግራፎች ግን የጉስቁልና አንዳች ምልክት የላቸውም።

  ጉልበት ተሳመ

  የሠርጋቸውን ዕለት በኢትዮጵያ ባህል መሠረት ጀመሩት።

  አይናለም ገነትን ከቤተሰቦቿ ቤት ወደ እራሱ ቤት ለመውሰድ ከመሄዱ በፊት የእናቱን ጉልበት ስሞ ነበር ከቤቱ የወጣው።

                                                                              

  በቤቱ ደጃፍ ላይም ጎረቤትና ጓደኞቹ ሊሸኙት ተሰብስበው ነበር።

         

  ጥቁር ሱፍ አንገትን በሚሸፍን ነጭ ሹራብ የለበሰው አይናለም ገነትን ለማምጣት ወደ ተዘጋጀችው ቼቭሮሌት አቀና ።

                                                                                 

  ቀለበቶቻቸውን ፒያሳ ከሚገኘው አፍሪካ ወርቅ ቤት የገዙት ሙሽሮች ከሰዓት በኋላ በገነት አባት ቤት ቄስ ፊት ቃል ገቡ።

  ከተጋበዙት 300 ሰዎችም ራቅ ብለው ሙሽሮቹ ፎቶግራፍም ለመነሳት ችለው ነበር።

                                                                                 

  ለገነት በሚያሳዝን ሁኔታ ግን አይናለም እ.አ.አ በ2008 ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ። እሷ ግን አብረው ያሳለፉትን ጊዜያት በጣም እንደምትወድና እንደምትናፍቅ ትናገራለች።

  "ያፈቀርኩትን ሰው ነበር ያገባሁት፣ ያሳደግሁትም ከልቤ የምወዳቸውን ልጆች ነው" ትላለች።

  የፎቶግራፎቹ መብት ሙሉ በሙሉ የVintage Addis Ababa ነው።

  ምንጭ፦ ቢቢሲ

  Read more »

 • ስንቶቻችን የኮሞሮሱን የአውሮፕላን አደጋ እናስታውሳለን? - Remembering Ethiopian Airlines Crash In The Comoros Island

                                             

  በደቡብ ምስራቅ አፍሪካ የምትገኘው የኮሞሮስ ደሴት ተመራጭ የጎብኚዎች መዳረሻ ስፍራ ነች።

  በህንድ ውቅያኖስ ዳርቻ ሲዝናኑ የነበሩ ጎብኚዎች እና የአካባቢው ነዋሪዎች ህዳር 14/1989 ዓ.ም ግን ያልተጠበቀ ነገር ተመለከቱ።

  ይህንን አሳዛኝ አጋጣሚም በካሜራቸው ቀርጸው ማቆየት የቻሉም ነበሩ።

  የኢትዮጵያ አየር መንገድ የበረራ ቁጥር ET961 ከአዲስ አበባ ወደ ናይሮቢ 175 መንገደኞችን አሳፍሮ በመጓዝ ላይ ሳለ ሶስት ኢትዮጵያን ወደ አውሮፕላኑን መቆጣጠሪያ ክፍል(cockpit) በኃይል በመግባት አብራሪዎቹ የበረራ አቅጣጫቸውን ወደ አውስትራሊያ እንዲያደርጉ አስገደዱ።

  አቅጣጫውን እንዲቀይር የተደረገው አውሮፕላን ለአራት ሰዓታት በአየር ላይ ከቆየ በኋላ ነዳጅ ጨርሶ በኮሞሮስ ደሴት ላይ ተከሰከሰ።

  ግዙፉ ቦይንግ 767 በሰዓት 324 ኪሎ ሜትር ፍጥነት በመብረር ላይ እያለ ነበር አካሉ ከውሃው ጋር የተጋጨው። ይህም የአውሮፕላኑ አካል ተሰባብሮ በርካቶች ህይወታቸውን እንዲያጡ ምክንያት ሆኗል።

  ዋና አብራሪው ካፒቴን ልዑል አባተ እና ምክትል አብራሪ የነበሩት ካፕቴን ዮናስ መኩሪያ ሊደርስ የነበረውን ከፍተኛ የሰው ህይወት መጥፋት ባደረጉት ጥረት በማዳናቸው ከበርካቶች ሙገሳ ቀርቦላቸዋል።

  የበረራ ሰራተኞችን ጨምሮ 125 ሰዎች ህይወታቸውን ያጡ ሲሆን 50 የሚሆኑት ደግሞ ቀላል እና ከባድ የአካል ጉዳት አስተናግደው በህይወት ተርፈዋል።

                                                      

  በህይወት ከተረፉት መካከል አቶ አስመላሽ ስብሃቱ ይገኙበታል።

  ዛሬ ላይ አቶ አስመላሽ የ83 ዓመት የዕድሜ ባለጸጋ ቢሆኑም የዛሬዋን ቀን 21ኛ ዓመት የልደት በዓላቸው አድርገው ነው የሚያከብሩት።

  የአቶ አስመላሽ ልጅ ወ/ሮ ኤደን አስመላሽ ''አባታችን ከአደጋው በመትረፉ እንደገና እንደተወለደ አድርገን ነው የምናስበው'' ትላለች።

  ''በህይወት በመትረፉ ለእኛ ከፍተኛ ደስታ የነበር ቢሆም እሱ ግን የተደበላለቀ ስሜት ነው የተሰማው። ቀኑን ሲያስብ በአደጋው ህይወታቸውን ያጡትን ያስባል። በሌላ በኩል ደግሞ በህይወት መትረፉ ያስደስተዋል'' ስትል ታስረዳለች።

  ''በአደጋው ህይወታቸውን ያጡት ህጻናት በህይወት ቢኖሩ ይሄኔ ትምህርታቸውን ያጠናቅቁ ነበር'' እያለ ያብሰለስላል ትላለች ኤደን ስለ አባቷ ስትናገር።

  አቶ አስመላሽ በአውሮፕላኑ ክፍት ቦታ ባለመኖሩ መጓዝ እንደማይችሉ ተነግሯቸው ነበር። ሆኖም የአየር መንገዱ የረዥም ጊዜ ደንበኛ ስለሆኑ ወንበር ተፈልጎ እንደተገኘላቸው ትናገራለች። አቶ አስመላሽ ጉዞ ከመጀመራቸው በፊትም የረዥም ጊዜ ጓደኛቸውን በአውሮፕላኑ ውስጥ አግኝተው ቦታ በመቀየር ጓደኛቸው ጋር እንደተቀመጡ ትናገራለች።

  የዕድል ነገር ሆኖ የአቶ አስመላሽ ጓደኛ በህይወት መትረፍ አልቻሉም።

  በሶስት ኢትዮጵያውያን የተጠለፈው አውሮፕላን ከአዲሰ አበባ የተነሳው ናይሮቢ የሚያደርሰውን ነዳጅ ብቻ ሞልቶ ነበር። ይሁን እንጂ ጠላፊዎቹ ወደ አውስትራሊያ እንዲበር በማስገደዳቸው ነዳጁ እስኪያልቅ በአየር ላይ ለአራት ሰዓታት ቆይቷል።

  አብራሪውና ረዳት አብራሪው ግን ጠላፊዎቹን "በቂ ነዳጅ የለንም ስለዚህ በአቅራቢያችን ባለ ቦታ አርፈን ነዳጅ መቅዳት አለብን" ቢሏቸውም ጠላፊዎቹ ግን አሻፈረኝ አሉ።

  ከዚያም የአውሮፕላኖቹ ሁለቱም ሞተሮች አገልግሎት መስጠት አቆሙ።

  አውሮፕላኑም ከፍታውን በከፍተኛ ፍጥነት በመቀነስ ወደታች መንደርደር ጀመረ።

  በመጨረሻም በኮሞሮስ ደሴት አካባቢ ህንድ ውቅያኖስ ላይ ከውሃ ጋር ተላተመ፤ የአውሮፕላኑ ክፍሎችም በግፊቱ ብዙ ቦታ ተበታተኑ።

  በአቅራቢያው የነበሩት የደሴቱ ነዋሪዎችና ጎብኚዎችም በፍጥነት ወደ አደጋው ቦታ በመሄድ የተረፉትንና የሞቱትን ሰዎች አስክሬን ከውሃ ውስጥ ማውጣት ችለዋል።

  ዋና አብራሪው ካፒቴን ልዑል አባተ የጠላፊዎቹን ከፍተኛ የአካልና የአዕምሮ ጥቃት ተቋቁመው ውሃ ላይ ማሳረፍ በመቻላቸው በብዙ መገናኛ ብዙሃንና ከአደጋው በተረፉ ተጓዦች "ጀግና" በማለት ተወድሰዋል።

  ዛሬ በናይሮቢ ኬንያ የሚኖሩት አቶ አስመላሽና ቤተሰባቸውም የሁለተኛውን የትውልድ ቀናቸውን 21ኛ ዓመት እያከበሩ ነው።

  ስለአደጋው ማወቅ ያባችሁ ነገሮች

  • የአውሮፕላኑ ሞዴል ቦይንግ 767-260ER ሲሆን በአውሮፓውያኑ 1987 የኢትዮጵያ አየር መንገድ ንብረት ሆኗል
  • አብራሪዎቹ ዋና ካፒቴን ልዑል አባተና ረዳት አብራሪው ዮናስ መኩሪያ ነበሩ
  • አውሮፕላኑ 175 ተጓዦችንና የበረራ ቡድን አባላትን በመያዝ ወደ ናይሮቢ ለመጓዝ ነበር ከአዲሰ አበባ የተነሳው
  • አውሮፕላኑ ናይሮቢ የሚያደርሰውን ነዳጅ ብቻ ነበር ሞልቶ የተነሳው
  • በጉዞው መሃል 3 ሰዎች አውሮፕላኑን በመጥለፍ "አውስትራሊያ አድርሱን ካልሆነ ይህን ቦምብ እናፈነዳዋለን" አሏቸው
  • ወደ መጀመሪያ መዳረሻው ናይሮቢ የሁለት ሰዓት ተኩል ጉዞ ለማድረግ የተነሳው አውሮፕላን ከአራት ሰዓት በላይ አየር ላይ በመቆየቱ ነዳጁን ጨረሰ
  • በመጨረሻም በህንድ ውቅያኖስ በኮሞሮስ ደሴት ውሃ ላይ ተከሰከሰ
  • በአደጋው 125 ሰዎች ሲሞቱ ሁለቱን አብራሪዎችን ጨምሮ 50 ሰዎች ተርፈዋል

  ሶስቱ ኢትዮጵያውያን ጠላፊዎችም ከሞቱት መካከል ናቸው።

  ምንጭ: ቢቢሲ

  Read more »

 • ታሪክን የኋሊት - የኮንኮርድ አውሮፕላን ነገር::

                                              

  (የኔነህ ከበደ)

  ኮንኮርድ የተሠኘው ከድምፅ የፈጠነ ሱፐር ሶኒክ የመንገደኞች አውሮፕላን በ27 ዓመት የአገልግሎት ዘመኑ አንዳችም የደህንነት እንከን አልታየበትም ነበር፡፡

  የዛሬ 17 ዓመት የዛሬዋ እለት ለኮንኮርድ መራራ እለት ሆነች፡፡

  በእለቱ ኤር ፍራንስ ኮንኮርድ አውሮፕላን የበረራ ቁጥር 4590 ከፓሪስ በኢኳደር በኩል ወደ ኒውዮርክ ለመብረረር አኮብኩቦ ተነሳ፡፡

  አየር ላይ ብዙም አልቆየ፡፡

  የሚትጐለጐል የእሳት ኳስ መትፋት ጀመረ፡፡

  ከአንድ ሆቴል አቅራቢያም ተከሰከሰ፡፡

  በውጤቱም ከ100 መንገደኞችና ከዘጠኙ የአውሮፕላኑ ሠራተኞች ለወሬ ነጋሪ የተረፈ አልነበረም፡፡ በአደጋው በመሬት ላይ የነበሩ ሌሎች አራት ሰዎችም ሞቱ፡፡

  ኮንኮርድ የብሪታንያና የፈረንሳይ ትብብር የታየበት፤ የሁለቱ ሀገሮች የአውሮፕላን እነፃ ኢንጂነሮች የተጠበቡበት በዘመኑ ዘመን አፈራሽ ተብሎ የተደነቀ የተጨበጨበለት ነበር፡፡

  ይህ ከድምፅ የፈጠነ ከተፎ አውሮፕላን ኢኮኖሚያዊ አዋጭነትና አትራፊነቱ ተመሠከረለት፡፡ 
  በመንገደኞች አውሮፕላን ታሪክ በፍጥነቱ አቻም፤ ወደርም አጣ፡፡

  ከፈጣንነቱ የተነሳ የአትላንቲክ ውቅያኖስ ማዶ ለማዶውን በረራ ከየትኛውም ሌላ ስሪት አውሮፕላን ባነሰ ጊዜ ማቋረጥ መቻሉ ትርፋማነቱን አሳደገው፡፡

  ኤር ፍራንስንም ሆነ ብሪቲሽ ኤርዌይስን አኮራቸው፡፡ ካዝናቸውም በትርፍ ሞላው፡፡

  በሰዓት ከ2 ሺህ ኪሎ ሜትር በላይ በመክነፍ አትላንቲከ ውቅያኖስን በ3 ሰዓት ተኩል ጊዜ ፉት ብሎ ጉዞው የሚጠይቀውን የጊዜ ርዝመት ጐምዶ ያስቀረ ነበር፡፡

  ይሄ ዝና፤ ይሄ አድናቆት ሳይደበዝዝ የዛሬ 17 ዓመቱ አደጋ ስጋትን ፈጠረ፡፡ እንደሚባለው ኮንኮርድ ከመነሳቱ ደቂቃዎች በፊት የበረረ ዲ.ሲ 10 አውሮፕላን በማከብከቢያ ሜዳው ቁራጭ የብረት ዘንግ ጥሎ ይነሳል፡፡

  ኮንኮርድ ሲያኮበኩብ ይሄን የብረት ዘንግ መትቶ ይንሸራተታል፡፡ በጐማ የተመታው የብረት ዘንግ የነዳጅ ታንከሩን ይመታል፡፡

  ይሄ አውሮፕላኑ በእሳት እንዲያያዝ ምክንያት መሆኑ ይነገራል፡፡

  ከአደጋው በኋላ የኮንኮርድን ጐማ፣ የነዳጅ መያዣ ታንኮር የኤሌክትሪኩን ሁኔታ ደህንነት ለማሳደግ ለ3 ዓመታት ጥረት ሲደረግ ቆየ፡፡

  ከፓሪሱ አደጋ አንድ ዓመት በኋላ ኮንኮርድ ዳግም ወደ በረራው ተመለሰ፡፡

  ይሁንና ከ14 ዓመታት በፊት ኤር ፍራንስም ሆነ ብሪቲሽ ኤር ዌይስ ኮንኮርድ በቃ፤ ይብቃው አሉ፡፡

  የ27 ዓመታት የአየር ላይ ንጉሱ ኮንኮርድ ጡረታ ወጣ፡፡

  ምንጭ:- የሸገር FM 102.1 ሬዲዮ

  Read more »

 • “ቺርስ”- ለኢትዮጵያና ኤርትራ ህዝቦች ወዳጅነት (አፈንዲ ሙተቂ)

   ወትር ስለኤርትራ በምጽፍበት ጊዜ የሚሰጠኝ አስተያየት (Comment) ከወትሮው ይበዛል፡፡ እነኝህ ኮሜንቶች በዓይነታቸውም ይለያያሉ፡፡ በአድናቆት ከሚያንቆለጳሱኝና የሌለኝን ብቃት እየተረኩልኝ የሰማይ ጥግ ሊያደርሱኝ ከሚሞክሩት ጀምሮ “ህልመኛ ነህ፤ በቁምህ አትቃዥ፣ ኤርትራዊያን ደመኛ ጠላቶቻችን ናቸው” እስከሚሉት ድረስ ዓይነተ-ብዙ ናቸው፡፡ “የሻዕቢያ ስውር አርበኛ፣ የወያኔ ተላላኪ፣ የህዝቡን ትኩረት ከወያኔ ወደ ኤርትራ ለመውሰድ የሚጥር ድብቅ ሸረኛ፣ የታላቋ ኢትዮጵያ ህልም ተንበርካኪ፤ የጋሽ መንግሥቱ ትውልድ አባል” የማይባል ነገር የለም፡፡ በፌስቡክ ቆይታዬ ሁሉንም የለመድኩት በመሆኑ በሆዴ “እሰይ! አበጀሁ” እያልኩ ዝም ብዬ እነጉዳለሁ፡፡

  አሁንም ግን እደግመዋለሁ!! እኔ ህልመኛ ነኝ! ይህ የኔ ህልም በፈጣሪም ሆነ በሰው ልጆች ዘንድ “ብሩክ” ተብሎ የሚወደስ ነው፡፡ ስለህዝቦች ፍቅር፣ ህብረት፣ አንድነትና እኩልነት ማለም የዘወትር ተግባሬ ነው፡፡ መቼም ቢሆን ይህንን ከማቆም ወደ ኋላ አልልም፡፡ እንኳንስ በደንብ የማውቃቸውን የኤርትራና የኢትዮጵያ ህዝቦችን ይቅርና አምስቱ የምስራቅ አፍሪቃ ሀገራት (ሱዳን፣ ኢትዮጵያ፣ ሶማሊያ፣ ጅቡቲና ኤርትራ) በኮሎኒያሊስቶች የተሰመሩ ድንበሮችን በጣጥሰው በአንድ ግዛት ስር እንዲጠቃለሉ በጽኑ አልማለሁ፡፡ ምን ይሄ ብቻ! ትልቋ እማማ አፍሪቃም አንድ ሀገር እንድትሆን በብርቱ ነው የማልመው፡፡
  *****
  ኤርትራና ኢትዮጵያ ሰው ሰራሽ ችግሮች በቆሰቆሷቸው አቧራዎች መነሾነት ሁለት ሀገር ሆነዋል፡፡ ፍቺያችን በደም የታጀበ መሆኑ በጣም ያሳዝነናል፡፡ ያስለቅሰናል፡፡ ይህ ማለት ግን “አንድ ላይ የመሆናችን ጉዳይ ለዘልዓለሙ አብቅቶለታል” ማለት አይደለም፡፡ ሰው ሰራሽ ድንበር በኛ መካከል ቢሰመርም ባህል፣ ታሪክ፣ ቋንቋና ጂኦግራፊ በአንድ ላይ ያስተሳስረናል፡፡ የህዝቦቻችን የጋራ ታሪካዊ ውቅር መቼም ቢሆን አይፋቅም፡፡

  እኛና ኤርትራዊያን በጣም ነው የምንመሳሰለው፡፡ እንዲህ የሚመሳሰሉ ህዝቦች የማታ ማታ ተመልሰው አንድ የሚሆኑበትን ሁኔታ የዓለም ታሪክ አሳይቶናል፡፡ ሁለቱ ጀርመኖች ከአርባ አምስት ዓመታት በኋላ ተዋህደዋል፡፡ ሁለቱ የመኖችም ከሰላሣ ዓመታት በኋላ ሲዋሃዱ አይተናል፡፡ ታዲያ ይህንን እያየን የምን ተስፋ መቁረጥ ነው?

  እኛና ኤርትራዊያን ከመመሳሰልም አልፎ በጣም ነው የምንቀራረበው፡፡ በጣም እንዋደዳለን፡፡ ይህንን በቀላሉ ለመረዳት ኤርትራዊያንና ኢትዮጵያዊያን በዲያስፖራው ክፍለ-ዓለም የሚኖሩበትን ሁኔታ ማስተዋል ይበቃል፡፡ ወደየትኛውም የዓለም ሀገር ሄደን ብናይ ከማንም በላይ ለኤርትራዊያን የሚቀርቡት ኢትዮጵያዊያን ሆነው እናገኛቸዋለን፡፡ ለኢትዮጵያዊያንም ከማንም በላይ የሚቀርቡት ኤርትራዊያን ናቸው፡፡ በህዳር ወር 2005 የሳዑዲ ዐረቢያ የጸጥታ ሀይሎች በኢትዮጵያዊያን ላይ የወሰዱትን በደልና ግፍ የተቀላቀላበትን ከሀገር የማባረር እርምጃ ከኢትዮጵያዊያን ጎን ቆመው ሲያወግዙ የነበሩት ኤርትራዊያን ብቻ ናቸው፡፡ ኢትዮጵያዊያን ባካሄዷቸው ሰልፎች ላይ ከኤርትራዊያን በስተቀር የሌላ ሀገር ዜጋ አልተሳፈተም (“ለምን ከጅቡቲ፣ ከሱዳንና ከሶማሊያ ጋር አንድነትን አትመኙም” ያልሺኝ “ነፂ ጓል ኤርትራ” ሆይ! ለጥያቄሽ መልሱን ከዚሁ ፈልጊው)፡፡

  የሜዲትራኒያን ባህርን በህገ-ወጥ ጀልባዎች በማቆራረጥ ወደ አውሮጳ ሲከንፉ ባህሩ የሚበላቸው ኢትዮጵያዊያንና ኤርትራዊያን ምንዱባንስ እንዴት ይረሳሉ?… ስለነርሱ በምንሰማው መጥፎ ዜና ሁለታችንም አንድ ላይ “እህ!” እያልንና በቁጭት እየተቃጠልን አይደለም እንዴ?… መርዶአቸው በአንድ ላይ እየደረሰን በአንድ ላይ ለቅሶ እየተቀመጥን አይደለም እንዴ?…

  በደጉም ቢሆን መመሳሰላችንና መፈቃቀራችን ብዙ የተጻፈለት፣ ብዙ የተነገረለት ነው፡፡ ዛሬም ድረስ ያንን ሳቂታ የቤኒ አምር ወጣት የኛ ልጅ በመሆኑ ነው የምናውቀው፡፡ ዛሬም ድረስ ከኤርትራዊ ጎረቤቶቻችን ጋር ፋሲካና አረፋን በአንድነት እንታደማለን፡፡
  *****
  እኛ ኤርትራን የምንፈልጋት ለወደቦቿ ስንል አይደለም፡፡ እኛ ኤርትራን የምንፈልገው ሁለመናዋ ከኛ ጋር ስለሚመሳሰልና አንድ ዓይነት ስለሆነ ነው፡፡ እኛ ኤርትራን የምንፈልገው ከነህዝቧ ነው፡፡ የኤርትራ ህዝብ የኛ ህዝብ ነው፡፡ እኛ ራሳችን የኤርትራ ህዝብ ነን፡፡ ኤርትራም ኢትዮጵያ ናት፤ ኢትዮጵያም ኤርትራ ናት፡፡ ኤርትራ ወደብ ባይኖራት እንኳ ይህ አቋማችን አይቀየርም፡፡ ታሪኳ፣ ባህሏ እና ቋንቋዋ እናንተ ከምታውቁት ተቀይሯል እስካልተባለ ድረስ ስለርሷ ማለማችንን አንተውም፡፡

  ህልማችን ጽኑ ነው፡፡ ወደፊት የትግበራ ምዕራፎቹን እያሰፋ የሚሄድ ነው እንጂ በእንጭጩ ተቀጭቶ የሚቀር አይደለም፡፡ ኮሎኔል መንግሥቱ ኃይለማሪያም በአፋቤት ሽንፈት ሲያጋጥማቸው በተስፋ መቁረጥ ስሜት “ቤንዚን አይቆፈርበት፤ አልማዝ አይወጣበት፣ ሰው የለበት! Nothing`” እንዳሉት እኛም ተስፋ ቆርጠን ኤርትራንና ህዝቧን የምናጥላላበት ሁኔታ በፍጹም አይከሰትም፡፡ ቢኢዝኒላህ!!

  እኛ ስለትልቋ ኤርትራ ማለምን ትተን “አሰብ የኢትዮጵያ ወደብ ናት” ከሚሉት የወደብ ጥማተኞች ጎንም አንሰለፍም፡፡ ፍላጎታችን “የኢኮኖሚ እድገት” በሚባለው የማቴሪያሊስቶች ዝባዝንኬ የሚመራ ባለመሆኑ ለጥቅም ብለን ህልማችንን በመንደር ደረጃ አናሳንሰውም፡፡ ቢኢዝኒላህ!!
  የእነዚህን የወደብ ጥማተኞች ቅስም ለመስበር በሚል የፖለቲካ ስሌት ተነሳስተን “የአሰብ ወደብ እጣ ፈንታ የግመሎች ውሃ መጠጫ ኩሬ ከመሆን አያልፍም” የሚል ታሪካዊ ተወቃሽነትን የሚያስከትል ቃልም አይወጣንም፡፡ ቢኢዝኒላህ!!

  እኛ ኤርትራዊያንን እንደኛው አድርገን ነው የምናያቸው እንጂ አንዳንድ ብስጩዎች በሚተነፍሷው ወሬዎች ተናደን “የቅኝ-ተገዥነት ስሜት ሰለባዎች ናችሁ” በማለት አንፈርጃቸውም፡፡ በምንም መልኩ ቢሆን ኤርትራዊ ወገናችንን የሚያሳቅቅና የሚያበሳጭ ክፉ ንግግር አንናገርም፤ ክፋታችንንና የውስጥ ጥላቻችንን የሚያሳብቅ ጽሑፍም አንጽፍም፡፡ በውስጣችን ስለኤርትራ መውደም እያሰብን በምላሳችን ብቻ “አንድ ህዝቦች ነን” እያልን የምንሰብክ መናፍቃንም አይደለንም፡፡ እኛ ኤርትራንና ህዝቧን የምንወደው ከልባችን ነው፡፡ ስለነርሱ የምናልመው ህልማችንም ከልባችን ከተወረወረ የፍቅር ፍላጻ የፈነጠቀ ነው፡፡
  *****
  ህልማችን የቅርብ ሳይሆን የሩቅ ነው! እጅግ በጣም ሩቅ!! ይሁንና ርቀቱን ፈርተን ማለማችንን አንተውም፡፡ ዘወትር ስለውቢቷ ኤርትራና ህዝቧ ማለማችንን እንቀጥላለን!! ከሩቁና መልከ-መልካሙ ህልማችን ጋር ወደፊት!!
  ----
  አፈንዲ ሙተቂ
  ሀምሌ 2009

   

   

  Read more »

 • ድሬ የኚህ ሰው ውለታ አለብሽ!! አቶ መርሻ ናሁ ሰናይ።

  ከጅቡቲ የተነሳው የባቡር ሀዲድ እ.ኤ.አ. በ1902 ዛሬ ድሬዳዋ ካለችበት ቦታ ሲደርስ በአቶ መርሻና በፈረንሳዊው ሌዎን ሸፍነ መሪነት አዲስ ከተማ እንዲቆረቆር ትእዛዝ ተሰጠ።
  የቦታውም ስም መጀመሪያ አዲስ ሐረር ተባለና ትንሽ ቆይቶ ግን ድሬዳዋ የሚል ስያሜ ተሰጠው። በአፋን ኦሮሞ ድሬ ማለት ሜዳ ሲሆን ዳዋ ማለት ደግሞ መድሃኒት እንደማለት ነው።

  በዚያው ዓመት አቶ መርሻ ናሁ ሰናይ የድሬዳዋና አካባቢው የመጀመሪያ አስተዳዳሪ ሆነው ተሾሙ። ብዙም ሳይቆይ በምድር ባቡር ኩባንያው ባልደረቦችና በበርካታ ኢትዮጵያውያን ከፍተኛ ድካም ድሬዳዋ ቶሎ ቶሎ መገንባት ጀመረች። በአጭር ጊዜ ውስጥም ዘመናዊ የሆነ ከተማ ተቋቋመ።

  አቶ መርሻ በከተማውና አካባቢው አስተዳዳሪነት እስከ 1906 እ.ኤ.አ. ድረስ ካገለገሉ በኋላ ለሚቀጥሉት ሃያ ዓመታት ማለትም ጡረታ እስከወጡብት ጊዜ ድረስ የኢሳ ግዛቶች እና የባቡር ሀዲዱ ጥበቃ ሀይል ኃላፊ በመሆን ሰርተዋል። በልጅ ኢያሱ ዘመነ ስልጣን ለአጭር ጊዜ ተሽረው የነበረ ሲሆን ኢያሱ ከሥልጣን ከተወገዱ በኋላ ወደ ቦታቸው ተመልሰዋል፡

  መርሻ ናሁሰናይ እንደ አውሮጳ አቆጣጠር በ1850 መጀመሪያ ገደማ በአንኮበር አካባቢ በሽዋ ተወለዱ። እድሜያቸው ለትምህርት እንደደረሰም በአቅራቢያቸው ከሚገኝው ወላጅ አባታቸው ከሚያገለግሉበት ቤተክርስቲያን ገብተው መሰረታዊ የሃይማኖትና ቀለም ትምህርትን እንደቀሰሙ ከትውልድ ትውልድ ሲተላለፍ የቆየ የቤተሰብ አፈ ታሪክ ያመለክታል።

  መርሻ የወጣትነት ጊዜያቸውን በአባታቸው እርሻና በቤተክርስቲያን አካባቢ በመማርና በመርዳት አሳልፈዋል። ከቦታ ቦታም እየተዘዋወሩ ሰፊ ዕውቀትንና ልምድን አካብተዋል። በጎልማሳነት ዕድሜያቸው ምን አይነት ባህርይ እንደነበራቸው ዝርዝር መረጃ እስካሁን አልተገኘም። ሆኖም ግን ከልጅነታቸው ጀምሮ የተለያዩ ነገሮችን ለመማርና ለመሞከር ከፍተኛ ፍላጎት እንደነበራቸውና ብርቱ ጥረት እንዳደረጉ ይነገራል፡፡

  የዓፄ ምኒልክና የራስ መኮንን አማካሪና የቅርብ ረዳት በመሆንም በወቅቱ ሀገራዊና ዲፕሎማሲያዊ ጉዳዮች ላይ ተሳታፊ ለመሆን እድል አግኝተዋል። አቶ መርሻ ዘመናዊ ዕውቀትን የቀሰሙ፤ የፈረንሳይኛ ቋንቋን ያጠኑ፤ ስለአውሮጳ ታሪክና ባህል ሰፊ ዕውቀት የነበራቸውና በሀገር ውስጥም ሆነ በውጭው ዓለም ለመታወቅ የበቁ አስተዋይ ሰው ነበሩ።

  ድሬ የኚህ ሰው ውለታ አለብሽ!!

  ድሬ ስትጠቀስ ስማቸውም አብሮ ከሚነሳ የጠሃይ መውጫ ልጆች መካከል
  ተወዳጅ ድምጻዊ አሊ ቢራ፣ ሐኪሙ ፕ/ር አስራት ወልደየስ፣ ባዮ ኬሚስቱ መምህር ዶ/ር ጌታቸው ቦሎዲያ፣ ዶ/ር አብዱል መጂድ ሁሴን፣ ባለሀብቱ ኦክሲዴ፣ ገጣሚና ደራሲ ዶ/ር ፍቅሬ ቶሎሳ፣ እግር ኳስ ተጫዋቹ ሚግ፣ ተወዳጆቹ ጋዜጤኞች ጳውሎስ ኞኞ እና ደምሴ ዳምጤ እንዲሁም ሌሎች ከድሬ ምድር በቀሉ፡፡

   

  ምንጮች
  ^ ታዴዎስ አሰበወርቅ Mersha Nahusenay bio in English)
  ^ Richard Pankhurst. "The beginnings of Ethiopia’s modernisation". 2003.
  ^ Getahun Mesfin Haile (2003). "Dire Dawa: Random thoughts on a centenary". Addis Tribune.
  ^ ገዛህኝ ይልማ (ታህሳስ 2000 ዓ.ም.). "ድሬዳዋ የምዕተ ዓመት ጉዞ". ድሬ መጽሔት (ልዩ እትም).

   

   

   

  Read more »

 • ቲማቲም መመገብ የሆድ ካንሰርን ይከላከላል - Eating Tomatoes Can Prevent Stomach Cancer.

                                         

  ቲማቲም መመገብ የካንሰር ህዋሳት እድገትን ለማቆም እንደሚረዳ አንድ ጥናት አመለከተ።

  ይህን ተወዳጅ ፍራፍሬ እስከነ ልጣጩ ሙሉውን መመገብ የሆድ ውስጥ ካንሰርን በመከላከሉ ረገድ ሚናው ላቅ ያለ መሆኑ ተሰምቷል።

  ከዚህ ቀደም የተደረጉ ጥናቶች በቲማቲም እና ሌሎች ቀይ ቀለም ያላቸው ፍራፍሬዎች እና አትክልቶች ውስጥ የሚገኘው ላይኮፒን የተሰኘ ኬሚካል ካንሰርን የመዋጋት አቅም እንዳለው ማረጋገጣቸው ይታወሳል።

  አዲሱ በጣሊያን ሜርኮግሊያኖ የካንሰር ጥናት ማዕከል የተደረገው ጥናት ደግሞ የቲማቲም ካንሰርን የመከላከል ብቃት ከላይኮፒን ኬሚካል ጋር ብቻ የተገናኘ አይደለም ብሏል።

  የጥናቱ ፀሃፊ ዳንኤል ባሮን እንደሚሉት፥ ቲማቲምን እስከነ ልጣጩ ቀቅለንም ሆነ ጥሬውን መመገብ የካንሰር ህዋሳት እንዳይስፋፉ እና እንዳያድጉ ከማድረጉም በላይ እንደሚገድላቸው በጥናቱ ተረጋግጧል።

  በጥናቱ የተሳተፉት ፕሬፌሰር አንቶኒዮ ጂርዳኖ በበኩላቸው፥ የጥናቱ ግኝት ተጨማሪ የሆድ ካንሰር መከላከያ መንገዶችን ለመፈለግ ለሚደረገው ጥረት ከፍተኛ አስተዋፅኦ እንደሚኖረው ተናግረዋል።

  ጥናቱ ቲማቲም በሽታውን ለመከላከል የሚያበረክተውን ሚና ከመጠቆሙ ባሻገር በቀጣይ አዲስ የበሽታው ማከሚያ ዘዴን ለመፈለግ መንገድ ይጠርጋል ተብሏል።

  ይህ ጥናት በሴሉላር ሳይኮሎጂ ጆርናል ላይ ታትሞ ወጥቷል።

  የሆድ ካንሰር ወይንም የጨጓራ ካንሰር በአለማችን ብዙም የተለመደ በሽታ አይደለም።

  ይሁን እንጂ በብሪታንያ በየአመቱ 7 ሺህ ሰዎች በበሽታው ይጠቃሉ።

  ምንጭ፦ www.dailymail.co.uk/

  Read more »

 • ፕሮፌሰር ሃይሌ ገሪማን በጨረፍታ

                                        
  (የዘመን አቆጣጠሩ ሁሉ እንደ አውሮፓውያን ነው ) 
  ከአሥር ልጆች አራተኛ በመሆን የተወለደው ኃይሌ ገሪማ መጋቢት 1946 ላይ ነው ይችን አለም የተቀላቀለው ፡፡ እናቱ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት አስተማሪ ሲሆኑ አባቱ, አቶ ገሪማ ተፊካ ደግሞ የተውኔት እና የቴአትር አዘጋጅ ነበሩ፡ እንደ ሳንኮፋ ድረገጽ ከሆነ ፕሮፌሰር ሃይሌ ገሪማ ገና በወጣትነት ዘመኑ የአባቱን ፈለግ በመከተል በአባቱ ቲያትሮች ይለማመድ ነበር ፡፡ ሃይሌ እና እህቱ ዘመናዊ ትምህርት ቤት በመሄድ በቤተሰባቸው ውስጥ የመጀመሪያዎቹ እንደሆኑ ድረገጹ ጠቅሶ የሃገሩን ባህል እና ሥርዓተ ትምህርት በማስተማር እና ለአሜሪካ የሰላም ጓድ አባላት እንዴት ፊደል መጻፍ እንደሚቻል በማስተማር እንዲሁም ባህሉን በማስተዋወቅ የድርሻውን ተወጥቷል ፡፡
  ፕሮፌሰር ሃይሌ. "ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ በፈጠራ ጥበብ ማዕከል ውስጥ አጭር ቆይታ ካደረገ በኋላ, ድራማ ለማጥናት ወደ አሜሪካ አቅንቷል፡፡እዚያም ሸሪኪያና ከተባለች ሴት ጋር በትዳር ተጣምሮ አምስት ልጆችን አፍርቷል፡፡
  በሎስ አንጀለሰ ከተማ ካሊፎርኒያ ዩኒቨርሲቲ ከ1976 ጀምሮ የፊልም ጥበብን በማስተማር ስራ ላይ ተሰማርቶ ይገኛል ፡፡
  የፊልም ጥበብ ቀማሪው ፕሮፌሰር ሃይሌ ገሪማ ከሰራቸው ፊልሞች መካከል አወር ግላሰ ፣ ቻይልድ ኦፍ ሬንሰንስ ፣ ቡሽ ማማ የተባሉ ስራዎችን በ1975 የሰራ ሲሆን ስሪ ታውዘንድ የተሰኘ ፊልም በ1976 ፣ዊልምግተን ፣ቴን ዩ ኤስ ኤ ቴን ታውዘንድ የተሰኘን ፊልም በ1977 አሽስ ኤንድ ኢምበርስ በ1982 ፣ አፍተር ዊንተር ስተርሊን ብሮውን በ1985 ፣ሳንኮፋ በ1993 አድዋ አን አፍሪካን ቪክትሪ በ2000 የሰራ ሲሆን በዩኒቨርሲቲው ተሸላሚም ነው፡፡ የፓን አፍሪካን የፊልም አዘጋጆች ፌዴሬሽን እና የአፍሪካን የፊልም አዘጋጆች ኮሚቴ አባልም ነው ፕሮፌሰር ሃይሌ ገሪማ፡፡
  ከሰራቸው ፊልሞች መካከል:-
  • 1972 - Hour Glass Hour Glass
  • 1972 - Child of Resistance
  • 1976 - Bush Mama
  • 1976 - Mirt Sost Shi Amit (also known as Harvest: 3,000 Years)
  • 1978 - Wilmington 10 -- U.S.A. 10,000
  • 1982 - Ashes and Embers
  • 1985 - After Winter: Sterling Brown
  • 1993 - Sankofa
  • 1994 - Imperfect Journey
  • 1999 - Adwa - An African Victory
  • 2009 - Teza
  Over the course of his career, Gerima has received numerous awards and distinctions in film festivals:-
  • 1976 - Grand prize / Silver Leopard for Harvest: 3,000 Years- Locarno
  • 1982 - Grand Prix Award for Ashes and Embers-Lisbon International Film Festival
  • 1983 - FIPRESCI Film Critics Award for Ashes and Embers-Berlin International Film Festival
  • Outstanding Production Ashes and Embers - London Film Festival
  • 1984 - Tribute Festival De la Rochelle, France
  • 1987 - Long Metrage De Fiction-Prix de la Ville de Alger for Ashes and Embers
  • 1993 - Best Cinematography Award for Sankofa, FESPACO, Burkina Faso
  • 2003 - Lifetime Achievement Award, 4th Annual Independence Film Festival, Washington D.C.
  • 2006 - Festival De Cannes Selection Official Cannes Classic -Harvest: 3,000 Years
  • 2008 - Venice Film Festival Special Jury Prize and Best Screen Play Award - Teza
  • 2009 - Jury Award at the 18th International Film Festival Innsbruck/Austria - Teza
  • 2009 - Golden Stallion of Yennenga at the FESPACO African Film Festival - Teza http://www.rfi.fr/actuen/articles/111/article_3102.asp
  • 2009 - Dioraphte Award Hubert Bals film in highest audience regard at the Rotterdam Film Festival
  • 2009 - Golden Tanit/Best Film Award for its "modesty and genius," Best Music (Jorga Mesfin Vijay Ayers), Best Cinematography (Mario Massini), Best Screenplay (Haile Gerima), Best Supporting Actor Abeye Tedla at the Carthage/Tunisia Film Festival for Teza
  • 2009 - Golden Unicorn and Best Feature Film at the Amiens/France International Film Festival France for Teza
  • 2009 -The Human Value's Award at the Thessaloniki Film Festival in Greece for Teza
  • 2009 - Official Selection at the Toronto Film Festival for Teza
  ፕሮፌሰር ሃይሌ ገሪማ በሚሰራቸው የፊልም ጥበቦች ሃገሩን በማሰተዋወቅ ባለውለታ እንደሆነ ብዙዎች ይመሰክሩለታል፡፡ ወደፊትም በሚያበረክታቸው የፊልም ስራዎቹ ውስጥ ለሃገሩ ልዩ ቦታ እንደሚሰጥ ተናግሯል፡፡
  #TEFERI_MIHIRET

  Read more »

 • "ሦስተኛው ይባስ"

                         
  ከያሬድ ሹመቴ

  1. ፊታውራሪ ዳምጠው ከተማ በዳግማዊ አፄ ምኒልክ ዘመነ መንግስት ስመ ጥር መኮንን ነበሩ። ከፍተኛ ዲፕሎማት በመሆን ለዓድዋ ጦርነት የሩሲያ መንግስትን የጦር መሳሪያ ድጋፍ እና የህክምና እርዳታ እንድናገኝ ያደረጉ ስኬታማ ሰው ናቸው። እኝህ ሰው ታዲያ ከሩሲያ በዲፕሎማሲያዊ ስኬት ተመልሰው እረፍት እንኳን ሳያደርጉ ዓድዋ ድረስ ተጉዘው በ1888 ዓ.ም የካቲት 23 ቀን ከወራሪው የጣልያን ጦር ጋር ገጥመው የጀግንነት ጀብዱ ፈጽመው በዚያው እለት ህይወታቸው እዚያው ጦር ሜዳ ላይ አልፏል። እኚህ ሰው "የሀገር ጀግና" የሚል ስያሜ መለያቸው ሆኖ እሰከዛሬ ስማቸው ይታወሳል።

  2. የእኚህ ታላቅ ሰው የአብራክ ክፋይ የሆኑት [ራስ] ደስታ ዳምጠው እንደ አባታቸው ሁሉ በርካታ መልካም ስራዎችን ለሀገራቸው ፈጽመው ሲያበቁ በ1928 የጣልያን ጦር ሀገራችንን ለሁለተኛ ጊዜ ሲወር በሱማሌ በኩል ይመጣ የነበረውን ጦር በጀግንነትና በወኔ ዶሎ ድረስ ወርደው በመግጠም የጀግንነት ስራ ቢሰሩም ጦሩ በደረሰበት ሽንፈት ሰራዊታቸው ተበተነ። እሳቸው ግን በአርበኝነት ለአንድ አመት ያህል ሲፋለሙ ኑረው ጣልያን እጅ ላይ ወደቁ። ጣልያን እኒህን ታላቅ ጀግና በየካቲት 16ቀን 1929 ዓ.ም በአደባባይ በጥይት ደብድቦ ገደላቸው። ራስ ደስታ በስማቸው መታሰቢያ ሆስፒታል የተገነባላቸው "ጀግና ሰው" በመሆን ዛሬም ድረስ ይታወሳሉ።

  3. የእኚህ ታላቅ ሰው ልጅ የነበሩት [ሪር አድሚራል] እስክንድር ደስታ ደግሞ እንደ አባታቸው እና እንደ አያታቸው ስኬታማ የአስተዳደር እና የዲፕሎማሲ ሰው ነበሩ። የኢትዮጵያ ባህር ኃይል ምክትል አዛዥ በመሆን ስኬታማ የነበሩት እኚህ ሰው እናታቸው የቀ.ኃይለሥላሴ ልጅ [ልዕልት ተናኜወርቅ] በመሆናቸው ብቻ በህዳር 14 ቀን 1967 ዓ.ም ከ60ዋቹ ከፍተኛ ባለስልጣናት መሀል አንዱ ሆነው በደርግ ጥይት ተደብድበው ተገደሉ።

  ሦስተኛው ይባስ እንግዲህ ይህ ነው። እኚህ ሰው 
  የሞቱት በሀገራቸው ሲሆን ገዳያቸውም የሀገራቸው ሰው ነው። እንደ አያታቸውና አባታቸው በጠላት እጅ ሳይሆን በሀገራቸው በግፍ ተገደሉ። ታሪካቸውን ስናጤነው የሀገሩን ልጅ የገደለው ደርግ እራሱ ጀግና አልተባለም። በሀገራቸውም ሰው የተገደሉትም እስክንድር እንዲሁ። ምክንያቱም "ለሀገሩ ሲል" የሀገሩን ልጅ የገደለ ጀግና አይባልም። "ለሀገሩ ሲል" በሀገሩ ልጅ የተገደለም እንዲሁ።

  "ለሀገሬ ስል ነው" የሚል ሰው የሀገሩን ልጅ የሚገድል ከሆነ ጀግና አይባልምና የታሪክ ተወቃሽ መሆኑ አይቀርም። "ለሀገሬ ስል ነው" ብሎ በሀገሩ ልጅ የሚሞትም እንዲሁ። ሦስተኛው ይባስ በሉ። እርስ በርሱ እየተላለቀ "ለሀገሬ ስለ ነው" የሚል ካለ ልቦና ይስጠው።

  ታሪክ ማለት ዛሬ አልፎ ሲያረጅ እንጂ የጨበጥነው ዘመን እውነታ አይደለምና፥ ዛሬ በሚሰጠን የጀግንነት ስያሜ አንመርቅን። ታሪክ አድሮ ይወቅሳል።

   

   

  Read more »

 • የጥምቀት ክብረ-በዓል እና ፋይዳዉ

                         

  በአዜብ ታደሰና በሸዋዬ ለገሠ 

  ይህ ታላቅ ሃይማኖታዊ በዓል ከሕዝቡ ባህል ጋር ጥብቅ ትስስር ያለው በመሆኑም ከሃይማኖታዊ በዓልነቱ ባሻገር ባሕላዊ ፋይዳውም የጎላ ስለሆነ በሀገር ዉስጥ ካለዉ ማኅበረሰብ በተጨማሪ በርካታ የውጭ ሀገር ጎብኝዎች ፣ በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያንና መንፈሳዊ ተጓዦች የሚታደሙበት በዓል በመሆኑ እንዲሁም የዓለም አቀፉን ሕብረተሰብ ቀልብ እየሳበ በመምጣቱ የአከባበር ሥነ-ስርዓቱን በተመ የትምሕርት፤የሳይንስና የባሕል ድርጅት በ«UNESCO» ጥበቃ ስር በዓለም ቅርስነት ለማስመዝገብ የተጀመረዉ ጥረት መጠናቀቁ ተሰምቶአል። በዚህ ዝግጅታችን የጥምቀት በዓል አከባበርን ይዘን በተለይ በዘንድሮዉ በጎንደር ስለሚካሄደዉ ልዩ አከበር፤ በክብረ በዓሉ ላይ ስለሚነገሩት ሥነ-ቃሎች እንዲሁም በዉጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያዉያን በዓሉን እንዴት እንደሚከብሩት እንቃኛለን።

  ምሁራን ጥምቀት ለሚለው ቃል መነከር ፣ መታጠብ የሚሉ ትርጓሜዎችን ይሰጡታል፡፡የጥምቀት ዋዜማ ከተራ ይባላል፡፡ የከተራ እለት/ ጥር 10 ማለት ነው/ ከቀኑ 9 ሰዓት ጀምሮ በሚሰማው የደውል ጥሪ ታቦታቱ ፤ የተለያዩ ህብረ ቀለማት ያላቸው አልባሳት በለበሱ ህዝበ ክርስቲያን ታጅበው ጉዞአቸውን ወደ ጥምቀተ ባህር ያደርጋሉ።  መምህር ካሳይ ገብረዝጊአብሔር የጥምቀት በዓል አመጣጥን እንዲህ ይገልጹታል።

  በኢትዮጵያ  ከዋዜማዉ ከከተራ ጀምሮ በመከበር ላይ የሚገኘዉ የጥምቀት በዓል ታቦታቱ ከየአብያተ ክርስቲያናቱ በክብር ወጥተው በሕዝቡ እልልታ፣ ሽብሽባ እና በካህናቱ ውብ ያሬዳዊ ዜማ ወደ ወንዝ አልያም ወደተዘጋጀ የዉኃ ቦታ በመውረድ ሕዝቡን በሰፊው የሚያሳተፍበት የጥምቀት ሥነ-ስርዓት ተከናዉኗል። በዓሉ በተለይ በጎንደር ከተማ በድምቀት በመከበር ላይ መሆኑን በስልክ የነገሩን የጎንደር ከተማ ባህል ቱሪዝምና ወጣቶችና ስፖርት መምርያ ኃላፊ አቶ አስቻለዉ ወርቁ ተናግረዋል። የብዙ ታቦታት ሀገር የሆነችው ይህች ከተማ በዓይነቱ ለየት ያለ ባሕረ ጥምቀትም አላት። ይህ የአፄ ፋሲል መዋኛ የነበረው ታሪካዊ ባሕረ ጥምቀት ለጥምቀት በዓሉ ትልቅ ሞገስን የሚሰጥ ነው። ለዚሁ ለጥምቀት በዓል የከተማዉን ዝግጅት በተመለከተ አቶ አስቻለዉ ወርቁ በጥምቀተ ባህሩ አካባቢ መቀመጫ መድረክ ተዘጋጅቶአል፤ እስከ 50 ሚትር የሚረጭ የዉኃ ማስተላለፍያም ተዘጋጅቶአል፤ የከተማዋ እንግዶች የሚያርፉበት በቂ ሆቴልም አለ። የደህንነት ስጋት የለም ሌቦችን ለመጠበቅ አካባቢዉ ላይ የቆመየፖሊስ ጣብያም ተዘጋጅቶአል ሲሉ ተናግረዋል።      

  በቅርቡ የተባበሩት መንግሥታት የማይዳሰሱ ቅርሶች ዓመታዊ ጉባዔን ለመጀመርያ ጊዜ ያስተናገደችዉ ኢትዮጵያ የጥምቀት ክብረ በዓልን በዓለሙ የቅርስ መዝገብ ለማካተት ዝግጅቱ መጠናቀቁን የነገሩን በኢትዮጵያ ቱሪዝም ድርጅት የሕዝብና ዓለም አቀፍ ዳይሪክተር አቶ ጌትነት ይግዛዉ ንጉሴ ከተቋሙ የመጡ ባለሞያዎች እቦታዉ ላይ ይገኛሉ። በርግጥ ክብረ በዓሉን በዓለሙ ቅርስ ለማስመዝገብ የሚደረገዉ ሥራ በአንድ ጊዜ የሚጠቃለል እንዳልሆነ ተናግረዋል።  

  ውብና ድንቅ የሆነዉን ይህን ክብረ በዓል ለማክበርና ለማየት  አገር ተሻግረው የሚመጡ የውጭ ሀገር ዜጎች ከዓመት ወደ ዓመት ቁጥራቸው እየጨመረ መምጣቱ ሃገርን በማስተዋወቁ ረገድ ጠቀሚታዉ የጎላ መሆኑ እሙን ነዉ። በጥምቀት በዓል ላይ በሚታዩት ባህላዊ ጭፈራዎች ላይ ከሚሰሙት ሥነ-ቃሎች መካከል ጥቂቶቹን መምህር ካሳይ ገብረዝጊአብሔር እንዲህ ሰፋ ያለ ማብራርያ ሰተዉናል።

  በሃይማኖታዊና በባህላዊ በዓልነቱ የሚታወቀዉ የጥምቀት በዓል በድምቀት የሚከበረዉ በኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን በተለያዩ ሃገራት በሚኖሩ ኢትዮጵያዉያን ዘንድም ነዉ። በጀርመን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን ኃላፊና የኮሎኙ ደብረ ሰላም ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስትያን  ሊቀ ካህናት ዶ/ር መርዓዊ ተበጀ፤ በጀርመን በሚገኙ ኢትዮጵያዉያን ዘንድ የበዓሉን አከባበር የሥራ ቀን በመሆኑ በሁለኛ ደረጃ በአዉሮጳ ከፍተኛ ቅዝቃዜ ወቅት በመሆኑ እንደ ኢትዮጵያ በአንድድ ቀን ባይዉልም ቅሉ በድምቀት እንደሚከበር ተናግረዋል። ።

  መልካም በዓል እየተመኘን በሠላም በጤና የዓመት ሠዉ እንዲለን በመመኘት ቃለ ምልሱን የሰጡንን በማመስገን ሙሉ ድምፁን ከድምፅ ማድመጫ ማዕቀፉን በመጫን እንዲከታተሉ እንጋብዛለን።

  ምንጭ:- DW

   

  Read more »

 • የዘመን መለወጫ በዓል ስያሜዎች

   

                                                                                                                       

   

   

  ይህ በዓል "የዘመን መለወጫ"፤ "አዲስ ዓመት" ከሚሉት በተጨማሪ ሌሎች ስሞችም አሉት፡፡

   ሀ. ቅዱስ ዮሐንስ

  ቅዱስ ዮሐንስ መጥምቅ ተብሎ ከጌታችን ስብከት አስቀድሞ እንደሚመጣና ጥርጊያውን እንደሚያዘጋጅ በነቢዩ ኢሳይያስ ተነግሮለት ነበር /ኢሳ.40.3/፡፡ በዚህም መሠረት በዘመነ ብሉይ መጨረሻና በዘመነ ሐዲስ መጀመሪያ ተነስቶ «መንግሥት ሰማያት ቀርባለችና ንስሐ ግቡ» «እነሆ የዓለሙን ኃጢአት የሚያስወግድ የእግዚአብሔር በግ» በማለት ስለ ጌታችን አዳኝነት መስክሯል፤ሕዝቡን ስለ ኃጢአታቸው እየገሰፁ ንስሐ እንዲገቡ አድርጓል፡፡ ጌታችንንም በዮርዳኖስ ወንዝ አጥምቋል፡፡


  የቅዱስ ዮሐንስ ዕረፍት/ምትረት ርእስ/ የሚታሰበው መስከረም ሁለት ቀን ቢሆንም እንኳን ተግባሩ በዘመነ ወንጌልና በዘመነ ሐዲስ መካከል የነበረ መሸጋገሪያ በመሆኑ የቅዱስ ዮሐንስ መጥምቅ መታሰቢያ በዓል የብሉይ ኪዳን ምሳሌ ከሚሆነው ካለፈው ዓመት የሐዲስ ኪዳን ምሳሌ ወደሚሆነው አዲሱ ዓመት መሸጋገሪያ በሆነው በመስከረም አንድ ቀን እንዲከበር፤ በዓሉም በእርሱ ስም እንዲሰየም አባቶ ወስነዋል፡፡


  ለ. ርእሰ ዓውደ ዐመት

  ዓውድ ማለት ዙሪያ፣ ክብ፣ ክስተቶች አንድ ጊዜ ከተከሰቱ በኋላ ደግመው የሚመጡበት ጊዜ ማለት መሆኑን ተመልክተናል፡፡ ስለዚህ ዓውደ ዓመት ማለት ዓመቱ አንድ ጊዜ ከተጀመረ በኋላ ሁለተኛ ዓመት እስኪጀመር ያለው ጊዜ ማለት ነው፡፡ ዓመትን መቁጠር ከየትኛውም ወር እና ቀን መጀመር ይቻላል፡፡ኅዳር 13 ብንጀምር አንድ ዓውደ ዓመት ማለት እስከሚቀጥለው ኅዳር 12 ቀን ያለው ጊዜ ማለት ነው፡፡ ነገር ግን መደበኛው ዓውደ ዓመት የሚጀምረው መስከረም አንድ ቀን ነው፡፡ ይህ ቀን ርእሰ ዓውደ ዓመት የተባለውም «የሁሉም ዓውደ ዓመት መጀመሪያዎች ቁንጮ ነው» ለማለት ነው፡፡


  ሐ. ዕንቁጣጣሽ

  ሐጎስ ዘማርያም ለምለም በቀለን ለመጀመሪያ ዲግሪ ማሟያ ያቀረበችውን ጽሑፍና ሌሎች የቃል ማስረጃዎችን ጠቅሶ በሐመር መጽሔት የ1997 ዓ.ም መስከረም/ ጥቅምት ዕትም ላይ በቀረበው ጽሑፍ «ዕንቁጣጣሽ» ለሚለው የዚህ ስያሜ ሁለት ዋና ዋና መነሻዎችን እንዳሉት ገልጿል፡፡

   

  1. ዕንቁጣጣሽ የሚለው ቃል ሁለት ቃላት ካሉት ጥምር ቃል የተገኘ ነው፡፡ ዕንቁ እና ጣጣሽ ከሚሉ ዕንቁ የከበረ ዋናው ውድ የሆነ አብረቅራቂ ድንጋይ ነው፡፡ ጣጣሽ የሚለው ቃል ፃዕ ፃዕ ከሚለው የግእዙ ቃል የተወረሰ ሲሆን ትርጉሙ ግብር፣ ጣጣ፣ ገጸ በረከት፣ ማለት ነው፡፡ለምሳሌ በሸዋ አካባቢ ግብር አለብኝ ሲል «ጣጣ አለብኝ» ይላል፡፡ይህ ስያሜ ለበዓሉ የተሰጠው ከንግሥተ ሳበ /ንግሥት ማክዳ/ ጋር በተያያዘ ነው፡፡ንግሥተ ሳባ ንጉሥ ሰሎሞንን ለመጎብኘት ሔዳ ሳለ የጸነሰችውንቀዳማዊ ምኒልክን በወለደች ጊዜ ሕዝቡ ንጉሥ ተወለደ ብሎ እልል እያሉ «አበባ እንቁ ጣጣሽ» እያለ ገጸ በረከት ለንግሥቲቱ አበረከቱ፡፡ያ የዘመን መለወጫ በዓልም ልጃገረዶች የአበባ ገጸ በረከት የሚያቀርቡበት ስለሆነ ዕንቁጣጣሽ ተባለ፡፡

  2. ዕንቁጣጣሽ ግጫ ማለት ነው፤ ግጫ ደግሞ የሣር ዓይነት ነው፡፡የአበባ፣ የእርጥብ ስጦታ መስጠት የተጀመረው በኖኅ ዘመን ነው፡፡ ኖኅ የጥፋት ውኃ በጎደለ ጊዜ መጉደሉን ለማረጋገጥ ርግብን ልኳት የወይራ ቅጠል አምጥታለች ይህ የሆነበት ወቅት የመስከረም ወር በመሆኑ ከዚያ ጊዜ ጀምሮ የዘመን መለወጫ ሆነ፡፡በርግቧ አምሳልም ልጃገረዶች የተለያየ ዓይነት ሣርና አበባ በመያዝና በማደል በዓሉን ያከብራሉ፡፡ በሣሩ ስምም በዓሉ ዕንቁጣጣሽ ተባለ፡፡

   
  Read more »

 • የኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር ፅንሰ ሃሳብ

   

  እንግዲህ በአጠቃላይ ዋናዎቹ የጊዜ / የዘመን/ መስፊሪያዎች ዕለት፣ ወር እና ዓመት ናቸው፡፡ ሦስትቱም ተመላላሽ ክስተቶችን / ለምሳሌ የፀሐይን መውጣት/ መሠረት ያደረጉ ናቸው፡፡ እነዚሀ ተመላላሽ ክስተቶች አንድ ጊዜ ከተከሰቱ በኋላ ደግመው እስኪከሰቱ የሚፈጁት ዘመንnወይም ጊዜ ዓውድ ይባላል፡፡ ዓውድ ማለት ዙሪያ፣ ክብ፣ እንደ ቀለበት ዙሮ የሚገጥም ማለት ነው፡፡ ስለዚህዓውድ ማለት ክስተቶቹ አንድ ጊዜ ከተከሰቱ በኋላ ደግመው እስኪመጡ ድረስ ያለው ጊዜ ማለት ነው፡፡ በዚህ መሠረት ከላይ ያየናቸው ሦስት መስፈሪያዎች/ ዕለት፣ ወርኀ፣ ዓመት/ ዓዕዋዳት / ዓውዶች/ የሚወጡበት ጊዜ ዓውደ ዕለት፣ ዓውደ ወርኀ፣ ዓውደ ዓመት ይባላሉ፡፡


  መጀመሪያ ላይ ሰዎች እነዚህን ሦስቱን መስፈሪያዎች /ዓዕዋዳት/ /በተለይም ቀንና እና ወርን/ለየብቻቸው ይጠቀሙባቸው ነበር፡፡ ከዚህን ያህል ቀን፣ከዚህን ያህል ወር በኋላ /በፊት/ እያሉ ጊዜን ይለኩ ነበር፡፡ እነዚህ ሦስቱን በቅንብር/በቅንጅት/ ለመጠቀም ሲፈለግ ግን የዘመን አቆጣጠር ስሌት ያስፈልጋል፡፡ምክንያቱም አንድ ወር 29 ከግማሽ ቀን ነው፡፡ እንዲሁ እንዳለ ለመቁጠር ቢፈለግ የመጀመሪያው ወር ጠዋት ላይ ቢጀመር ሁለተኛው ወር ምሽት ላይ ይጀምራል፣ ሦስተኛው ደግሞ ድጋሚ ጠዋት ላይ ይጀምራል፤ ይህን ለመቅረፍ ወሩን ሙሉ ሰላሳ ቀን ቢያደርጉት ከትክክለኛው ወር /የጨረቃ ዐውድ/ ግማሽ ቀን ይተርፋል፤ 29 ቀን ብቻ ቢያደርጉት ደግሞ ግማሸ ቀን ይጎድላል፡፡


  አንድ ዓመት 365 ከሩብ ዕለታት አሉት፡፡ ዓመትን በወራት ለመቁጠር ቢፈለግ፤ዓመቱን 12 ወር ቢያደርጉት የዓመቱ /የዕለታት ቁጥር /29.5X12=354/ ብቻ ይሆናል፡፡ይህም ከትክክለኛው ዓመት /365-354=11/ ዕለታት ያህል ያንሳል፡፡13 ወር ቢያደርጉት ዓመቱ /365X13=385.5/ ቀናት ይሆናል ይህም ከትክክለኛው ዓመት /383.5-365=19/ ቀናት ያህል ይበልጣል፡፡ ስለዚህ እነዚህን መስፈሪያዎች በቅንጅት ለመጠቀምይህንን አለመጣጣም የሚፈታ ቀመር /የዘመን አቆጣጠር ሥርዓት/ ያስፈልጋል፡፡ በተለያዩ አካባቢዎች የተለያዩ የዘመን አቆጣጠሮች ተዘጋጅተዋል፡፡ ከእነዚህ መካከል የአይሁድን፣የሮማውያንን እና የሀገራችንን አቆጣጠሮች በአጭሩ እንመለከታለን፡፡ የአይሁድ ዘመን አቆጣጠር የአይሁድ ዘመን አቆጣጠር እያንዳንዳቸው 29 እና 30 ዕለታት ያሏቸው 12 ወራት አሏቸው፤

   

  ተ.ቁ

  የአይሁድወራት

  የዕለታት ብዛት

  ወራቱ በእኛ

  1

  ኒሳን

  30

  መጋቢት/ ሚያዝያ

  2

  ኢያር

  29

  ሚያዝያ/ ግንቦት

  3

  ሲዋን

  30

  ግንቦት/ ሰኔ

  4

  ታሙዝ

  29

  ሰኔ/ ሐምሌ

  5

  አቭ

  30

  ሐምሌ/ ነሐሴ

  6

  አሉል

  29

  ነሐሴ/ መስከረም

  7

  ኤታኒም

  30

  መስከረም/ጥቅምት

  8

  ቡል

  29/30

  ጥቀምት/ ኅዳር

  9

  ከሴሉ

  30/29

  ኅዳር/ ታህሳስ

  10

  ጤቤት

  29

  ታህሳስ/ ጥር

  11

  ሳባጥ

  30

  ጥር/ የካቲት

  12

  አዳር 1

  29

  የካቲት/ መጋቢት

   እነዚህ የዓመቱ 12 ወራት በአጠቃላይ 354 ያህል ብቻ ዕለታት ይኖሯቸዋል፡፡ ይህም በትክክለኛው ዓመት በ11 ዕለታትያህል ቢያንስም አዲስ ዓመት ይጀምራሉ፡፡ ልዩነቱ በሁለት ዓመታት 22 ዕለታት፣ በሦስት ዓመት ደግሞ 33 ዕለታት ያህል ይሆናል፡፡ስለዚህ በየሦስት ዓመቱ ከአስራ ሁለተኛው ወር ጳጉሜን በፊት አንድ ሌላ ወር ይጨምሩና የዓመቱን የወራት ቁጥር ዐሥራ ሦስትያደርጉና ልዩነቱን ያስተካክሉታል፡፡

  በፕሮፊሰር ጌታቸው ኃይሌ

  Read more »