PLANET ETHIOPIA
Advertisment

Most Popular Articles


 • በቤት ውስጥ የሚዘጋጁ የቆዳ ሸንተረር ማጥፊያ መላዎች

  በቆዳዎት ላይ ያለ ሸንተረር ምቾት ነስቶት ይሆናል። ሸንተረሩን የሚያስወጡ ሁለት ዋነኛ ምክንያቶች ከእርግዝና እና ከውፍረት በኋላ ያለው የሰውነት መቀነስ ነው፡፡ እነዚህ ምልክቶች በእግር፣ ክርን፣ ወገብ፣ ጡት እና ጀርባ ላይ ሊወጡ ይችላሉ፡፡ ይሄን ለማጥፋት ግን ከገበያ ተገዝተው ከሚመጡ ይልቅ በቤት ውስጥ የተሰሩ መድሀኒቶች ሁነኛ መፍትሄዎች ናቸው::

  የእንቁላል (ነጭ) ፈሳሹ ክፍል፦ ይህ የእንቁላል ፈሳሽ በፕሮቲን የበለጸገ ነው። በዚህ ምክንያትም በቆዳችን የሚገኝን ሸንተረር ለማጥፋት በጣም ይረዳል፡፡ እንቀላሉን ከመቀባታችን በፊት ሸንተረር ያለበትን በማጠብ ቆዳችንን ንጹህ ማድረግ ይኖርብናል። ከዚያም ሁለት እንቁላል ወስደን አስኳሉን ከፈሳሹ በመለየት የእንቁላሉን ፈሳሽ ክፍል በሹካ በደንብ አማስለን ካበቃን በኋላ መቀባት፡፡ የእንቁላሉ ፈሳሽ እንዲደርቅ ቢያንስ ለ20 ደቂቃ እንተወው። ከዚያም በኋላ መታጠብ እና ብንችል የወይራ ዘይት ቆዳችንን መቀባት። ይህን ማድረግ ቆዳችን እንዳይደርቅ ያግዛል። ይህን ዘዴ ቢያንስ ለሁለት ሳምንታት በየቀኑ መጠቀም ውጤቱን አስተማማኝ ያደርገዋል።

  ይሞክሩት፤

  በእርግጠኝነት ጥሩ ውጤት ያገኛሉ፡፡

   

  ምንጭ: http://www.mahderetena.com/

   

  Read more »

 • “የተመኘሀትን ሴት ማንም ትሁን የራስህ ልታረጋት ትችላለህ” (ምርጥ የሆነ ሳይኮሎጂ)

  ከታደለች ስዩም

  ሴቶች የሚወዱት ወንድ ሚሊዮን ብር ወይም ብዙ ታላቅና ውብ
  ነገር ያላቸው ያህል እንዲሰማቸው አድርጎ ለሚመለከታቸው
  በውስጣቸው ቦታ የመስጠት ዝንባሌያቸው ከፍተኛ ነው፡፡ ነገር
  ግን በየሁኔታዎቹ አጋጣሚ ለጥቂት ሰከንድም ቢሆን የእሷን
  ደስታ ሊጨምርላት የሚችሉ የተለያዩ ሌሎችም በርካታ ነገሮችን
  ልታውቅላት የሚያስፈልግና ለአንተም ጥሩ ግንኙነት ለመፍጠር
  ወሳኝ ጉዳይ ይሆናል፡፡
  ሌላው ደግሞ ሴቶች ብዙውን ጊዜ ራሳቸውን ንግስት አድርገው
  የማሰብ ዝንባሌው ያላቸው ስለሆነ ከእሷ ሳይመጣ ይህን ራሷን
  የመካብ ስራ ከአንተ ይውጣና በውስጧ ይህ ስሜት እንዲሰማት
  አድርጋት፡፡ እነዚህን ነገሮች እንደመቀስቀሻና ራሷን ማንቂያ
  አድርጋ እንድታስብ አድርገህ ከያዝካት ምንጊዜም ካንተ
  ለመለየት ሙከራው ቀርቶ ይህን ነገር ማሰብ እንደ መጥፎ
  ህልም ያባንናታል፡፡
  ለአንተ ንግስትህ እንደሆነች በድርጊትም ሆነ በንግግርህ
  ከገለጽክላት ሁሌም ጥሩ ስሜት ስለሚሰማት እንደማግኔት
  ልብህ ላይ ትጣበቃለች፡፡ ሴቶች ከወንዶች ይልቅ ስሜታቸውን
  ተከትለው ይፈሳሉ፡፡ በጥልቁ ስሜታቸው ከመጣህባቸው
  አይመለሱም፡፡ ለዚህም ስሜቷ ሲነካ የሚገርሙ ምላሾች
  አሏት፡፡ ይህንን ሁሉ ስሜታቸውን የማይረዱላቸው ወንዶች
  ወይም መጀመሪያውኑ ሴቷን እየፈለጋት ከንግግሩ ጀምሮ እስከ
  አቀራረቡ ድረስ ገገማ ዓይነት የሚሆንባቸው ወንድ
  ያናድዳቸዋል፡፡ ሴትን ልጅ ቀርቦ ማናገርና ጥሩ ግንኙነት
  መፍጠር የብዙ ወንዶች ችግር ነው፡፡ ከተዋወቁና ጥሩ የሆነ
  መቀራረብ ውስጥም እያሉ ወንዶች አሁንም ትልቅ የሆነ
  የግንኙነት እንቅፋት ይፈጠርባቸዋል ወይም በራሳቸው ጊዜ
  ይህንን ሁኔታ ይፈጥራሉ፡፡ ታዲያ በጣም ወሳኝ የሆኑና
  የትኛውም ወንድ ሊያውቃቸው የሚገቡ መሰረታዊ ነገሮች አሉ፡፡
  እነዚህ የመልካም ግንኙነት ቅመሞች ወንድ ልጅ ከመጀመሪያ
  ጀምሮ ውስጡ የደነገጠላትና ለፍቅር የሚመኛትን ሴት ቀርቦ
  ከማናገር ጀምሮ እንዴት በጥሩ ግንኙነት ወደ አስደሳች የፍቅር
  ሽሚያ ውስጥ መግባት አለበት የሚለውን ያጠቃለለ ነው፡፡
  ታዲያ በፍቅር ሽሚያ ውስጥም ሆነው ወንዶች ቀጣይ የሆነ
  አስደሳች ግንኙነት እንዲኖራቸው ማድረግ እንዳለባቸው ሊያውቁ
  ይገባል፡፡
  አስቀድሜ የመጀመሪያ የፍቅር ግንኙነት ችግር የሚለውን ሀሳብ
  ላብራራ፡፡ ይህም ጎልማሳ የሆኑ ወንዶች ከአንዲት ሴት ጋር
  ለሶስት ወይም ለአራት ወር አብረው ይቆያሉ፡፡ በዚህ ጊዜ ከእሷ
  ጋር በስልክ በሳምንት ሁለቴ ብቻ ሲገናኙ በአካል ደግሞ አንድ
  ጊዜ ብቻ ይገናኛሉ እንበል፡፡ ታዲያ በዚህ የረጅም ጊዜ ግንኙነት
  ጥሩ የሆነ መግባባትን ለመፍጠር አልቻሉም፡፡ ይህ አይነት
  ችግር ያለባቸው ብዙ ወንዶች ከመሆናቸው አንፃር የሚከተሉትን
  አጠቃላይ መደምደሚያ ማንሳት ይቻላል፡፡ እነዚህ የሚነሱ
  ሀሳቦች መሰረታዊና በወንዶች ላይ በብዛት የሚታዩ ችግሮች
  ናቸው፡፡ ችግሩን አውቀውት ወደ ተሻለ የፍቅር መፍትሄ
  የሚመልሳቸውም ጭምር ነው፡፡ ከእነዚህም መካከል፡-
  1.
  ከተቃራኒ ጾታ ጋር ቀርቦ ለመነጋገር በራስ የመተማመን ችሎታ
  ማነስ፡-
  ብዙ ጊዜ እነኚህ ሰዎች በአንድ ቤተሰብ ብቻ (single
  parent) ያደጉ ወይም እህት ኖሯቸው የማያውቁ ናቸው፡፡
  በዚህም ስለሴቶች ያላቸው እውቀትና ለሴት ልጅ ያላቸው
  አመለካከት የተዛባና ፍራቻ የነገሰበት ይሆናል፡፡ ከሴቶች ጋር
  አብሮ ማደግ በቅርብ የሴቶች ባህሪ ምን እንደሚመስል
  ለማወቅ ስለሚያስችል በዚያም ወንድ ልጅም ሲያድግ ስለ
  ሴቶች ባህሪ ጥሩ እውቀት እንዲኖረው ያደርጋል፡፡ ስለሴቶች
  ባህሪ ማወቅ ደግሞ ሴትን ልጅ በምን መልኩ ለፍቅር ማቅረብ
  እንዳለብህ ያሳውቅህ፡፡


  2. የትላልቅ ቦታዎች ፍራቻ፡-
  ትልቅ ቦታ ለመግባት ማለትም ከሀብታም ሰዎች የመዝናኛ ቦታ
  ወይም ትላልቅ ሆቴሎች ገብቶ ለመዝናናት አንዱና ትልቁ
  ችግራቸው ነው፡፡ እነኚህ ወንዶች እንዴት ለብሰው መሄድና
  እንዴት መመገብ እንዳለባቸው አናውቅም ብለው በውስጣቸው
  ስለሚያስቡና ራሳቸውን ስለሚያሳንሱ በእንደዚህ አይነቱ ቦታ
  አይገኙም፡፡ ስለዚህ እነዚህ ሰዎች ከሰው ጋር ያላቸው ግንኙነት
  የተወሰነ ስለሚሆን ብዙ እውቀት (Information) ስለሌላቸው
  ብዙ አዝናኝ የሆነ ነገር ለሴቶች ለማቅረብ ያዳግታቸዋል፡፡
  ሴቶች ደግሞ ሁል ጊዜ ተመሳሳይ ቦታና ሁኔታን ስለሚጠሉ
  ከለመዱት ወጣ ባለ መልኩ ራሳቸውን የሚያሳድጉበትን ታላላቅ
  ነገሮችና መዝናኛዎችን ይመርጣሉ፡፡

  3. ሴቶችን በምን ዘዴ መቅረብ እንደሚቻል አለማወቅ፡-
  ብዙ ጊዜ ሴቶችን ለማጥመድ በሆነ ርዕስ ላይ አብረሃት
  እውቀትህን ለማሳየት ከመጽሐፍት ያነበብከውን ታካፍላታለህ፡፡
  ነገር ግን ከአንዲት ሴት ጋር የሆነ ትውስታን ሊጭር የሚችል
  ግንኙነት ካልፈጠርክ ከሰከንድ በኋላ ትረሳሃለች፡፡ ታዲያ ሴትን
  ልጅ በተለያዩ ዘዴዎች ልትቀርባትና ከቀረብካትም በኋላ ነገሯን
  አንበብህላት ታላቁን የጨዋታ ሚናህን ልትወጣ ይገባሃል፡፡
  ታዲያ በምትፈጥረው ድንቅ አጋጣሚዎች ሁሉ አንተነትህን ወደ
  ፍቅር ሰው የምትለውጥ አድርገህ አቅርበው፡፡ ጨዋታህ የፍቅር
  ምልክት ቢኖረውም ጠርሷ ላይና ጆሮዋ ላይ ብቻ የሚቀር
  ሳይሆን ጨዋታህ ሁሉ ፍቅርህን ልቧ ላይ የሚተክል መሆን
  እንዳለበት ራስህን አዘጋጅተህ ቀጥል፡፡ ለፍቅርህ እንቅፋት
  ከሚሆኑ ሰዎችም ራሳችሁን አርቁ፡፡ የማይመቹ ነገሮችን
  ትታችሁ ወደሚመቻችሁ ነገር ራሳችሁን አምጡት፡፡
  4. በመጀመሪያ ሴቶች ስትቀርብ ተለሳልሰህና በጥሩ ባህሪ
  ይሁን፡-
  የሚያስደስት ባህሪ ያለህ መስለህ መቅረብ ወይም በጣም ጥሩ
  የሚባል ወንድ ሆነህ ራስህን ማቅረብ ትልቅ ሚና
  ይጫወትልሀል፡፡ ይህንን ለቅርበት ብለህ በራስህ ላይ
  ያመጣኸውን ባህሪህን ትተህ ወደ እውነተኛ ባህሪህ እንዴት
  መመለስ እንደምትችል ወይም ጥሩ ባህርይ ተፈጥሯዊና
  ቀጣይነት ያለው ግን ፍቅርን የሚናገር መሆኑን ካላወቅህ
  ከሴቶች ጋር ሁሉ ጥሩ ሰው የሚባል ሰው ሆነህ ብቻ ከቀረብክ
  ያቺ ሴት እቤቷ ሄዳ ስለ አንተ ጥሩነት ብቻ ታወራለች፡፡ ነገር ግን
  እንደ አንድ ጥሩ ወንድምና ጓደኛዋ ብቻ ስለምትቆጥርህ ከሌላ
  ወንድጋር ሌላ የፍቅር ግንኙነት ትመሰርታለች፡፡ ስለዚህ ጥሩ
  ሰው ብቻ ሳትሆን ጥሩ የፈቅር ሰው ወይም የፍቅር አጋር
  መሆንም እንደምትችል ማሳየት አለብህ፡፡
  5. ሁል ጊዜ የሚያስደስታትን ነገር እወቅላት፡-ከምንም በላይ
  ሴቶች የውስጣቸውን ምቾት የሚጠብቅላቸውን ወንድ
  ያመቻቸዋል፡፡ ታዲያ ምን እንደሚያስደስታት ማወቅ የአንተ
  የወንዱ የቤት ስራ ይሆናል ማለት ነው፡፡ አስደስታት ምቾቷንም
  በሚገባ ጠብቅላት፡፡ ይህን እያደረክ ስትመጣ የበለጠ
  ግንኙነትህን አስደሳች ታደርገዋለህ፡፡ ምክንያቱም ስሜቷን
  ስትጠብቅላት ሁሌ አንተን ብቻ ትላለች፡፡ ያን ጊዜ ፈላጊና
  ተፈላጊ ተገጣጠሙ ማለት ነው፡፡


  6. የፍቅር ሰው መሆንህን አሳውቃት፡-
  በማንኛውም የግንኙነት አጋጣሚ ወንድሟን ወይም እህቷን
  ወይም እናቷን መስለህ ሳይሆን ፍቅረኛዋ እንደሆንክ መስለህ
  ወይም ሆነህ ቅረባት፡፡ ይህም ማለት እንክብካቤና የእናትነት
  አይነት ስሜት ከመጠን በላይ አታብዛባት፡፡ እንክብካቤህ
  በጥቂቱና በጥበብ ሆኖ ጨዋታዎችህ ግን ፍቅር ፍቅር
  የሚያሸትቱህ ሊሆን ይገባል፡፡ የብዙ ወንዶች ችግር ውስጣቸው
  ለፍቅር ከሚፈልጋት ሴት ጋር በጓደኝነት ቀርበው በኋላ ላይ ወደ
  ማንነታቸው መለወጥ ነው፡፡ ነገር ግን በየትኛውም አይነት
  አቀራረብ ቅረባት፡፡ ብዙ ጊዜ ሳትወስድ ግን አቀራረብህን ወደ
  ፍቅር ለውጠው፡፡ ጥሩ የፍቅር ሁኔታን ከሰጠኻትና ያንተ መሆን
  ከፈለገች እሷም ብዙ
  ብዙ ጊዜ ሳትወስድ ግን አቀራረብህን ወደ
  ፍቅር ለውጠው፡፡ ጥሩ የፍቅር ሁኔታን ከሰጠኻትና ያንተ መሆን
  ከፈለገች እሷም ብዙ ጊዜ አታባክንብህም፡፡ ያኔ ቅርርባችሁን
  ወደ ጣፋጭ የፍቅር ግንኙነት በቀላሉ መቀየር ትችላለህ፡፡


  7. አማላይነትህን ተጠቀምበት
  የራስህን ማንነት ከመጠበቅ ጀምሮ ጥሩ የሚባል ስብዕና ያለው
  ወንድ ሆነህ ቅረባት፡፡ ባገኘኸው አጋጣሚ አማላይ ሆነህ
  ቅረባት፡፡ በአንተ መልካምና አማላይ የሆነ አቀራረብ ውስጥ
  ለእሷም ጥሩ ነገር የምትፈጥርና የበለጠ አምራና ጎልታ
  እንድትወጣ ታደርጋታለህ፡፡ ምክንያቱም በእነዚህ ሁኔታዎች
  ውስጥ ከአንተ ጋር ተነፃፃሪ በሆነ መልኩ ራሷን አማላይና
  ማራኪ በሆነ መልኩ ለማቅረብ ስለምትጨናነቅ ነው፡፡ እነዚህንና
  መሰል ነገሮችን በሚኖራችሁ ቅርርብ ውስጥ የምትተገብራቸው
  ከሆነ ግንኙነታችሁ ጣፋጭና ድንቅ የፍቅር ጊዜ ይሆንላቸዋል፡፡
  ሰዓቶችና ቀናት ሁሉ ያጥራቸዋል፡፡ ያኔ የፍቅር መቀሶችህን
  ለይተህ በማወቅህ በፍቅር ቅመሞች የመለወጥና
  የግንኙነታችሁም ታላቅ የፍቅር ንጉስ የመሆን ዕድሉ ይኖርሀል፡፡
  አማላዬ የሚለውን ዜማም ጀባ በላት፡፡ እሷም አንተ የእኔ… የእኔ
  የነብሴ ክፋይ ትልሀለች፡፡

  ምንጭ: //www.mahderetena.com

   

  Read more »

 • በኦፕሬሽን መውለድ ጥቅሙና ጉዳቱ - Birth (C-Section and Normal Delivery)

                                                     

  (በሰብለወንጌል አይናለም)
  ህጻናት ይህችን ዓለም በሁለት መንገድ ይቀላቀላሉ፡­ በምጥ ወይም ደግሞ በኦፕሬሽን (surgical delivery by Caesarean section)፡፡ በአሁን ወቅት የህክምና አማራጭ ያላቸው እናቶች አምጦ ከመውለድ ይልቅ በኦፕሬሽን መውለድን እንደተሻለ አማራጭ ሲወስዱት ይታያል፡፡ አንዳንድ የህክምና ባለሙያዎችም በሁለቱም መንገድ መውለድ ያለውን ጠቀሜታና የጎንዮሽ ጉዳት አስረድተው ውሳኔውን ለእናቶች ከመተው ይልቅ በኦፕሬሽን እንዲወልዱ እናቶችን ሲገፋፉ ይታያል፡፡ ለመሆኑ በኦፕሬሽን መውለድ መቼ መፈቀድ አለበት? ያለው ጥቅምና ጉዳቱስ ምንድን ነው?
  በኦፕሬሽን መውለድ መቼ መወሰን አለበት?
  1. አምጦ መውለዱ ለእናትየው ወይም ደግሞ ለህፃኑ ህይወት አደጋ ሊያመጣ ይችላል ተብሎ ሲታመንበት
  2. ጽንሱ በጣም የፋፋ/የወፈረ/ ከሆነ እና የእናትየው ማህጸን ጠባብ ከሆነ 
  3. የጽንሱ አቀማመጥ በትክክል ካልሆነ ማለትም በእርግዝና የመጨረሻዎች ቀናት ጭንቅላቱ ወደታች ካልመጣ 
  4. በምጥ ወቅት ጽንሱ በቂ ኦክስጅን ካላገኘና የመተንፈስ ችግር ካጋጠመው 
  5. መንታና ከዚያ በላይ ጽንስ ሲኖር 
  6. የተራዘመ ምጥ ሲኖር እና 
  7. እናትየው ከፍተኛ የደም ግፊት ካለባት፤ የስኳር በሽተኛ ከሆነች፡ የHIV ቫይረስ ካለባት

  ጥቅሙ፡­

  በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ያሉ እናቶችን እና የጽንስን ህይወት ይታደጋል፡፡ እናቶች በምጥ ወቅት ሊሰማቸው የሚችለውን የተራዘመ ስቃይ ያስቀራል

  ጉዳቱ፡­

  1. ጽንሱን ለማውጣት የሚቀደደው የሰውነት ከፍል ለመዳን ጊዜ ይወስዳል፤ በሰውነት ላይ ጥሎት የሚያልፈው ጠባሳም በቀላሉ የሚድን አይደለም
  2. የእናቶችን የሆስፒታል ቆይታ ያራዝማል፡፡ በኦፕሬሽን የሚወልዱ እናቶች በፍጥነት አገግመው ልጆቻቸውን ለማጥባትም ሆነ ለመንከባከብ ይቸገራሉ
  3. የመጀመሪያ ልጃቸውን በኦፕሬሽን የወለዱ እናቶች ቀጣይ ልጆችን በተመሳሳይ ሂደት እንዲወልዱ ሊገደዱ ይችላሉ፡፡ ይህም በማህጸን ግድግዳ ላይ ተደጋጋሚ ጠባሳዎች ያስከትላል፤ ቁስሉ በቶሎ ካልዳነ ደግሞ የማህጸን ግድግዳ ከሌላ የሰውነት ከፍል ጋር ሊጣበቅ ይችላል 
  4. በምጥ ከሚወልዱ እናቶች ይልቅ በኦፕሬሽን የሚወልዱ እናቶች ለከፍተኛ ደም መፍሰስና እንፌክሽን ይጋለጣሉ፡፡ በኦፕሬሽን የሚወልዱ እናቶች በምጥ ከሚወልዱ እናቶች የመሞት ዕድላቸው ሶስት አጥፍ የሰፋ ነው
  5. በኦፕሬሽን ሂደት ውስጥ የሽንትና የሰገራ ማስተላለፊያ ቱቦዎች ሊጎዱ ይችላሉ
  ስለዚህ አስገዳጅ ሁኔታ ካልተፈጠረ በቀር እናቶች አምጠው መውለድን ቢመርጡ ይመከራል፡፡ አምጠው የሚወልዱ እናቶችም የተሻለ የመንፈስ እርካታ እንዳለቸው ይናገራሉ፡፡

  ምንጭ፡- ጤና

  Read more »

 • ሊያገቡት የሚፈልጉትን ሁነኛ ሰው ማግኘትዎን የሚያሳዩ 10 ምልክቶች!

    

   

   

  በሳሙኤል ዳኛቸው

  ከፍቅረኛዎ ጋር የፍቅር ግንኙነት ከጀመሩ ዋል አደር ብለዋል እንበል፤ በተደጋጋሚ የሚነሳብዎት ጥያቄም መቼ ነው እናንተ የምትጋቡት? የሚለው ሊሆን ይችላል።

  ይሁንና መሰል ጥያቄዎች ሲደጋገሙ ምቾትን ሊነሱ እና ስጋትንም ሊደቅኑብዎት የሚችሉበት ዕድልም ሰፊ ነው።

  ታዲያ ጋብቻ ትልቅ ውሳኔን የሚጠይቅ እንደመሆኑ ሊያገቡት የሚፈልጉትን ሰው ማግኘትዎን የሚያረጋግጡልዎን ነጥቦች እንካችሁ የሚለው ደግሞ ሰልፍ ዶት ኮም የተሰኘው ድረ ገፅ ነው።

  1.ስለምንም ነገር ሲያወሩ ምቾት ይሰማዎታል፦

  ከፍቅር ጓደኛዎ ጋር የትኛውንም አይነት ርዕስ አንስተው ከመወያየት ወደኋላ አይሉም ፣ ሲወያዩ ምቾት ይሰማዎታል።

  ስጋትዎን፣ ግምትዎን ውጥንዎንም ሆና ሌላውን ከመግለፅ አያመነቱም፤ ይህን በማለቴ ትዝብት ላይ እወድቅ ይሆን የሚለው ፍራቻም ከአጠገብዎ ዝር አይልም።

  2. ስለምንም ጉዳይ በቅድሚያ ለማዋየት ይደፍራሉ፦

  ከመስሪያ ቤትዎ ያገኙትን የስራ ዕድገትንም ሆነ ስለፍላጎትዎ፣ ስለገጠመዎ ችግርም ሆነ መልካመ አጋጣሚ ለማውጋት በመጀመሪያ የሚመርጡት ለፍቅረኛዎ ይሆናል።

  3.ብዙ ጊዜዎን ከፍቅረኛዎ ጋር ማሳለፍን ይመርጣሉ፦

  ከፍቅረኛዎ ጋር ሰፊውን ጊዜዎን እንደማሳለፍ የሚያረካዎት ነገርን ያጣሉ።

  አብሮነታችሁንም ሁሌም ቢሆን ይመኙታል።

  ቲያትርም ሆነ ሲኒማ ቤት መሄድ ፣ በቤትዎ ቴሌቭዥን መመልከትም ሆነ የእግር ጉዞ ማድረግ ፣ ጨረቃ ማየትም ሆነ ሌላ ሌላ ነገር ለማድረግ ምርጫዎ አሁንም ፍቅረኛዎ ይሆናል።

  4.ይከባበራሉ ፣ ይደጋገፋሉ፦

  ድካምዎን ለሌላ ሰው አይነግሩም ፍቅረኛዎም ቢሆን ይህንኑ በእርስዎ ላይ ለማድረግ አቅሙ አይኖራቸውም።

  ዝንባሌያቸውን፣ ምን እንደሚያስደስታቸው ምን እንደሚያስከፋቸው ያውቃሉ፤ በመሆኑም አንዳያዝኑብዎ ይጠነቀቁላቸዋል።

  ያከብሯቸዋል፣ ይታመኑላቸዋል፣ ከአጠገብዎ በስራም ሆና በሌላ ምክንያት ሲርቁም ናፍቆትዎን መቋቋም ሲሳንዎ ራስዎን ያገኙታል።

  5.ወደፊት አብረው እንዴት እንደሚዘልቁ ያነሳሉ፦

  ወደፊት ግንኙነትዎ በእንዴት ባለ ሁኔታ መቀጠል እንደሚኖርበት ያለ ፍርሃት ይገልፃሉ።

  ምናልባትም ለመጋባት እንደሚያስቡ እና ይህም በምን ያህል ጊዜ ቢከናወን ምርጫዎ እንደሆነም ከመናገር ወደኋላ አይሉም ነው የተባለው።

  6.የፍቅር ጓደኛዎ ከእነጉድለትዎ ሊቀበሉዎ ዝግጁ ናቸው፦

  የፍቅር አጋረዎ በጥንካሬዎ ብቻ ሳይሆን ደካማ ጎንዎን አውቀው ያን በሂደት እንደሚቀርፉት በማመን ጭምር ነው ግንኙነታቸውን ከእርስዎ ጋር የሚወጥኑት።

  ፍቅረኛዎ እርስዎን ባለዎት ሃብት እና ንብረት ሳይሆን የሚመዝኑዎት በአመለካከትዎ እና ለሴቶች በሚሰጡት ከበሬታ ይሆናል።

  7.ፍቅረኛዎ ከቀድሞ የፍቅር ህይወታቸው መላቀቃቸው ያስታውቃል፦

  ፍቅረኛዎ የቀድሞ የፍቅር ህይወታቸውን የረሱ እና ለአዲስ ፍቅር የተዘጋጁ መሆናቸውን የሚያረጋግጡ አካላዊ፣ ስነ ልቦናዊ ዝግጁነቶችን ያነቡባቸዋል።

  8.ለፍቅር ግንኙነት መፈላለጋችሁ ያሳብቅባችኋል፦

  ምንም እንኳን ለፍቅረኛዎ ካለዎ ከበሬታ የተነሳ የተቃራኒ ፆታ ግንኙነትን ከጋበቻ በፊት መፈፀሙ ባይዋጥልዎም ለፍቅር ግንኙነት የሚፈልጉት (ጓት) አይነት ሰው መሆናቸውን አይን ለአይን ስትጋጩ አልያም የመደንገጥ ስሜት ድንገት ሲሰማዎት ራስዎን ያገኙታል።

  9.ግጭቶችን ጤናማ በሆነ መንገድ ለመፍታት ያለ ዝግጁነት፦

  የትኛውም አይነት የሃሳብ ግጭት ሲፈጠር በሰከነ እና በሰለጠነ መንገድ በመወያያት ለመፍታት እርጋታ እና ፍላጎት ይኖርዎታል።

  ኩርፊያንም ሆነ ግጭትን በአጭሩ ለመቅጨት ወኔውንም ሆነ ትዕግስተ እንዳለዎት በተለያየ መንገድ ያረጋግጣሉ።

  10. ፍቅረኛዎ ይሰሙዎታል፦

  ፍቅረኛዎ እርስዎ ሲናገሩ በፍላጎት እና በትዕግስት ማድመጥ ምርጫቸው ነው።

  ለፍቅረኛዎ ሊሰጡት የሚችሉት ትልቁ ቦታም ማድመጥ መሆኑን እርስዎም በሚገባ ይገነዘባሉ።

  በዚህም ምክንያት ለመስማት ብዙ ጊዜዎን ለመናገር ደግሞ ጥቂቱን ይጠቀማሉ።

  ምንጭ: ማህደረ ጤና ዶት ኮም

   

  Read more »

 • ለከፍተኛ ራስ ምታት (ለማይግሪን) የሚያጋልጡ ምግቦች

   

   የምንመገባቸው ምግቦችና መጠጦች ለከፍተኛ ራስ ምታት (ማይግሪን) መንስኤ ሊሆኑ ይችላሉ። በራስ ምታት የመያዝ አጋጣሚዎች በተለያዩ ምክንያቶች (በአየር ፀባይ መለዋወጥ፣ በጠንካራ ሽታዎች፣ በከፍተኛ ብርሃን፣ በሌሎች በሽታዎች ሳቢያ፣ በካፌይን ሱሰኝነት ወዘተ) የሚያጋጥመን ቢሆንም የምንመገባቸው ምግቦችና ወደ አንጀታችን የምንልካቸው የተለያዩ መጠጦችም ለከፍተኛው ራስ ምታት (ማይግሪን) ሊያጋልጡን እንደሚችሉ የአሜሪካ ተመራማሪዎች አስታውቀዋል፡፡ ኔቸር በተሰኘው የምርምር ጆርናል ላይ ተመራማሪዎቹ ይፋ እንዳደረጉት፤የምንመገባቸው ምግቦች ከጭንቅላት ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት ያላቸው ታይራሚንስና ናይትሪ የተባሉ ኬሚካሎችን በስፋት ይይዛሉ፡፡ እነዚህ ኬሚካሎች ደግሞ የደም ዝውውር ሂደትን በማወክ፣ የራስ ምታትንና የዓይን አካባቢ ህመምን ያስከትላሉ፡፡

  ሣይንቲስቶቹ በምርምር አረጋግጠናል ካሏቸውና ከፍተኛ የራስ ምታትን ያስከትላሉ በማለት ከዘርዘሯቸው የምግብና የመጠጥ ዓይነቶች መካከል የሚከተሉት ይገኙበታል፡፡
  ቀይ የወይን ጠጅ
  ቀይ ወይን ለራስ ምታት ህመም የሚያጋልጡ ኮንጀነርስና ታይራሚን የተባሉ ንጥረነገሮችን በብዛት ይይዛል፡፡ ስለዚህም ከሌሎች አልኮል መጠጦች ሁሉ የራስ ምታት ህመምን በማነሳሳት በእጅጉ ይታወቃል። የችግሩ ከፍተኛነት በወሰድነው የቀይ ወይን መጠንና በሽታን በመከላከል አቅማችን የሚወሰን ቢሆንም ቀይ ወይን መጠጣት ለከባድ የራስ ምታት ህመም የሚያጋልጥ መሆኑን አረጋግጠናል ሲሉ ተመራማሪዎቹ ገልፀዋል፡፡ ቀይ ወይን ለራስ ምታት ህመም እንድንጋለጥ የሚያደርገን በአልኮልነቱ ሳይሆን በነጭ ወይን ውስጥ የሌለና በቀይ ወይን ውስጥ ብቻ በሚገኘው ተፈጥሮአዊ ውህድ መነሻነት እንደሆነም እነዚሁ ተመራማሪዎች ጠቁመዋል፡፡
  ቸኮሌት
  ቸኮሌትን አብዝቶ መመገብ ለከፍተኛ ራስ ምታት ያጋልጣል፡፡ በተለይም ጠቆር ያለውና ቡናማ ቀለም ያለው የቸኮሌት አይነት ህመሙን በማባባስ ለከፍተኛ ስቃይ የሚዳርግ መሆኑን የጠቆሙት ተመራማሪዎቹ፤ ከካካዋ ቅቤ የሚሰራው ነጭ ቸኮሌት ከራስ ምታት ህመም ጋር የሚያገናኘው ምንም ነገር አለመኖሩን በጥናታቸው ማረጋገጣቸውን ገልፀዋል፡፡
  አይስክሬምና ሌሎች ቀዝቃዛ ምግቦች
  እንደ አይስክሬም ያሉ በጣም የቀዘቀዙ ምግቦችን በምንመገብበት ወቅት በአፋችን ውስጥ የሚፈጠረው ከፍተኛ ቅዝቃዜ ለከባድ ራስ ምታት ያጋልጠናል፡፡ ለዚህም ምክንያቱ በአፋችን ውስጥ የተፈጠረው ቅዝቃዜ እስከ ጭንቅላታችን ድረስ ስለሚሰማን እንደሆነም አሜሪካዊያን ተመራማሪዎቹ ጠቁመዋል፡፡
  ካፌን
  ቡና እና ኮካ መሰል መጠጦች ውስጥ የሚገኘው ካፌን ሱስ የማስያዝ ባህርይ አለው። ይህንን መጠጣት በምናቆምበት ወይንም ሳንጠጣ በምንቆይበት ጊዜ ከባድ የራስ ምታት ህመም ያጋጥመናል፡፡ ካፌይን መውሰድ ያቆሙ ሱሰኞች ለድብርት ስሜት፣ ለመጫጫንና ለከባድ ራስ ምታት ህመም የተጋለጡ ናቸው፡፡ ካፌይኑ የአንጐላችንን ኤሌክትሪካል ሲስተም በማዛባት ሰውነታችን ተጨማሪ የቤታ ንዝረቶችንና አነስተኛ የቴታ ንዝረቶችን እንዲለቅ ያደርገዋል፡፡ ይህ ደግሞ በአንጐላችን ውስጥ የሚካሄደውን ኤሌክትሪካል እንቅስቃሴ በማዛባት ለከፍተኛ የራስ ምታት ህመም እንድንጋለጥ ያደርገናል፡፡
  ካፌይን ነክ የሆነ መጠጦችን በጠዋት የመጠጣት ልምድ ያላቸው ሰዎች ካፌይኑ በሕብለ ሰረሰራቸው ውስጥ የሚገኙትን የደምቅዳ ቧንቧዎች በማጥበብ ደም በበቂ መጠን ወደ አንጐል እንዳይገባ ያደርጋል። በዚህ ሣቢያም ከባድ የራስ ምታት ህመም ያጋጥመናል ሲል ተመራማሪዎቹን ዋቢ አድርጐ ኔቸር ዘግቧል፡፡

  ምንጭ – አዲስ አድማስ & www.mahderetena.com/

  Read more »

 • የፀጉር መሳሳትን ለመከላከል እና ፀጉራችን ተጨማሪ እድገት እንዲኖረው በቤት ውስጥ የሚዘጋጁ መድሃኒቶች

                                                       

  1. የቀይ ሽንኩርት ጭማቂ፦ ሽንኩርት ከምግብነት ባለፈ ፀጉራችን እንዲበዛ እና እንዲያድግ የማደርግ ጠቀሜታ አለው።

  ይህም በውስጡ ባለው ሰልፈር አካማኝነት ፀጉር እንዲያድግ ስለሚያደርግ ነው።

  አዘገጃጀት፦

  ብዛታቸው ከሁለት እስከ አራት የሚሆን ቀይ ሸንኩርት ከላጥን በኋላ ሽንኩርቱን በመጭመቅ ጭማቂውን ማውጣት።

  ያዘጋጀነውን የሽንኩርት ጭማቂ የጸጉራችን ስር ላይ በመቀባት ማሻሸት።

  የሽንኩርቱን ጨማቂ ተቀብተን ከ15 ደቂቃ እስከ አንድ ሰዓት ማቆየት።

  ከዚያም ፀጉራችንን በንጹህ ውሃ እና በጸፀር ሻምፖ ወይንም ሳሙና መታጠብ።

  ለጸጉራችን እድገት ቀይ ሽንኩርትን ለመጠቀም የሚያስችሉን ተጨማሪ አዘገጃጀት፦

  አራት ወይንም አምስት ራስ ሽንኩት ልጠን መክተፍ።

  አንድ ሊትር ውሃ ማፍላት።

  የተከተፈውን ሸንኩርት በፈላው ውሃ ውስጥ በመጨመር አንድ ላይ ከአምስት እስክ አስር ደቂቃ ድረስ እንዲፈላ ማድረግ።

  ያፈላነውን ሽንኩርት ለብ እንዲል ማድረግ።

  ፀጉራችንን በሻምፖ ከታጠብን በኋላ ባፈላነው የሽንኩርት ውሃ መታጠብ።

  ሽንኩርቱ የሚፈጥረውን ሽታ መቋቋም ከቻልን ለአንድ ቀን በጸጉራችን ላይ የጨመርነውን የፈላ የሽንኩርት ውሃ ሳንታጠብ ብንውል ይመከራል ይህን ማድረግ የማንችል ግን ቢያንስ ለ15 ደቂቃ ያህል እንዲቆይ በማድረግ መታጠብ።

  ሽንኩርት ጸጉራችን እንዲያምር ብቻ ሳይሆን የተነቃቀሉ ፀጉሮችም እንደገና እንዲበቅሉ እና እንዲያድጉ ያደርጋል።

  2. የድንች ጭማቂ፦ የድንች ጭማቂ ሌላኛው በቀላሉ በቤት ውስጥ በማዘጋጀት ፀጉራችን እንዲያድግ የሚረዳን መድሃኒት ነው።
  ድንች ውስጡ ቪታሚን “ኤ”፣ “ቢ” እና “ሲ” ስላለው ለፀጉራችን እድገት ተመራጨ ያደርገዋል።

  አዘገጃጀት፦

  ሶስት ወይንም አራት ራሰስ ድንች ከላጥን በኋላ በመጭመቅ ጭማቂውን ለብቻ ማውጣት።

  የድንቹን ጭማቂ የፀጉራችን ስር በመቀባተ ማሸት ከዚያ በኋላ ሳናጥበው ቢያንሰ ለ15 ደቂቃ ካቆየን በኋላ በንጹህ ውሃ መታጠብ።

  በተጨማሪም የድንች ጭማቂውን ለማዘጋጀት የሚያግዙን ዘዴዎች፦

  የሚያስፈልጉ ቁሳቁሶች፦ ሶስት ራስ ድንች፣ የአንድ እንቁላል አስኳል እና አንድ የሻይ ማንኪያ ማር።
  አዘገጃጀት

  ድንቹን በመጭመቅ ጭማቂውን ማዘጋጀት፣ የእንቁላል አስኳሉን እና ማሩን በድንች ጭማቂው ውስጥ በመጨመር በድንብ ማዋሃድ።

  ውህዱን በፀጉራችን ስር ላይ በመቀባት ለግማሽ ሰዓት ያህል ማቆየት።

  ንጹህ ውሃ እና ሻምፖ በመጠቀም የድንች ጭማቂውን መታጠብ

  ማር እና እንቁላልን በድንች ጭማቂ ላይ ደባልቆ መጠቀም ጸጉራችን እንዲያድግ ከማድረግ በተጨማሪ የጸጉር ድርቀትንም ይከላከላል።

  ምንጭ:- FBC(ኤፍ.ቢ.ሲ)

  Read more »

 • የሴትን ልጅ ልብ ለመማረክ እና ቀጣይነት ያለው ግንኙነት ለመመስረት የሚረዱ 6 ነጥቦች (በወንዶች መነበብ የሚገባው የፍቅር ግንኙነትን በተመለክተ የሴቶችን ባሕሪ የሚገልጽ መካሪ ርዕሰ ትምህርት)

  ሴቶች በፍቅር ውስጥ አጥብቀው የሚፈልጉት ምንድነው?

  በጥንዶች መካከል ለሚኖር የተሳካ የፍቅር ግንኙነት የፍላጎት መጣጣም እጅግ አስፈላጊ መሆኑ አጠያያቂ አይደለም፡፡ በዚህ ረገድ የሰው ልጆች በአጠቃላይ፣ ተመሳሳይ የሚመስል መሰረታዊ ፍላጎቶች ቢኖራቸውም ወንዶችና ሴቶች በየግል ከፍተኛ ቦታ የሚሰጧቸው የተለያዩ የስሜት ፍላጎቶች ይኖሯቸዋል፡፡
  በግንኙነት መስክ ውስጥ ከምንጠቀምባቸው ክህሎቶች ሁሉ የመጀመሪያውና ጠቃሚ ነገር፣ የተጓዳኛችንን ጥልቅ ፍላጎት እና ተግባራት አስቀድሞ መረዳት ሲሆን፣ ይህ ማስተዋል አብሮን ያለውን ሰው ጠንቅቀን እንድንረዳ ስለሚያግዘን ችግሮች ከመሰከታቸው በፊት እንድንታደጋቸው ብሎም ከተፈጠሩ በኋላ በንቃት እና በጥበብ መለስ እንድንል ይረዳናል፡፡ አንዳንድ ጊዜ የሰዎችን መሻት ሳይነግሩን የማወቅ ክህሎትን መማርና መለማመድ፣ አታካችና አድካሚ ቢመስልም ውጤቱ ግን እጅግ አመርቂ እንደሚሆን አያጠያይቅም፡፡ አብዛኛውን ጊዜ በጥንዶች መካከል ተቀራርቦ ፍላጎቶችን ማውራት፣ ስሜትን መጋራትና ምክንያትን መግለጽ፣ የተሻለ ቅርርቦሽን በመፍጠር በትዳር ላይ መተማመንን ስለሚጨምር መልካም የሚባል ውጤትን ሊያስገኝልን ይችላል፡፡

  ብዙውን ጊዜ ሰዎች ጥምረት የሚገቡት በዘርፉ በቂ የሚባል ዝግጅት ሳይኖራቸው እንደሆነ በተደጋጋሚ በዚህ አምድ ላይ የተነሳ ጉዳይ ነው፡፡ ይህም ትዳርን ውስብስብ እና አታካች እያደረገ መጥቷል፡፡ ከስልጣኔ ጋር ተያይዞ የመጣውም የሰው ልጅ ፍላጎት መጨመርና በትንሽ ነገር ያለመርካት አባዜ፣ በትዳር ውስጥ ተስፋ መቁረጥ የራሱን የሆነ ሚና ይጫወታል፡፡
  በአንድ ወቅት ኖራ ሃይደን የተባለች የማህበራዊ ህይወት ተመራማሪ በመጽሐፏ እንዳለችው፣ አብዛኛው ወንዶች ስለ ሴቶች ያላቸው አተያይ እጅግ አስደንጋጭ ነበር፡፡ በወንዶች ዓይን ሴቶች ማለት፣ በዚህች ምድር ላይ ካሉ ነገሮች ሁሉ በላቀ ደረጃ እጅግ ውስብስብና፣ ፍላጎታቸው የማይታወቅ በቀላሉ የማይረኩ ፍጡሮች እንደሆኑ ይገልፃሉ፡፡
  በዚሁ ጥናት ላይ የሴትን ልጅ ፍላጎት ከመረዳትና፣ ሴትን ልጅ ደስተኛ ከማድረግ ይልቅ (ኑዩክለር ፊዚክስ ማጥናት እንደሚቀል ገልጧል)
  ይህ በእውነቱ ከእውነታው ጋር እጅግ የሚጣረስና ለሴቶች እጅግ አስደንጋጭ ጉዳይ ነው፡፡ ይህ እሳቤ የሚመነጨው ሁላችንም በራሳችን ግለኛ ዓለም ውስጥ ተከልለን የራሳችንን ተፈጥሮና ፍላጎት ብቻ ስለምናዳምጥና የሌሎችን ማንነት ለማወቅና ተጣጥሞ ለመኖር ምንም አይነት ጥረት ስለማናደርግ ይመስለኛል፡፡
  በተለያየ ጊዜ በዘርፉ የተሰማሩ ባለሙያዎች፣ ስለወንዶችና ሴቶች ረቂቅ ባህሪያትና ፍላጎት ለማወቅ በርካታ ጥናቶችን አካሂደዋል፡፡ ከእነዚህ ጥናቶች የተውጣጣውን መደምደሚያ መሰረት በማድረግ ከ90 በመቶ በላይ የሚሆኑት ሴቶች የሚስማሙበትንና፣ ሴቶች ከትዳር አጋራቸው ወይም ፍቅረኛቸው አጥብቀው የሚሹትን 6 ነጥቦችን ከሀገራችን ነባራዊ ሁኔታ ጋር በማጣጣም ላካፍላችሁ ወደድኩ፡፡

  የሴትን ልጅ ልብ ለመማረክ እና ቀጣይነት ያለው ግንኙነት ለመመስረት የሚረዱ 6 ነጥቦች
  1.(Caring) እንክብካቤ
  በጥናቱ ውስጥ ከተካተቱ አብዛኛዎቹ ሴቶች በፍቅር ለሚንከባከብ ወንድ በቀላሉ እንደሚሸነፉ ገልፀዋል፡፡ ይህም የሚሆነው ሴቶች በተፈጥሮ ካላቸው የእንስትነት ባህሪ የተነሳ ከወንዶች ስሜት እና ፍቅርን ብቻ ሳይሀን፣ ከለላን፣ አለኝታነትን እና እክብካቤን አጥብቀው እንደሚሹ ተናግረዋል፡፡ ይሄም ምኞት እና ደህንነት እንዲሰማው ስለሚያደርግ ህይወትን ለቀቅ አድርገው በመመልከት የበለጠ ደስተኛ ያደርጋቸዋል፡፡

  2. ትኩረት
  ይሄንን ፍላጎት በሁለት ከፍለን ልናየው እንችላለን፡፡
  2.1 መደመጥ
  Joeu Barton የተባለ የስርዓተ ፆታ ተመራማሪ በጥናቱ ላይ እንዳሰፈረው፣ ሴቶች በቀን ውስጥ በአማካኝ 20,000 ቃላቶችን ሲጠቀሙ፣ በተቃራኒው ወንዶች ደግሞ 7,000 ቃላትን በመጠቀም ሀሳባቸውን ያስረዳሉ፡፡ ይህም በግልፅ እንደሚያስረዳን አንደኛ ሴቶች ለቋንቋ እና ለንግግር ፈጣን የሆነ አዕምሮ እንዳላቸው ሲሆን፣ ሌላው እና ትኩረት ሊሰጠው የሚገባው ጉዳይ፣ ሴቶች በንግግር ራሳቸውን በመግለፅ የበለጠ ነፃነት እንደሚሰማቸው ሲሆን ችግር በገጠማቸውና በጨነቃቸውም ጊዜ በማውራት ብቻ ያለ ምንም ተጨማሪ ምክርና መፍትሄ የተሻለ እፎይታና እረፍት እንደሚሰማቸው ሲሆን፣ በዚህም ጊዜ ንግግራቸውን በትኩረት ለሚያዳምጣቸው ወንድ የተለየ ፍቅርና አክብሮት ይኖራቸዋል፡፡
  2.2 አንዲሰት ሴት አብሯት ካለ ወንድ ከፍቅርና እንክብካቤ ባሻገር አትኩሮ ትሻለች
  በርካታ የህይወት ተሞክሮዎች እንደሚያመለክቱት፣ ሰዎች በተሰበሰቡበት ግብዣ ላይ አንድ ወንድ ፍቅረኛውን ወይም የትዳር አጋሩን ከሰዎች ጋር በሚኖረው ጨዋታ እጇን በማሻሸት ወይም በመሳም፣ አብሮነቱን ቢያረጋግጥላት በቀላሉ ልቧን በፍቅር በማቅለጥ የጥሩ ስሜት ባለቤት እንድትሆን እንደሚረዳ ይታመናል፡፡ አብዛኛውን ጊዜ ወንዶች በግንኙነት ውስጥ የሚመለከቱት፣ ትልቁን ምስል ብቻ በመሆኑ አብሮነት በራሱ በቂ ነው ብለው ሊያስቡ ይችላሉ፡፡ ሴቶች ደግሞ ባላቸው የተለያየ አፈጣጠር ዝርዝር ነገሮች ላይ ትኩረት ስለሚያደርጉ እያንዳንዱን እንቅስቃሴና ፍሰት ይከታተላሉ፡፡ በመሆኑም ወንዶች ፍቅረኛቸው ወይም የትዳር አጋራቸውን ከመነፈጠሯም ረስተው ለረጅም ሰዓት ከሶስተኛ ወገን ጋር ጨዋታ ውስጥ ሊገቡ ይችላሉ፡፡ ይህ በሴቶች አዕምሮ ውስጥ የመተውና አትኩሮት የማጣት ስሜትን ሊያጭር ስለሚችል ወንዶች ትኩረት ሊያደርጉበት ይገባል፡፡ ይሄንን በጣም ቀላል ግን ከፍተኛ ተፅዕኖ ሊፈጥር የሚችል እውነታ በመረዳት፣ በሄዳችሁበት ሁሉ ለሴቶቻችሁ አብሮነት ትኩረትና ዕውቅናን በመስጠት፣ ስሜታቸውን ከመጉዳት ብትታደጉ በምላሹ ፍቅር እና አድናቆትን ትቀበላላችሁ፡፡
  እዚህ ጋ ልብ ልንለው የሚገባው እውነታ፣ ይህ ዓለም መስጠትንና መቀበልን መሰረት ያደረገ ነው፡፡ የሰውን ስሜት ጎድቶ መልካም የስሜት ምላሽ መጠበቅ የዋህነት ስለሆነ፣ የምንፈልገውን ለማግኘት የሚፈለገውን መስጠት ግድ ይለናል፡፡

  3. (Security) ጥበቃ
  ከጥንት ጀምሮ ሲወርድ ሲዋረድ የመጣው፣ የወንድ ልጅ ከለላ እና መጋ መሆን፣ አሁንም ድረስ በብዙዎች ዘንድ ተቀባይነት ያለው እውነታ ነው፡፡ በዚህ በሰለጠነው እና የሴቶች እኩልነት በተረጋገጠበት 21ኛው ክፍለ ዘመን እንኳን፣ ሴት ልጅ በግሏ ገቢ በማስገኘት ሀብት ማካበት ብትጀምርም፣ የወንድ ልጅ ግብአት አቅራቢ እና ጠባቂ መሆን የሴትን ልጅ ስሜት ለማረጋጋት በጣም አስፈላጊ ነው፡፡ ከዚህም በዘለለ ወንድ ልጅ ለሴት ከተለያየ አደጋ ጠባቂ ሆኖ መገኘቱ፣ እምነቷን የበለጠ ስለሚያጠነክረው ፍቅሯ እየጎለበተ ይሄዳል፡፡

  4. Blind Loyalty (ፍፁም የሆነ ተአማኒነት)
  በአብዛኛው አንዲት ሴት የፍቅር ግንኙነት ውስጥ ስትሆን ወይም በወንድ ስትፈቀር ራሷን የተለየች ፍጡር አድርጋ እንድታይ ትሆናለች፡፡ ይህም ምን አልባት ከሴቶች ተፈጥሮ በተጨማሪ ወንዶች በፍቅር መብረቅ በተመቱ ጊዜ ያፈቀሯትን ሴት የግላቸው ለማድረግ የሚጠቀሙበት ገደብ የለሽ ሙገሳና ማሞካሸት፣ ሴቶች ለራሳቸው ያላቸውን አመለካከት በማዛባት፣ ውጫዊ መስህብን እንደ ብቸኛ የማንነታቸው መለኪያ አድርገው እንዲወስዱት ሳያስገድዳቸው አልቀረም፡፡
  በመሆኑም በግንኙነት ውስጥ አንዲት ሴት የራሷን የመስህብ ደረጃ ጠንቅቃ ብታውቅም ባፈቀራት ወንድ እይታ ስትፈረጅ ‹‹ሁሉን ያስናቀች ቆንጆና ፀባየ ሰናይ መሆኗን እንዲነገራት ትፈልጋለች›› በማንኛውም አጋጣሚ የእሷ ወንድ የሌላዋን ቆንጆ አለባበስ ወይም አቋም ቢያደንቅ እሷን የወሰደባት ያህል ስለሚሰማት መጠንቀቅ ያስፈልጋል፡፡ በመሆኑም የሰውን ቆንጆ በመቃረም፣ የትዳር አጋራችንን ስሜት ከምንጎዳ፣ ያገባናትን ሴት በትዳር አብረን እንድንኖር ውሳኔ ላይ ያደረሰንን መልካም ሰብዕና፣ ውበት፣ ወይም ተግባር በማስታወስ ከልብ የመነጨ አድናቆታችንን እና ሙገሳችንን መቸርን ብንለማመድ፣ ለትዳራችን ዕድሜ ማራዘሚያነት እንደሚጠቅም ጥናቶች እና ተሞክሮዎች ያመለክታሉ፡፡

  5. Understanding (መረዳት)
  በርካታ ሴቶች ከተጓዳኛቸው አጥብቀው የሚፈልጉት ተጨማሪው ነገር፣ የትዳር አጋራቸው የእነሱን ሚና እና በቤት ውስጥ ያላቸውን አስተዋፅ እንዲረዳ እና ዕውቅና እንዲሰጥ ነው፡፡ አንዳንድ ወንዶች ሴት ልጅ በቤት ውስጥ የምታከናውናቸውን ረቂቅና እጅግ ወሳኝ ተግባራት ባለማወቅ ዕውቅናን ሲነፍጉ ይስተዋላሉ፡፡ የሴት ልጅ ተፈጥሮ ማለትም በሴትነት የምታልፋቸውን ከባባድ ደረጃዎች፣ እርግዝና፣ ወሊድ፣ ማጥባት እና ልጅን መንከባከብ በምድራችን ካለ ነገር ሁሉ እጅግ ውድ፣ ፈታኝ እና ዋጋ ሊተመንለት የማይችል መሆኑን በመረዳት፣ ሴት ሆነው ያንን መክፈል እንኳን ባይችሉ፣ ክብደቱን በመረዳት እና ርህራሄ በማሳየት ሊያዝኑላቸው፣ ሊንከባከቧቸው እና ሊደግፏቸው ይገባል፡፡ ይሄም በሴት ልጅ ልቦና ውስጥ እስከ መጨረሻው ለመቀመጥ ጥርጊያ መንገድ ይሆናል፡፡

  6. Sex (ወሲብ)
  በተጣማሪዎች መካከል ፍቅር ሰምሮ ኑሮ እንዲደረጅ፣ በሐሳብ እና ፍላጎት መጣጣም ተቀዳሚው መሆኑ የማያጠያይቅ ሀቅ ነው፡፡ መከባበሩ፣ መፈቃቀሩና የሐሳብ መጣጣሙ እንደተጠበቀ ሆኖ በወሲብ አለመጣጣም ባለትዳሮች ከትዳራቸው ውጪ ሌላ ሰው መጎብኘታቸው የተለመደ ተግባር እየሆነ መጥቷል፡፡
  ብዙውን ጊዜ ተጣማሪዎች፣ የሐሳብ አለመጣጣምን አቻችለውና ተቻችለው ኑሮን ሲገፉ ይስተዋላል፡፡ በአሁኑ ዘመን እየተስተዋለ የመጣው እውነታ እንደሚያመለክተን ግን በወሲብ አለመጣጣምን ማስታመም ስለሚያቅታቸው ወይም ከሌላ ጋ ሲማግጡ ወይም ከነጭራሹ ትዳርን ሲያፈርሱ ይታያሉ፡፡
  በአብዛኛው በርካታ ወሲብ ነክ ፅሑፎችና ጥናቶች አንድን ወንድ እንዴት ለወሲብ ማነሳሳት እንዳለብን እና እንዴት እርካታ ላይ እንዲደርስ መርዳት እንዳለብን የሚገልፁ ናቸው፡፡ ይህም የሚያሳየው የሴት ልጅ ስሜት ይሄ ነው የሚባል አትኩሮት ከማህበረሰቡ ጭምር እንዳልተቸገረው ነው፡፡
  Nora Hayden (How to satisfy a women every time) በተሰኘው መጽሐፏ ላይ እንደገለፀችው 80% የሚሆኑት ሴቶች፣ እውነተኛ እርካታ ላይ እንደሚደርሱ ሆኖም የትዳር አጋራቸውን ለማስደሰት ሲሉ ብቻ እርካታ ላይ እንደደረሱ እንደሚያስመስሉ ይናገራሉ፡፡ ይህም የሚሆነው ወንዶች በወሲብ ጊዜ የሴትን ልጅ ፍላጎት እና የስሜት ምስጢር መረዳት ስለሚያቅታቸው እነሱ በሚረኩበት መንገድ ይረካሉ ብለው በማሰብ ዘልማዳዊ የሆነውን ግንኙነት ያደርጋሉ፡፡ ሆኖም ፈጣሪ ወሲብን በትዳር መካከል እንድትደሰትበትና ትውልድን እንድናስቀጥልበት የሰጠን ታላቅ ፀጋ በመሆኑ፣ የሴትም ልጅ ስሜት መጠበቅ እና በባሏ መደሰት እንዳለባት በመረዳት በግልፅ በመወያየትም ሆነ በዘርፉ የተፃፉ ጽሑፎችን በማንበብ፣ ደስታውን የጋራ የማድረግ የወንዶች ተቀዳሚ ኃላፊነት ነው፡፡
  በመጨረሻ ማንሳት የምፈልገው ነጥብ፣ ብዙዎች በትዳር ላይ በግንኙነት ዙሪያ በመርህ ደረጃ የሚነሱ ጠቃሚ ምክሮችን ማንበብ ፋይዳ ቢ መሆኑን ሲናገሩ ይታያል፡፡ ለዚህም እንደ ምክንያትነት የሚያነሱት መከራከሪያ የፀሐፊዎቹ ወይም አነበብን የሚሉ ሰዎችን ግለ ህይወት በናሙናነት በማንሳት፣ በትዳር ህይወታቸው ስኬታማ አለመሆናቸውን ነው፡፡ እዚህ ጋ መረዳት ያለብን ቁም ነገር፣ ችግሩ ያለው ከዕውቀቱ ወይም ከንባቡ ሳይሆን ያወቅነውን እና የሰማነውን በልቦናችን አኑረን መተግበር ስለሚሳነን መሆኑን ነው፡፡ በመሆኑም ተፈጥሮ የለገሰችን ሰብዕና፣ በህይወት ተሞክሮ እና ዕውቀት በማዳበር፣ ያካበትነውን ዕውቀት በመተግበር እና ለውጥ በማምጣት ትዳራችን በግምት ሳይሆን፣ በጥበብ የምንመራትን ልቦና ይስጠን፡፡

  ሴት ልጅ ምን መስማት አትሻም?
  ሴቶች ስለ ሌላ ሴት ወይም ስለ ቀድሞ ጓደኛህ ስታደንቅ መስማት አትፈልግም፡፡ ከሌላ ሴት ጋር እንድታወዳድራትም እንዲሁ፡፡ ስለ ሰውነት ቅርጽና ውበቷ አድናቆት እንጂ ነቀፌታ ቅር ያሰኛታል፡፡ በድንገት ተሳስተህ የሌላ ሴት ስም ማንሳትም አይኖርብህም፡፡ በሌላ መንገድ ያስጠረጥርሃልና፡፡ ከአሁን ቀደም በነበረህ የሴት ልጅ ትውውቅ ውስጥ አላግባ ያደረካቸውን ነገሮች ማውራትህ ከባድ ግምት ውስጥ ይጥልሃልና በተቻለ መጠን ከኋላ ፈቅር ታሪክህ ውስጥ ጥሩ ጥሩውን እንጂ የሚያስተችህን ለመርሳት ወይም ላለማንሳት ጥረት አድርግ፡፡ በሌላዋ ላይ ይህን ያደረገ በእኔም ላይ ማድረጉ አይቀርም የሚል እምነት ይኖራታልና፡፡ ሴቶች ስለ አንተ ማወቅ የሚፈልጉትን ሲጠይቁህ እውነቱን መናገሩን ብቻ ነው የሚያዋጣው፡፡ ብዙ ጊዜ ሴቶች ለማወቅ በሚመስል መልኩ ይጠይቃሉ እንጂ የሚጠይቁትን ነገር ቀድሞውኑ ያውቁታልና አትዋሽ!
  በተቻለ መጠን ከአሁን ቀደም ከነበረህ የፍቅር ትስስር እንዴት እንደተለያየህ ምክንያትህን አሳማኝነት ያለውና ከአንተ በኩል ከፍተኛ ጥረት ማድረግህ ላይ ያነጣጠረ ይሁን እንጂ ኃላፊነትህን ስላለመወጣትህ የሚያንፀባርቁ ምክንያቶችን ወይም ደግሞ ቀድሞውኑ ለመለያየት የማያበቁ ምክንያቶችህን ሴቶች መስማት አይፈልጉም!! ቢሰሙም ትዝብት ውስጥ ይጥሉሃልና ጠንቀቅ በል!!

  ምንጭ: //www.mahderetena.com

  Read more »

 • የብብት ጠረንን መልካም ለማድረግ የሚጠቅሙ ምክሮች

   ኤፍ.ቢ.ሲ) የሰው ልጅ የራሱ የሆነ የተለየ የሰውነት ጠረን አለው።

  ይህ የሰውነት ጠረን ጤናማ ቢሆንም በአንዳንድ ሰዎች ዘንድ ግን ከመጠን ያለፈ ይሆንና ከራስ አልፎ ሌሎችንም ሊረብሽ ይችላል። ሰውነታችን ኤክሶክራይን (exocrine) እና አፖክራይን (apocrine) የተሰኙ ሁለት አይነት ላብ አመንጪ እጢዎች አሉት። ኤክሶክራይን የተባሉት እጢዎች በሁሉም የሰውነታችን ክፍል የሚገኙ ሲሆን፥ የአፖክራይን እጢዎች ደግሞ ጉርምስናን በሚያመላክቱና ፀጉር በሚወጣባቸው አካባቢዎች የሚገኙ ናቸው። የአፖክራይን እጢዎች ፕሮቲንና ስባማ ንጥረ ነገሮችን ያመነጫሉ፤ ይህም ነው ለሰውነት ጠረን መፈጠር ምክንያት የሚሆነው። ከመጠን ያለፈ ላብ እና የብብት ጠረንን ሁላችንም ልንከላከለው የምንፈልገው ጉዳይ ነው። ቅመም የበዛባቸው ምግቦችን እንደ ነጭ ሽንኩርት፣ ዝንጅብል እና ማጣፈጫዎችን አዘውትሮ መመገብ እንዲሁም ከላብ ጋር ተያይዞ የሚፈጠሩ ባክቴሪያዎች ለሰውነት ጠረን መለወጥ በምክንያትነት ይጠቀሳሉ።

  ንፅህናን መጠበቅ፣ የአየር ማቀዝቀዣዎችን መጠቀም፣ እንደ አየር ሁኔታው ሳሳ ያሉ ልብሶችን መልበስ፣ ልብሶቻችን በአጭር ጊዜ ልዩነት መቀየር፣ ቅመም የበዛባቸውን ምግቦችን ከመመገብ መቆጠብ፣ ፀረ ባክቴሪያ የሆኑ ሳሙናዎችን መጠቀም እና ዲዮድራንት ወይም የላብ ማጥፊያ ከመጠቀማችን በፊት ብብታችን ደረቅ መሆኑን ማረጋገጥ ለችግሩ በመፍትሄነት ይነሳሉ።

  የሰውነት ጠረንን በተለይም የብብት መጥፎ ጠረንን ለማስወገድ ከፍተኛ ጥረትን የሚጠይቅ ነው። ኬሚካሎችን ለመጠቀም ካልፈለጉና እየተጠቀሙት ያለው ዲዮድራንት የሚያረካ ውጤት ካላስገኘልዎ ከዚህ በታች የተጠቀሱትን ቢሞክሯቸው መልካም ውጤት ያስገኛሉ ይላል የሄልዚ ላይፍ ላንድ ድረ ገጽ ዘገባ።

  1. ቤኪንግ ሶዳ ቤኪንግ ሶዳ

  የፍሪጅ እና ላውንደሪዎችን መጥፎ ጠረን ለማስወገድ እንደሚረዳው ሁሉ የብብት ጠረንን ለማስተካከል እንደሚያግም ይነገራል። ጥቂት ቤኪንግ ሶዳ ከበቆሎ ዱቄት ጋር በመቀላቀል ከብብት ውስጥ መክተት ቆዳችን ደረቅ እና ንጹህ እንዲሆን ያደርጋል።

  2. የብብት ጸጉርን አለመላጨት 

  ሁሉም ነገር ሲፈጠር በምክንያት ነው፤ በሰውነታችን የሚወጡ ጸጉሮችም ለባክቴሪያ መፈጠር እና ለብብት ጠረን መቀየር ምክንያት የሚሆን እርጥበትን መሳብ አቅም አላቸው። እናም የብብት ጸጉርን መላጨት (ሼቭ ማድረግ) ለባክቴሪያዎች መራባት እድል ይፈጥራል ማለት ነው። የብብት ጸጉራችንን ከላጨን በኋላ የምንጠቀመው ቅባት ወይም ክሬምም የቆዳ መቆጣትን ሊያስከትል ስለሚችል የብብት ጸጉርዎን ከመላጨት ይቆጠቡ ይላል መረጃው።

  3. የሻይ ዛፍ ዘይት 

  የተለያዩ ቆዳ ነክ ችግሮችን እና መጥፎ የሰውነት ጠረንን ከሻይ ዛፍ በሚገኘው ዘይት ማከም ይቻላል። የዚህ ዛፍ ዘይት በጸረ ባክቴሪያ እና ጸረ ፈንገስ ይዞታው ነው የሚታወቀው። መጠነኛ የሻይ ዛፍ ዘይት ከሮዝ አበባ ውሃ ጋር ቀላቅሎ ብብትን መቀባት መጥፎ ጠረንን ለማስወገድ ይረዳል።

  4. ተፈጥሯዊ ሳሙና

  መላ ሰውነታችንን በተፈጥሯዊ ሳሙና መታጠብ መጥፎ የሰውነት ጠረንን ለማስወገድ ይጠቅማል። ከወይራ ዘይት እና ሶዳ እንዲሁም ከፍየል ወተት የሚዘጋጁ ተፈጥሯዊ ሳሙናዎችን መጠቀም የቆዳ ውበትን ከመጠበቅ ባለፈ ማራኪ ጠረንን ያላብሳል ተብሏል።

  5. አልኮል

  እንደ ቮድካ ያሉ ሽታ አልባ የአልኮል መጠጦችን በስፕሬይ ብብትን መርጨት መጥፎ ጠረንን እና ባክቴሪያዎችን ለማስወገድ ይረዳል። ይሁን እንጂ አልኮል ልንጠቀም የሚገባው ልብስ ከመልበሳችን በፊት ነው።

  6. ሎሚ

  ሎሚ የቆዳችንን ፒ.ኤች ደረጃ ለማስተካከል ያግዛል። የሎሚ ቁራጭን ከብብታችን ስር በማድረግ ለ15 ደቂቃ መቆየት ቀኑን ሙሉ መልካም መዓዛ እንዲኖረን ይረዳል።

  7. የአፕል ጭማቂ

  የአፕል ጭማቂ፣ ውሃ እና የሎሚ ጭማቂ በደንብ በማዋሃድ በመርጫ (ስፕሬይ) ውስጥ ማስገባት፤ ከዚያም ውህዱን በጠዋት ልብስ ከመልበሳችን በፊት ብብታችንን መርጨት ለመጥፎ ጠረን መከሰት ምክንያት የሆኑ ባክቴሪያዎችን ለማጥፋት ከፍተኛ ድርሻ አለው።

  8. ሀይድሮጅን ፐርኦክሳይድ

  ሀይድሮጅን ፐርኦክሳይድን ከውሃ ጋር በመቀላቀል ብብትን መርጨትም እንዲሁ የብብት ጠረንን ለማስተካከል እንደሚጠቅም ነው የሚነገረው። በአጠቃላይ የሰውነት ጠረንን ለመጠበቅ በዋነኝነት ንጽህናችንን ለመጠበቅ ትኩረት ልንሰጥ ይገባል።

  ምንጭ፡- mahderetena.com

  - See more at: http://www.mahderetena.com/amharic/?p=4452#sthash.bbuCihtv.dpuf

  Read more »

 • ማድያት (Melasma)

  ማድያት ብዙ ጊዜ ከሚከሰቱ የቆዳ ላይ ችግሮች ዉስጥ አንዱ ነዉ፡፡ ይህ ችግር በፊት ላይ በቡናማና በግሬይ መካከል ያለ የፊት ላይ ቆዳ ቀለም ለዉጥ የሚያመጣ ሲሆን ብዙ ሰዎች በጉንጫቸዉ፣ በአፍንጫቸዉ፣ በግንባራቸዉ፣ አገጫቸዉና በላይኛዉ ከንፈራቸዉ ከፍ ብሎ ባለ ቦታ ይወጣል፡፡ በተጨማሪም ማድያት ብዙ ጊዜ የፀሃይ ብርሃን በብዛት የሚያገኙ እንደ አንገትና ክንድ ያሉ የሰዉነት ክፍሎችንም ያጠቃል፡፡

  የማድያት ህመም ምልክቶች
  ማድያት በፊት ላይ ግራጫና ቡናማ መካከል ያለ በጣም የተለመደ የቆዳ ቀለም ለዉጥ የሚያመጣ ሲሆን ብዙዉን ጊዜ የሚታየዉ/የሚከሰተዉ በሚከተሉት ቦታዎች ላይ ነዉ፡-
  • በጉንጭ ላይ
  • በአፍንጫ
  • ከላይኛዉ ከንፈር ከፍ ብሎና
  • አገጭ ላይ ናቸዉ፡፡

  በተወሰኑ ሰዎች ላይ በአንገታቸዉና በክንዳቸዉ ላይ ሊታይባቸዉ ይችላል፡፡ ይህ ግን ብዙ ጊዜ አይታይም፡፡ ማድያት የሚያስከትለዉ ምንም አይነት የህመም ምልክት ባይኖረዉም ሰዎች ማድያት ቆዳቸዉ ላይ የሚያመጣዉን ለዉጥ አይፈልጉትም፡፡

  ማድያት የሚከሰተዉ/የሚበዛዉ እነማን ላይ ነዉ?
  ማድያት ከወንዶች ይልቅ በሴቶች ላይ በብዛት የሚታይ ሲሆን ማድያት ከሚከሰትባቸዉ ሰዎች ዉስጥ የወንዶች ተጋላጭነት/ድርሻ 10 በመቶ ብቻ ነዉ፡፡ ማድያት ጠቆር ያለ የቆዳ ቀለም ባላቸዉ እንዲሁም በቤተሰባቸዉ ዉስጥ የማድያት ችግር ባለባቸዉ ሰዎች ላይ በብዛት ሊከሰት ይችላል፡፡

  የማድያት መንስኤዎች
  ለማድያት መከሰት መንስኤ የሆነዉ ነገር በትክክል ባይታወቅም በቆዳችን ዉስጥ ያሉና የቆዳ ቀለም እንዲፈጠር የሚያደርጉ ሜላኖሳይት የሚባሉ ሴሎች ከመጠን ያለፈ ቀለም በማምረት ምክንያት የሚከሰት ነዉ፡፡ ነጭ የቆዳ ቀለም ካላቸዉ ይልቅ ጠቆር ያለ የቆዳ ቀለም ያላቸዉ ሰዎች ለማድያት የሚጋለጡ ሲሆን ይህ የሆነበት ምክንያት ጠቆር ያለ የቆዳ ቀለም ያላቸዉ ሰዎች ነጭ ቆዳ ካላቸዉ ሰዎች ይልቅ ብዙ ሜላኖሳይቶች በቆዳቸዉ ውስጥ ስላላቸዉ ነዉ፡፡

  ማድያትን ሊያስነሱ የሚችሉ ነገሮች
  • ለፀሃይ ብርሃን መጋለጥ፡- ለፀሃይ ብርሃን መጋለጥ ሜላኖሳይትን እንዲነቃቁ ያደርጋቸዋል፡፡ማድያት ከጠፋ በኃላ ድጋሚ ለመቀስቀስ ለትንሽ የፀሃይ ብርሃን መጋለጥ ብቻ ይበቃል፡፡ ይህ ክስተት በብዙ ሰዎች ለማድያት ተደጋግሞ መምጣት አይነተኛ ምክንያት ሊሆን ይችላል፡፡
  • የሆርሞን መለዋወጥ፡- ነፍሰጡር እናቶች ማድያት ብዙዉን ጊዜ ከሚከሰትባቸዉ ዉስጥ የሚጠቀሱ ሲሆን የእርግዝና መከላከያ እንክብል ና የሆርሞን ህክምና ለማድያት መከሰት ምክንያት ሊሆኑ ይችላሉ፡፡
  • ኮስሞቲክስ፡- ቆዳን ሊቆጠቁጡ የሚችሉ ለቆዳ እንክብካቤ የሚጠቀሙባቸዉ ነገሮች ማድያትን ሊያባብሱ ይችላሉ፡፡

  የማድያት ምርመራ
  ማድያትን የቆዳ ህክምና ባለሙያዎች በማየትና በመመርመር የሚለዩ ሲሆን ማድያቱ ምን ያህል ወደቆዳዎ ዘልቆ እንደገባ ለመለየት/ለማወቅ ቆዳዎትን ዉድስ ላይት በሚባል መመርመሪያ መሳሪያ ሊያዎት/ሊመረምሩ ይችላሉ፡፡
  አንዳንዴ ማድያት ከሌላ የቆዳ ችግር ጋር ሊመሳሰል ይችላል፡፡ ስለሆነም ሌሎቹን የቆዳ ችግሮች ከማድያት ለመለየት ከቆዳዎ ላይ ትንሽ ናሙና(ባዮፕሲ) በመዉሰድ ለምርመራ ሊልኩት ይችላሉ፡፡

  ማድያት እንዴት ሊታከም ይችላል?
  ማድያት በራሱ ጊዜ እየጠፋ ሊመጣ ይችላል፡፡ ይህ ብዙዉን ጊዜ የሚከሰተዉ ማድያትን ሊያስነሱ የሚችሉ ነገሮች ሲቀንሱ/ሲጠፉ ሲሆን ለምሳሌ ነፍሰጡር እናት ከወለደች በኃላ፣ የእርግዝና መከላከያ እንክብል የሚወስዱ መዉሰዱን በሚያቆሙበት ወቅት ቀስ እያለ ሊጠፋ ይችላል፡፡
  አንዳንድ ሰዎች ላይ ማድያት ለረጅም ጊዜ/ አንዳንድ ጊዜ ደግሞ ለእድሜ ልክ ሊቆይ ይችላል፡፡ ማድያትዎ እየጠፋ ካልመጣ ወይም የወሊድ መከላከያ እንክብልዎን መቀጠል ከፈለጉ ማድያት ህክምና ስለለዉ የህክምና ባለሙያዎን ያማክሩ፡፡ ለማድያት የሚረዱ ህክምናዎች የሚከተሉትን ያጠቃልላል፡፡ እነርሱም
  • ሃይድሮኪዪኒን፡- ይህ ብዙዉን ጊዜ ለመጀመሪያ ጊዜ ለማድያት ህክምና የሚያገለግል ሲሆን ማድያት የወጣበት ቦታ በሚቀባበት ወቅት ቦታዉ ቀስ እያለ ወደ ቀድሞዉ መልኩ እንዲቀየር ያደርጋል፡፡ መድሃኒቱ በክሬም፣በሎሽን፣በጄልና ፈሳሽ መልክ የሚገኝ ሲሆን የተወሰኑትን ያለህክምና ባለሙያዎ ማዘዣ ሊያገኙ ይችላሉ፡፡
  • ትሪቲኖን እና ኮርቲኮስቴሮይድ፡- ይህ ለማድያት ህክምና የሚያገለግልና በሁለተኛ ደረጃ ያለ ሲሆን በሚጠቀሙበት ወቅት ማድያቱ ቀስ እያለ እንዲለቅ ያደርጋል፡፡
  • ሌሎች በቆዳ ላይ የሚቀቡ መድሃኒቶች፡- የቆዳ ህክምና ባለሙያዎ እንደ አዞሊክ አሲድ፣ ኮጂክ አሲድ ያሉ መድሃኒቶችን ሊያዝልዎ ይችላል፡፡
  • ፕሮሲጀርስ፡- ቆዳዎ ላይ የሚቀቡት መድሃኒቶች ለዉጥ የማያመጡ ከሆነ የህክምና ባለሙያዎ ኬሚካል ፒል፣ ማይክሮደርማአብሬሽን እና ደርማአብሬሽን የሚባሉ የህክምና ፕሮሲጀሮችን ሊያከናዉኑልዎ ይችላሉ፡፡

  የህክምናዉ ዉጤት
  የቆዳ ህክምና ክትትል ከተደረገ/ካደረጉ ብዙ ጊዜ በህክምናዉ ጥሩ ዉጤት የሚያዩ ቢሆንም ጥቂቶች ላይ ህክምናዉ ዉጤት ላይኖረዉ ይችላል፡፡ የህክምና ባለሙያዎን ምክር ከተከተሉ/ከተገበሩ ህክምናዉን በጀመሩ በጥቂት ወራት ዉስጥ ለዉጥ ሊያዩ ይችላሉ፡፡
  ማድያትዎ በህክምናዉ ከጠፋልዎ በኃላ የቆዳ ህክምናዎን መቀጠል አስፈላጊ ነዉ፡፡ ይህ ማድያትዎ ተመልሶ እንዳይመጣ ያግዝዎታል፡፡ በተጨማሪም የፀሃይ መከላከያ ዘዴዎችን እንደ ሰንስክሪንና ኮፍያ/ጃንጥላ ያሉ ነገሮችን መጠቀም ያስፈልጋል፡፡

  ማድያት ካለዎ የቆዳ ህክምና ባለሙያዎች የሚከተሉትን ምክሮች እንዲተገብሩ ያዛሉ
  1. የፀሃይ መከላከያ ሁሌ/በየቀኑ መጠቀም፡- ብዙዉን ጊዜ ለማድት ህክምና ከሚያገለግሉ ነገሮች ዉስጥ አንዱ የፀሃይ መከላከያን መጠቀም ነዉ፡፡ እንደሚታወቀዉ ለፀሃይ ብርሃን መጋለጥ ማድያትን የሚያመጣ ሲሆን የመከላከል ብቃታቸዉ ከ30ና ከዚያ በላይ የሆኑ( Sun Protection Factor (SPF) of 30 or more) ያሉ እንደ ዚንክ ኦክሳይድ ወይም ቲታንየም ዳይ ኦክሳይድ ያሉ ሰን ስክሪኖችን ለፀሃይ ከመጋለጥዎ ከ15 ደቂቃዎች ቀደም ብለዉ መቀባትና በየ2 ሰዓቱ መልሶ መቀባት
  2. ከቤትዎ ዉጭ ፀሃይ ላይ በሚሄዱበት ወቅት ኮፍያ መጠቀም፡- በቅርቡ በተደረገ ጥናት መሰረት የፀሃይ መከላከያ ቅባት ብቻ መጠቀም ሙሉ በሙሉ ከችግሩ ላይከላከልልዎ ይችላል፡፡ ከተቻለ ከሚቀቡት የፀሃይ መከላከያ ቅባት(ሰንስክሪን) በተጨማሪ ኮፍያ መጠቀም ይመከራል፡፡
  3. ለቆዳ እንክብካቤ የሚጠቀሙባቸዉን ነገሮች በጥንቃቄ መምረጥ፡- ለቆዳ እንክብካቤ የሚጠቀሙባቸዉ ነገሮች ቆዳዎትን የማይቆጠቅጡ ወይም የማያቃጥሉ ነገሮች መሆን አለባቸዉ፡፡ ምክንያቱም እነዚህ ነገሮች ማድያቱን ሊያባብሱ ይችላሉ፡፡
  4. ዋክሲንግ ያለማድረግ(ፀጉርን ያለመንቀል)፡- ዋክሲንግ ማድረግ የቆዳን መቆጣት ስለሚያመጣና ማድያትን ስለሚያባብስ ማድያት ባለበት ቦታዎች ዋክሲንግ ከማድረግ ቢቆጠቡ፡፡

   

  ምንጭ: http://www.mahderetena.com/

  Read more »

 • ቅናት ለፍቅር ምኑ ነው? (በተለይ በፍቅር ውስጥ ሆነው በአፈቀሩት ላይ የሚቀኑ እንዲያነቡት ይመከራል)

  ከሊሊ ሞገስ

  ብዙ ሰዎች እርር ድብን ብለን እናውቅ ይሆናል፡፡ በቅናት! ዛሬ እኔ እና እናንተ ስለ ቅናት ልናወጋ፣ በቅናት ያረርንባቸውን ጊዜያቶች በድጋሚ ልናጤን ነው፡፡ የእናንተን አላውቅም እንጂ እኔ በበኩሌ ከዚህ ቀደም የኔው ጉድ በቅናት አንፃር ያደረገችበትን ቀኖች በምናቤ እንደ ፎቶ አልበም ደርድሬያቸዋለሁ፡፡ መቼም ቀንቼ አላውቅም አትሉኝም፡፡ ቅናት መጠኑ ይብዛም ይነስም የሁላችንንም ልብ ያንኳኳል፡፡ ቅናት እና እሳት ቤት አይዘሉም፡፡ እርግጥ ነው ቅናት ውስጣችን አስደሳች ስሜት የሚፈጥር አለመሆኑን እናውቃለን፡፡ ከዚህ አኳያ ቅናትን ከአሉዊ ስሜቶች ተርታ ልንፈርጀው እንችላለን? ወይንስ ለትዳር አጋራችን ወይንም ለፍቅር ጓደኛችን ያለን ፍቅር ኃያል መሆኑን ማረጋገጫ አድርገን እንወስደዋለን? ይህንን ጥያቄ ለመመለስ ብዕሬ ጉሮሮዋን ጠራርጋለች፡፡

  ከሁሉ በፊት ግን ስለምንወያይበት ርዕስ ግልፅ የሆነ መረጃ ሊኖረን ይገባል፡፡ ለዛም ነው ቀድመን ቅናት ምንድን ነው? የሚለውን ጥያቄ መመለስ ያለብን፡፡

  ቅናት ምንድነው?

  ቅናት ማለት በተቃራኒ ፆታ ግንኙነት ውስጥ እያለን በተለያዩ ምክንያቶች በውስጣችን ሊፈጠር የሚችል፣ የምንወደውን ሰው ከማጣት ጋር የተያያዘ የስጋት እና ሽብር ስሜት ነው፡፡ ቀደም ብዬ እንደጠቀስኩት ይሄ የሽብር ስሜት ነው፡፡ ቀደም ብዬ እንደጠቀስኩት ይሄ የሽብር ስሜት በተለያዩ ምክንያቶች ሊፈጠር ይችላል፡፡ በተጨማሪም ቅናት ያለንን ግንኙነት ሊጠቅምም ሊጎዳም እንደሚችል በዘርፉ የተመራመሩ ሰዎች ገልፀዋል፡፡

  አሉታዊ ቅናት
  ቅናትን አሉታዊ የምንልበት ዋናው ምክንያት በዓለም ላይ ከተፈፀሙ የትዳር ጓደኛ ግድያ መንስኤዎች መካከል ቅናት ፊት አውራሪ ሆኖ በመምራት ላይ ስለሚገኝ ነው፡፡ ይሄ ደግሞ ቅናት ልክ የማይኖረው ከሆነ አደገኛ ሊሆን እንደሚችል ያሳያል፡፡
  ቅናትን አሉታዊ ቅናት የምንለው መቼ ነው? ቅናት ከልክ እንዳለፈ ለማረጋገጥ የተወሰኑ ምልክቶችን ልጠቃቅስ፡፡
  ሀ. የቅናት ስሜት በሚፈጠርበት ወቅት ስሜታችንን ለመግለፅ ቃላትን ሳይሆን ጉልበትን መጠቀም ስንጀምር፤ በግልፅነት ከመወያየት ይልቅ ቅናት እንዲያድርብን አደረግን የምንለው ሰው ላይ ለዱላ ስንጋብዝ፡፡
  ለ. የትዳር አጋርህ/ሽ፣ ጓደኛህ/ሽ ካንተ/ካንቺ ጋር በሌለ/ች ሰዓት ጊዜህን/ሽ ‹‹ምን እያደረገ/ች ይሆን?›› በማለት ቀኑን ሙሉ የምንብሰለሰል ከሆነ አልፎ ተርፎም ቀኑን ብቻ ሳይሆን ሌሊትም ኮርኒስ እየቆጠርን ነገር የምንበላ ከሆነ ችግር አለ ማለት ነው፡፡
  ሐ. የቅናት ስሜት ከፍቅር የመነጨ ሳይሆን እምነት ከማጣት የመጣ ሲሆን፤
  መ. የትዳር አጋርህ/ሽ ውሎውን/ዋን ለመናገር ወይም አንተ/አንቺ በሌለህበት/ሽበት ሰዓት የተፈጠሩ ነገሮችን ለመናገር የምትሳቀቅ/ቂ ከሆነ፤
  ሠ. በዚህ በመዘዘኛ ቅናት ምክንያት ለምግብ ያለን ፍላጎት ከቀነሰ፤ ጭንቀት ውስጥ ከገባን፤ የልብ ምታችን በተደጋጋሚ የሚጨምር ከሆነ፣ ከልክ በላይ የሚያልበን እንዲሁም ቶሎ የሚደክመን ከሆነ፤
  ረ. በመጨረሻም ቅናት ከፍቅረኛችሁ ጋር ያላችሁ ግንኙነት ላይ ክፍተት እየፈጠረ ከመጣ ችግር አለ ማለት ነው፡፡
  ከዚህ በተጨማሪ ሊንዳ ብሎር የምትባል ክሊኒካል ሳይኮሎጂስት ቅናታችን አሉታዊ መሆን አለመሆኑን ለማረጋገጥ እነዚህን ሶስት ጥያቄዎች ራሳችሁን ጠይቁ ትለናለች፡፡
  1. ይሄ ቅናት የዕለት ተዕለት ኑሮአችሁ ጋር እየተጋጨ ነው?
  2. የምወደውን ሰው እያሳዘነ እና እየጎዳ ነው?
  3. ቅናቱ እኔ ከምቆጣጠረው በላይ እሱ ይቆጣጠረኛል?
  ከላይ ለተዘረዘሩት ሶስት ጥያቄዎች መልሳችሁ ‹‹አዎን›› ከሆነ ጉድ ፈልቷል ማለት ነው ትላለች የሳይኮሎጂ ባለሙያዋ፡፡
  እንግዲህ ወዳጆች ከላይ የጠቀስኳቸው ነገሮች በተደጋጋሚ በፍቅር ግንኙነትሽ/ህ ጊዜ የሚከሰቱ ከሆነ ቆም ብሎ ማሰብ ያስፈልጋል፡፡ በአቅራቢያችን ወደሚገኝ የስነ ልቦና አማካሪ ብንሄድ መፍትሄ ልናበጅለት እንችላለን፡፡ አሊያም ማማከሩ ለውጥ ካላመጣ በሰላም መለያየቱ ሁሉ የሚበጅ ይመስለኛል፡፡

  አዎንታዊ ቅናት
  ቅናት በአብዛኛው ግንኙነቶች አደጋ ላይ ሲጥል ብንመለከተውም መጠኑ ሳይበዛ ግን አዎንታዊ ጎኑ ሊያመዝን የሚችልበት ሁኔታ ይፈጠራል፡፡ ታዲያ አዎንታዊ ቅናት ስል ደስ የሚል ስሜት የሚፈጥር ቅናት ማለቴ እንዳልሆነ ይገባችኋል፡፡ ታዲያ ቅናትን አዎንታዊ የምንለው እንዴት ነው?
  አንዳንድ ጥናቶች እንደሚያትቱት መጠነኛ ቅናት በፍቅር ጓደኛ ላይ ደስ የሚል ስሜት ይፈጥራል፡፡ ምክንያቱም የፍቅር ጓደኛችንን ምን ያህል እንደምንወድ ሊያሳይ ይችላል፡፡ የፍቅር ወይም ትዳር አጋራችን መጠነኛ ቅናትን እንደ ፍቅር መገለጫ ሊመለከቱት ይችላሉ፡፡ ይሁን እጂ ብዙ ጥንዶች የተሰማቸውን ደስ የሚል ስሜት ቅናት ላደረበት አጋራቸው ሲያካፍሉት አይስተዋልም፡፡ በሌላ መልኩ ደግሞ መግባባት ባለመቻል እና ንትርክ መካከላቸው ያለው የፍቅር ድባብ የተጋረደባቸው ጥንዶች መጀመሪያ በፍቅር ሲወድቁ ለፍቅረኛቸው የነበራቸው ወይንም ስለ ፍቅረኛቸው የሚወዱትን ጎን መልሶ ለማግኘት ይቸገራሉ፡፡ ታዲያ በዚህ ወቅት ፍቅረኛቸውን ከሌላ ሰው ጋር ቢመለከቱት/ቷት በሚፈጠርባቸው የቅናት ስሜት ያ ጠፍቶ የነበረ የጠብ ምክንያት ግልጽ ሊሆን ይችላል፡፡ ስለዚህ ከዛ ሰው ጋር ያላቸውን ግንኙነት እንዲያድሱ ያስገድዳቸዋል፡፡ ከንትርክ የበለጠ ጥሩ የጋራ ታሪክ እንደነበራቸው ያስታውሳሉ፡፡ ያንንም ጥሩ ጊዜ ለመመለስ የሚያስችል አቅም ያገኛሉ፡፡ ‹‹በእጅ ያለ ወርቅ ከመዳብ ይቆጠራል›› እንዲሉ ነው ነገሩ አንዳንዴ፡፡

  የቅናት መንስኤዎች
  ቅናት አዎንታዊ እና አሉታዊ ጎኖች እንዳሉት ሁሉ መንስኤዎቹም የተለያዩ ናቸው፡፡ የቅናት መንስኤ በተለይ ቅጥ ያጣ ቅናት መነሻው የፍቅር አጋራችን ላይ ከመጠን ያለፈ ጥገኛ መሆን እና በራስ መተማመን አለመቻል ነው፡፡ ይሁን እንጂ የሁሉም አፍቃሪ ቅናት መንስኤ ጥገኛ መሆን እና በራስ መተማመን አለመቻል አይደለም፡፡ አንዳንድ ድርሳኖች እንደሚያስነብቡን አዎንታዊ ቅናቶች ኃያል ከሆነ ፍቅር ሊመጣ እንደሚችል እና መንስኤውም ፍቅረኛችን ካላት/ካለው የሶስተኛ ወገን ግንኙነት ጋር ሳይሆን ሌሎች ግዑዝ ከሆኑ ነገሮች ጋር በተያያዘ ሁሉ ሊመጣ ይችላል፡፡ ለአብነት ያህል ፍቅረኛ ሆዬ በስራ ብዙ ሰዓቱን/ቷን የሚያሳልፍ/የምታሳልፍ ሲሆን ወይንም ብዙ ጊዜውን/ዋን በማንበብ የምታሳልፍ/የሚያሳልፍ ከሆነ አዎንታዊ የምንለው አይነት ቅናት ሊያድርብን ይችላል፡፡ ቅናቱም የፍቅር ግንኙነቱን የሚያቀጭጭ አይነት ቅናት አይደለም፡፡ ጊዜ ከመፈለግ ጋር የሚያያዝ ብቻ ነው፡፡ ከዚህ በተጨማሪ የቅናት መንስኤ አሁን ካላቸው ግንኙነት በፊት በነበራቸው ግንኙነት የተከዱ ወደፊት በሚኖራቸው ግንኙነት የቅናት ስሜት ሊያድርባቸው ይችላል፡፡ ይህ ቅናት በበኩሉ በአመዛኙ ከእምነት ማጣት ጋር የተያያዘ ነው፡፡

  አሉታዊ ቅናትን ለማስወገድ
  ‹‹እርር ድብን ማለት አንገሽግሾኛል፤ ጨጓራዬን ልተፋው ነው፤ አንድ በሉኝ›› የሚሉ ከሆነ ደግሞ ቅናትን ፈፅሞ ልናጠፋው ባንችል እንኳ እንዴት ልንገራው እንደምንችል እንመልከት፡፡
  1. መፍትሄው ብዙ ጊዜ ያለው እዛው ፍቅረኛችን እጅ ስለሆነ የሚስማማንን ስሜት ለፍቅረኛችን ግልፅ ማድረግ ይመከራል፡፡
  2. ምክንያታዊ ለመሆን መሞከርም ጥቅም አለው፡፡ ለምን በሉኝ? ብዙ ጊዜ ቅናት ያሳደረብን ጉዳይ የሚጨበጥ ነገር ላይሆን፣ ጨርሶ ያልታሰበና ያልተፈጠረ የእኛ አዕምሮ ብቻ ያውጠነጠነው ሊሆን ይችላል፡፡ ስለዚህ የሚያስቀናንን ጉዳይ ከእውነታው ጋር በማስተያየት፣ ምክንያታዊ ለመሆን በመጣር የሚስማማንን ስሜት መርምረን ልንገራቸው እንችላለን፡፡
  3. ለራሳችን ያለን ክብር ሊጨምር ይገባል፡፡ በራስ መተማመናችንን ከፍ ያደርጋሉ የምንላቸውን የሌሎችን በራስ መተማመን የማይነኩ ነገሮችን ማድረግ ጠቃሚ ነው፡፡ አለ አይደል እኛ ከፍ ብለን እንድንታይ ሌላው ዝቅ ማለት የለበትም፡፡ ሌላውን ዝቅ ሳያደርጉ እኛን ከፍ የሚያደርጉ ነገሮችን ማድረግ በራስ መተማመናችንን ይጨምራል፡፡
  4. ፍቅረኛሞች በአመለካከት ስለሚለያዩ ከሶስተኛ ወገን ጋር ያላቸው የግንኙነት ገደብ ይለያያል፡፡ ስለዚህ የኛን ገደብ ባለማወቅ ፍቅረኛችን ልታስቀይመን/ሊያስቀይመን ትችላለች/ይችላል፡፡ በመሆኑም አስቀድመን የሚመቹንን እና የማይመቹንን ከሶስተኛ ወገን ጋር ያሉ ግንኙነቶች ግልፅ ማድረግ መልካም ነው፡፡
  ሰላም ሰንብቱልኝማ!!

  Read more »

Advertisment