ምንጭ: ያሬድ ሹመቴ
የዛሬ 80 ዓመት ልክ በዛሬው ዕለት ሐምሌ 22 1928 ዓ.ም. ብጹእ አባታችን አቡነ ጴጥሮስ ለሀገራቸው እና ለሀይማኖታቸው ክብር ሲሉ በግፈኛው ጣሊያን በጥይት ተደብድበው በመገደል ሰማዕትነትን ተቀበሉ።

በረከታቸው ይደርብን።

ታሪካቸውን በአጭሩ እነሆ። (ደቂቀ ናቡቴ ጽሁፉን እንዳሰናዳው)

በ1875 ዓ.ም.በሰሜን ሸዋ አገረ ስብከት ሰላሌ አውራጃ ፍቼከተማ ተወለዱ። ወላጆቻቸው ዕድሜያቸውገና በወግ ለትምህርት ሳይደርስ ወደ ደብረ ሊባኖስ ገዳም በመውሰድ ባሕታዊ ተድላለተባሉ መምህር አደራ ሰጧቸው። በዚያውገዳም የንባብ ቤቱንና የዜማውን የትምህርትደረጃዎች በሚያስገርም ሁኔታ በአጭር ጊዜአቀላጥፈው በመጨረስ ገና በልጅነትየዕድሜ ደረጃቸው ሦስተኛውን የቅኔትምህርት ጀምረው በአጭር ጊዜ ሙሉ ቤትተቀኙ። ይህንኑ የቅኔ ትምህርት ለማስፋፋትበምዕራብ ጎጃም አገረ ስብከት ወደሚገኘውየቅኔ ትምህርት ማዕከል ዋሸራ ተሻግረው ለመምህርነት የሚያበቃውን ትምህርት ፈጽመው አስመሰከሩ።

ከዚያም ከቅኔው ዐውድማ ጎጃም ወደዜማው አዝመራ ጎንደር ተሻገሩ። በዚያምእንደ ቅኔው ሁሉ እስከ ማስመስከርባይደርሱም የዜማውን ትምህርት በአጥጋቢሁኔታ ቀጸሉ። ከጎንደርም በወቅቱ ወሎ ቦሩሜዳ ከተባለው ቦታ ላይ ወንበር ዘርግተውየመጻሕፍትን ምሥጢር በየዓይነቱ ሲመግቡወደ ነበሩት ስመ ጥሩው መምህር አካለወልድ ዘንድ በመሔድ ዋና ዋናዎቹንየመጻሕፍት ትርጓሜ ትምህርቶች ማለትምብሉያትን፣ ሐዲሳትንና ሊቃውንትን በብቃትአካሔዱ።
ከዚህ በኋላ ልክ በ1900 ዓ.ም. እዚያው ወሎአማራ ሳይንት በተባለው ቦታ ወደሚገኘውምስካበ ቅዱሳን ገዳም በመሔድ ወንበርዘረጉ። በዚያው ቦታ ለዘጠኝ ዓመታት ያህልቅኔንና መጻሕፍትን አስተማሩ።

በዚህ ዓይነት በመማርና በማስተማርራሳቸውን በእግዚአብሔር ቃል በሚገባከጐሰሙ በኋላ በ1909 ዓ.ም. ወደ ደብረሊባኖስ ገዳም በመሔድ ሥርዓተ ምንኩስናንፈጸሙ። ብዙም ሳይቆዩ ማዕረገ ቅስናንተቀብለው ከወንበሩ አገልግሎት ጋር የቤተመቅደሱን ተልእኮም ደርበው ያዙ።
በ1910 ዓ.ም. መምህር ኃይለ ማርያምተብለው በወላይታ ሶዶ በሚገኘው ደብረመንክራት ምሁር ኢየሱስ ገዳም ተሾሙ።በ1916 ዓ.ም. እንደገና በዝዋይ ደብረምሕረት ቅዱስ ገብርኤል ገዳምበመምህርነት ተሾሙ። በ1919 ዓ.ም. ወደአዲስ አበባ በመምጣት የመንበረ መንግሥትቅዱስ ማርቆስ መምህርና በቤተ መንግሥትየግርማዊ ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ አበ ንስሐሆኑ። 

የግብፅ ቤተ ክርስቲያን ከአንድ ሺ ስድስትመቶ ዓመታት በኋላ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በዕውቀት መንፈሳዊከእርሷ ተወልደው በእቅፏ ውስጥ ባደጉኢትዮጵያውያን ጳጳሳት እንድትመራ ፈቃዷን ስትገልጽ ከተመረጡት አባቶች አንዱ በመሆንግንቦት 18 ቀን 1921 ዓ.ም. በእስክንድርያውመንበረ ማርቆስ ቤተ ክርስቲያን ማዕረገጵጵስናን ተቀበሉ። ከዓመት በኋላም “አቡነጴጥሮስ ጳጳስ ዘምሥራቅ ኢትዮጵያ ተላዌአሠሩ ለአቡነ ኢየሱስ ሞዓ” ተብለው በያኔውመንዝና ወሎ አገረ ስብከት ተሾሙ።
ሐምሌ 22 ቀን 1928 ስምንት ወታደሮችበስተጀርባቸው ሃያ እርምጃ ርቀውተንበርክከው በተንጠቀቅ ቆሙ። ወዲያውአዛዡ «ተኩስ» በማለት ትእዛዝ ሲሰጥስምንቱም ተኩሰው መቷቸው። ግን በስምንትጥይት ሳይሞቱ ቀሩ። መሞታቸውንናአለመሞታቸውን ለማረጋገጥ ዶክተር ተጠራ።ዶክተሩም እንዳልሞቱ አረጋገጠ። ከዚያምሌላ ወታደር በሦስት የሽጉጥ ጥይት ራስቅላቸውን መትቶ ገደላቸው።

« እኔ ግን ኢትዮጵየዊ ነኝ፡፡ ሓላፊነትምያለብኝ የቤተክርስቲያን አባት ነኝ፡፡ ስለዚህስለ ሀገሬና ስለ ቤተ ክርስቲያኔእቆረቆራለሁ፡፡. . . እኔን ለመግደልእንደወሰናችሁ አውቃለሁ፡፡ ስለዚህ በእኔ ላይየፈለጋችሁትን አድርጉ፡፡ ግን ተከታዮቼንአትንኩ» ሰማዕተ ጽድቅ በሆነ ደማቸውአተሙ፡፡ አኩሪ በሆነ አባታዊ ሓላፊነታቸውለአገር፣ ለቤተክርስቲያን፣ ለወገን ሁሉአለኝታነታቸው አረጋግጠው ሐምሌ 22 ቀን1928 ዓ.ም. በሰማዕትነት አለፉ፡፡

"ብፁዕነታቸው በፍርድ ችሎት ላይ እንዳሉሕዝቡ ሁሉ ስለእርሳቸው እያዘነ ሳለመስቀላቸውን አውጥተው እየጸለዩ ሕዝቡንባረኩ። ወዲያው የሞታቸው ሰዓት መድረሱንዐውቀው ሰዓታቸውን ከኪሳቸው አውጥተውተመለከቱ። በዚህ ጊዜ ሁሉ ምንም ፍርሃትአይታይባቸውም ነበር። የሞታቸውን ፍርድያነብ የነበረው ኢጣልያዊ ዳኛ ግንይንቀጠቀጥ ነበር። ታላቅ ፍርሃትም በፊቱይታይ ነበር።"

የኢጣሊያ ፋሺስት በ1928 ዓ.ም. በኢትዮጵያ ላይ የግፍ ጦርነትን ባነሣ ጊዜ ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ ከጦር ስፍራ ለመለየት ስላልሆነላቸው፣ ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴን ተከትለው ወደ ሰሜን ጦር ግንባር ዘምተዋል፡፡ ፋሺስቱ በማይጨው የመርዝ ጦርነት ከማድረጉ የተነሣ፣ የኢትዮጵያ ሠራዊት ሲበታተንም ከንጉሠ ነገሥቱ ጋር የተመለሱት አቡነ ጴጥሮስ ወደ ደብረ ሊባኖስ ሄደው ለአገርና ለነፃነት መሞት ቅዱስ ተግባር መሆኑን ለሥላሴ አርበኞች በመስበክም ይታወቃሉ፡፡

አርበኞች አዲስ አበባን በሁለት አቅጣጫዎችከሰሜናዊ ምዕራብ እና በደቡባዊ ምሥራቅ አቅጣጫ ለመቆጣጠር ውጊያ በከፈቱበትጊዜ የተማረኩት አቡነ ጴጥሮስ፣ ለፋሺሽትእንዲገዙ የኢጣሊያ መንግሥት ገዢነትንም አምነው አሜን ብለው እንዲቀበሉ ግፊትቢያደርጉባቸውም፤ እምቢኝ ለሀገሬናለሃይማኖቴ ብለው ለሰማዕትነት ያበቃቸውንየሞት ጽዋ ተቀብለዋል፡፡

ቅዱስ ጳውሎስ ደቀ መዝሙሩ የሆነውጢሞቴዎስን የተሰጠውን አደራ በመጠበቅ ሓላፊነቱንና ግዴታውን መወጣት እንደሚገባው ሲገልጽ «እቀብ ማህጸንተከ፤አደራህን ጠብቅ» በማለት ነው፡፡ 1ኛጢሞ.6 .2፡፡ ጢሞቴዎስ በመምህሩ የተጣለበትንአደራ ለመወጣት የዚህ ዓለም ፈቃድሳያሸንፈው ተወጥቷል፡፡ የዓላውያን ነገሥታትማዋከብ፣ ድብደባ አደራውን እንዳይወጣአላደረገውም፡፡ የአቡነ ጴጥሮስየሰማዕትነትም ጉዞ መነሻውም መድረሻውምየእነዚህ አባቶች አርአያ ፍኖት ነው፡፡

ለሀገራቸውና ለወገናቸው እስከ መጨረሻዋሰዓት ድረስ እውነቱን ከሐሰት በመለየትለሕዝባቸው የሰጡት ምስክርነትየተጣለባቸውን አደራ ከመወጣት ነው፡፡ አለቃተጠምቀ የተባሉ ቅድስናን ከሊቅነት ጋራአስተባብረው የያዙ የቅኔ መምህራቸው አንድቀን ብፁዕነታቸውን ጠርተው የሚከተለውንየአደራ ቃል ያስተላልፋሉ፡፡ «ኀይለማርያምአንተ ወደፊት ጳጳስ ትሆናለህ፤ በወቅቱምአረመኔ በዚህች ሀገር ይሠለጥናል፡፡ ታዲያያኔ አንተ ለነፍስህ ሳትሳቀቅ በሰማዕትነትእለፍ፤ ሰማዕትነት ክፍልህ ነው፡፡ አደራ፡፡» /መርሻ አለኸኝ /ዲያቆን/፣ 1986 ዓ.ም፣ ዜናጳጳሳት ኢትዮጵያውያን፣ ገጽ.80/

ሐዋርያው ቅዱስ ጢሞቴዎስ የመምህሩንየአደራ ቃል በመያዝ እስከ መጨረሻውእንደጸናው ብፁዕነታቸውም የመምህራቸውንየአደራ ቃል በሰማዕትነት አትመው ጠበቁ፡፡አንዲትም ቀንና ሰዓት ከሞት ሳይሸሹ እናሳይደበቁ ለአገራቸው ፣ለቤተ ክርስቲያናቸውእና ለሕዝባቸው ሲሉ ሞትን ተጋፈጡ፡፡የሰማዕትነትን ጽዋ ተጎነጩ፡፡ የዚህ ምንጩአደራ ነው፡፡ ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስቤተክርስቲያን በአደራ የሰጠቻቸውን ሓላፊነትለመወጣት ሕዝበ ክርስቲያኑን በጸሎታቸውእየደገፉ፣ በትምህርታቸው እያበረቱአስተዳድረዋል፡፡

ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ ሕዝብ ቀስቅሰዋል፤ራስዎም አምጸዋል፣ ሌሎችንም እንዲያምጹአድርገዋል በሚል የወንጀል ክስ ፍርድ ቤትቀረቡ፡፡ ችሎቱ ተሰይሞ ሲቀርቡ ዳኛው«ካህናቱም ሆኑ የቤተክህነት ባለሥልጣናትጳጳሱ አቡነ ቄርሎስም የጣሊያንን መንግሥትገዥነት አምነው አሜን ብለው ሲቀበሉእርስዎ ለምን ዐመፁ) ለምን ብቻዎንአፈንጋጭ ሆኑ)» ሲል ጠየቃቸው፡፡ ብፁዕአቡነ ጴጥሮስ በቆራጥነት «አቡነ ቄርሎስግብጻዊ ናቸው፤ ስለ ኢትዮጵያና ስለኢትዮጵያውያን የሚገዳቸው ነገር የለም፡፡ እኔግን ኢትዮጵየዊ ነኝ፡፡ ሓላፊነትም ያለብኝየቤተክርስቲያን አባት ነኝ፡፡ ስለዚህ ስለሀገሬና ስለ ቤተ ክርስቲያኔ እቆረቆራለሁ፡፡
.እኔን ለመግደል እንደወሰናችሁ አውቃለሁ፡፡ስለዚህ በእኔ ላይ የፈለጋችሁትን አድርጉ፡፡ግን ተከታዮቼን አትንኩ» በማለት ሕያው በሆነቃላቸው መለሱ፡፡ ሰማዕተ ጽድቅ በሆነደማቸው አተሙ፡፡ አኩሪ በሆነ አባታዊሓላፊነታቸው ለአገር፣ ለቤተክርስቲያን፣ለወገን ሁሉ አለኝታነታቸው አረጋግጠውበሰማዕትነት አለፉ፡፡ / መርሻአለኸኝ/ዲያቆን/፣ 1996ዓ.ም፣ዜና ጳጳሳትኢትዮጵያውያን፣ገጽ.77/

በረከታቸው ይደርብን!

Yared Shumete :https://www.facebook.com/shumeteyared/photos/a.1474134062917101.1073741829.1381171442213364/1619884771675362/?type=3&theater

አቡነ ጴጥሮስ - Abune Petros (1892 - 1936)

10176 views
0

Uploaded to 5 years ago