Advertisment

Avocado Face Mask - አቮካዶ የፊት ጭንብል

Loading...
1,777 Views
Published

Avocado Face Mask - አቮካዶ የፊት ጭንብል::

በቤት ውስጥ የሚሰሩ የአቮካዶ የፊት መዋቢያዎች- እንዴት እንደሚሰሩ
የአቮካዶ የፊት መዋቢያዎችለቆዳዎ አስደናቂ የውበት ምንጭ ናቸው፡፡ ፍራፍሬው ብዙ ማዕድናትን እንደ ብረት፣ ፖታሲየም፣ ካልሺየም፣ ሶዲየም፣ መዳብ፣ ማግኔዢየም ወ.ዘ.ተ የያዙ ናቸው፡፡ ቪታሚን ኤ፣ ኢ፣ ቢ እና ኬንም የያዙ ናቸው፡፡ የዚህ የተለየ ውህድ ውጤት የአቮካዶ የፊት መዋቢያ የላይኛውን ቆዳ በመዝለቅ የታችኛው ክፍል የሚደርስ ሲሆን በደረቅ ቆዳ ላይ የመለጠጥ ባህሪን ይሰጣል፡፡
በቤት ውስጥ የሚሰራው የአቮካዶ የፊት መዋቢያ ከተፈጥሮ የፊት መዋቢያዎች መካከል በጣም ምርጡ ሲሆን ቆዳን በመመገብ እና ጥንካሬን በመስጠት ይታወቃል፡፡ ይህ ፍራፍሬ ለቆዳ ተስማሚ በሆኑት ማዕድናት እንደ ብረት፣ ካልሺየም፣ ፖታሲየም፣ ሶዲየም፣ መዳብ፣ ማግኔዢየም ወ.ዘ.ተ ቪታሚን ኤ፣ ኢ፣ ቢ እና ኬ እና በፈሳሽ ቅባት የተሞላ ነው፡፡ በዚህ ፅሁፍ በቤት ውስጥ የሚሰራ የአቮካዶ የፊት መዋቢያ እንዴት እንደሚሰራ ያገኛሉ፡፡
የአቮካዶ የፊት መዋቢያ ከኬሚካል እና ከሰው ሰራሽ ግብዓቶች ነፃ ስለሆነ ከብዙ መሸጫ ቦታ ላይ ከሚገዙ የውበት ምርቶች ይልቅ አነስተኛ አለርጂ እና የቆዳ መቆጣት እንዲኖረው ያደርጋል፡፡
አቮካዶን እንደ ግብዓት በመጠቀም የሚሰራው ፊት መዋቢያ በብጉር ለሚጠቃ፣ ለደረቅ እና ቶሎ ለአደጋ ለሚጋለጥ ቆዳ ጥሩ ነው፡፡
የአቮካዶ የፊት መዋቢያ በጣም ደየረቀ ቆዳን የመለጠጥ ሁኔታውን ለማሻሻል የውስጠኛው የቆዳ ክፍሎች ሊደርስ ይችላል፡፡
የማርጀት ሂደትን ለመቀነስ አስደናቂ ስራን ይሰራል፡፡
አቮካዶ ለጤና ብቻ ሳይሆን ጥሩ የሚሆነው የደረቀ ቆዳንም ያረጥባል፡፡ እንደ እርጎ፣ ወተት እና ማር የያዘው መዋቢያ ለደረቀ ቆዳዎ ጥሩ ነው፡፡ የደረቀ ቆዳዎን ለመመገብ፣ ለማለስለስ፣ ለማንፃት፣ እና ለማርጠብ የራስዎን በቤት ውስጥ የሚሰራ የአቮካዶ የፊት መዋቢያን ይሞክሩ፡፡
የአቮካዶ ማር መዋቢያ፡- ይህ ለደረቅ ቆዳ የፊት መዋቢያ ለመስራት ቀላል የሆነው አቮካዶ እና ማር የሚባሉትን 2 የተፈጥሮ ግብአቶችን የሚጠቀም ሲሆን ሁለቱም እንደ የተፈጥሮ ማርጠቢያ ያገለግላሉ፡፡ ይህ መዋቢያ ለቆየ፣ ለተጨማደደ እና ለደረቀ ቆዳ የሚያስገርም ስራ ይሰራል፡፡ አንድ ሙሉ ለሙሉ የበሰለ አዲስ የተቆረጠ አቮካዶ ይውሰዱ፤ ቆዳው እና ዘሩን ያስወግዱ፤ ከዚያም በጎድጓዳ ሳህን ውስጥ የሚበላውን የአቮካዶ የውስጠኛው ክፍል ለንቅጠው ያስቀምጡ፡፡ 1 የሻይ ማንኪያ ማር በመጨመር ተመሳሳይ ውህድ እሰከሚሆን ድረስ ድብልቁን ያማስሉ፡፡ በቆዳው ላይ ያድርጉት እና ለ 10-15 ደቂቃዎች ይተውት፡፡ ለብ ባለ ውሀ ድብልቁን ከፊትዎ ላይ ይጠቡት እና በለስላሳ ፎጣ ፊትዎን በዝግታ ያድርቁ፡፡
የተፈጨ አጃ አቮካዶ የፊት መዋቢያ፡- ይህ እንደ ታላቅ የማርጠቢያ መዋቢያ የሚያገለግል እና የተጎዳ ቆዳን ወደነበረበት ቦታ ለመመለስ ይረዳል፡፡ ½ የበሰለ አቮካዶ እና ½ የተፈጨ አጃ ይውሰዱ፡፡ በተፈጨ አጃ ማሸጊያ ላይ በተፃፈው መመርያ መሰረት የተፈጨ አጃውን ያብስሉት እና ከሚበላው የአቮካዶ የውስጠኛው ክፍል ተመሳሳይ ይዘት ወዳለው ውህድ እስኪመለስ ድረስ ከተለነቀጠው አቮካዶ (ያለ ቆዳው እና ዘር) ጋር ያዋህዱት፡፡ በቆዳዎ ላይ ያድርጉት እና ከ 10-15 ደቂቃ ወይም እስከሚደርቅ ድረስ ይተውት፡፡ ይህን ካደረጉት በኋላ ለብ ባለ ውሀ ይታጠቡት እና በለስላሳ ፎጣ በዝግታ ቆዳዎን ያድርቁ፡፡
የእርጎ አቮካዶ የፊት መዋቢያ፡- እርጥበትን ወደ ቆዳዎ ለመሳብ ከፈለጉ ይህ መዋቢያ ተዓምር ይሰራል፡፡ እርጎ በብጉር ለሚጠቃ ቆዳ በጥሩ ሁኔታ የሚሰራ ነው፡፡ ምክንያቱም ባክቴሪያ የሚገል ላክቲክ አሲድ አለው፡፡ የተለመደው እርጎ በትንሹ አሲድ ያለው ሲሆን የቆዳውን ፒ. ኤች. ለማስተካከል እና ለመመለስ ይረዳል፡፡
ይህ በደንብ የሚሰራው በበጋ ወቅት ነው፡፡ ¼ የበሰለ አቮካዶን በጎድጓዳ ሳህን ውስጥ ጉብታው ነፃ እስከሚሆን ድረስ ይለንቅጡ፡፡ 1 የሻይ ማንኪያ የተለመደ እርጎ እና ½ የሻይ ማንኪያ ማር ከሚበላው የአቮካዶ የውስጠኛ ክፍል ጋር ይደባልቁ፡፡ ተመሳሳይ ውህድ እስከሚያገኙ ድረስ ድብልቁን በደንብ ያማስሉት፡፡ በቆዳዎ ላይ መዋቢያን ያድርጉት እና ለ 10-15 ደቂቃዎች ወይም እስከሚደርቅ ድረስ ይተውት፡፡ ለብ ባለ ውሀ ይጠቡት እና ቆዳዎን በዝግታ ያድርቁ፡፡
የተፈጥሮ ውበት ምክር፡- ቆዳዎ ቅባታማ ከሆነ አነስተኛ ቅባት ያለውን ይፈልጉ፡፡
የአቮካዶ፣ የሙዝ፣ የእንቁላል የፊት መዋቢያ፡- ½ የበሰለ አቮካዶ፣ ½ የበሰለ ሙዝ እና 1 የእንቁላል አስኳል ይውሰዱ፡፡ ሁሉንም ግብዓቶች በአንድ ላይ ውሁዱ ተመሳሳይ ይዘት እስከሚሰራ ድረስ ይለንቅጡት እና ያደባልቁት፡፡ በቆዳዎ ላይ ያድርጉት እና ለ 10- 15 ደቂቃዎች ይተውት፡፡ አንዴ ይህን ካደረጉ በኋላ ለብ ባለ ውሀ ይታጠቡት እና በለስላሳ ፎጣ ቆዳዎን ያድርቁ፡፡
እነዚህን በራስዎ የሚሰሯቸው የአቮካዶ የፊት መዋቢያዎችን ለመስራት እና ለመጠቀም እንዴት ቀላል እንደሆነ አሁን መመልከት ይኖርባችኋል፡፡ ውድ ያልሆኑ እና ከኬሚካል ነፃ ናቸው፡፡ በሳምንት አንድ ቀን አንዳቸውን መጠቀም የሚችሉ ሲሆን ቆዳዎ የልጅ እየሆነ እና እያማረ እንደሚመጣ ይመልከቱ፡፡
የተፈጥሮ ውበት ምክሮች
i) የላይኞቹ ተጨማሪ ግብዓቶች አማራጮች ናቸው፡፡ የአቮካዶ የፊት መዋቢያ በአቮካዶ ብቻ እንኳን ቢሰራ ውጤታማ ናቸው፡፡ ለተለየ ተጨማሪ ባህሪያቸው ሊጨምሩ የሚችሉት አማራጭ ግብዓቶች የቆዳዎን ጤና ያሻሽላሉ፡፡
ii) ለፊት መዋቢያ አገልግሎት ለስላሳ እና የበሰለ አቮካዶ ይጠቀሙ፡፡
iii) የአቮካዶ መዋቢያን ቀዝቃዛ እና የሚያድስ ለማድረግ ከመተቀምዎ በፊት በማቀዝቀዣ ውስጥ ለተወሰኑ ደቂቃዎች ያስቀምጡት፡፡
iv) በፊት መዋቢያ ላይ እንቁላል የሚጨምሩ ከሆነ መዋቢያው ቆዳዎትን ለማጥበቅ ይረዳል፡፡
v) የመዋቢያ ግብዓቶቹ ወደ ቆዳዎች ቀዳዳዎች ዘልቀው እንዲገቡ ለማድረግ መዋቢያውን ከመጠቀምዎ በፊት ፊትዎን ለብ ባለ ውሀ ይታጠቡ፡፡
vi) እጅግ በጣም ደረቅ ቆዳ ላላቸው ሰዎች ምክር፡- የአቮካዶን የፊት መዋቢያን በጣም እንዲረጥብ ለማድረግ የተወሰኑ የወይራ ዘይት ጠብታዎች ይጨምሩበት፡፡
vii) ማንኛውንም መዋቢያዎች ከመጠቀምዎ በፊት ሜካፖችን እና ቆሻሻዎችን ለማስወገድ ፊትዎን ለብ ባለ ውሀ ይታጠቡ፤ ከዚያም የፊት መዋቢያው በጣም ጥሩ ውጤት ይሰጥዎታል፡፡
viii) ማንኛውም ግብዓቶች ለቆዳዎ አለርጂ ከሆነ አይጠቀሙ፡፡
ix) አቮካዶ ልብስዎ ላይ ሊፈናጠቅ ስለሚችል የአቮካዶ የፊት መዋቢያን ሲያዘጋጁ ወይም ሲያደርጉ የድሮ ቲሸርቶችን ይልበሱ፡፡

የአማርኛ የምግብ ዝግጅት መምሪያ ገፅ - Amharic Cooking Channel

እንኳን ወደ ምግብ ዝግጅት መምሪያ ገፃችን በደህና መጡ። ይህ ገፅ የመላው አለምን የምግብ ዝግጅት መምሪያ የያዘ ሲሆን በኢትዮጵያ ብሄራዊ ቋንቋ አማረኛም የቀረበ ነው። ይህ ገፅ የሚያተኩረው ኢትዮጵያዊ ባልሆኑት የምግብ ዝግጅቶች ነው፤የኢትዮጵያ የምግብ ዝግጅት መምሪያ ፈልገው ከመጡ እባክወ ይህንን ሊንክ ተጭነው በተለየ ሁኔታ ኢትዮጵያዊ የሆኑ የምግብ ዝግጅቶችን ብቻ የሚያገኙበትን ድረገፅ ይጎብኙ። http፡//www.howtocookgreatethiopian.com/